Site icon ETHIO12.COM

ለመዲናዋ የምግብ ጨው የሚያቀርቡ አከፋፋዮች ላይ እርምጃ ተወሰደባቸው

ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታን በመጠቀም አላስፈላጊ ዋጋ በመጨመር የምግብ ጨው ዋጋ እንዲጨምር ባደረጉ ሶስት ቀጥታ አከፋፋይ ነጋዴዎች ላይ የንግድ ፍቃዳቸውን የመሰረዝና ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉ ተገለጸ፡፡

ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታን በመጠቀም አላስፈላጊ ዋጋ በመጨመር የጨው ዋጋ እንዲጨምር ባደረጉ ሶስት ቀጥታ አከፋፋይ ነጋዴዎች ላይ የንግድ ፈቃዳቸውን መሰረዝን ጨምሮ የንግድ ተቋማቸው ታሽጎ ጉዳያቸውም በፍርድ ቤት እንዲታይ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል ።

መጭውን የዘመን መለወጫ በዓል ታሳቢ በማድረግ በሁሉም የሸማች ማህበራት ሱቆች አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች እየቀረበ መሆኑ ተጠቅሷል።

የግብርናና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን ቀጥታ ለማቅረብ እየተሠራ ነው ተብሏል።

የሀሰት መረጃዎችን በሚያሰራጩ እና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ የንግድ ተቋማት ላይ ህብረተሰቡ ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን ማድረግ እንዳለበት ጥሪ መቅረቡን ከአ/አ ከተማ ፕሬስ ሴክረተሪ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ENA

Exit mobile version