Site icon ETHIO12.COM

ዓለም ላይ አንድ ሀቅ አለ

አሜሪካ የቻይናን መነሳት እንደማታቆመው ሁሉ፣ ግብጽም የኢትዮጵያን መነሳት ልታቆመው አትችልም።

መጽሃፍ ቅዱስ “ እጆቿን ወደ እግዜአብሔር ትዘረጋለች” ያላት ኢትዮጵያ ትነሳለች።

ነብዩ መሃመድ “ የፍትህ አገር” ብለው የመሰከሩላት ኢትዮጵያ ትነሳለች።

ሄሮድተስ “ የውቦችና እና የአንጋፋዎች” አገር ሲል የገለጻት ኢትዮጵያ ትነሳለች።

ከ 2ሺ ዓመታት በፊት ሲኩለስ ፦ “ ኢትዮጵያውያን ከፍጥረታት ሁሉ የመጀመሪያ ናቸው” ሲል ምስክርነቱን የሰጠላት ኢትዮጵያ ትነሳለች።

እስጢፋኖስ ከ ሺ ዓመት በፊት፦ “ ኢትዮጵያ የምድራችን ቀዳሚ አገር ናት” ያላት ኢትዮጵያ ትነሳለች።

ባርባዶሳዊው አርኖልድ ፎርድ፦ “ጉልበተኞች የሚንበረከኩልሽ የአባቶቻችን አገር ኢትዮጵያ፣ ልጆችሽ ከባህር ማዶ ስምሽን በናፍቆት ይጣራሉ” ሲል

ቅኔ መወድስ የከተበላት ኢትዮጵያ ትነሳለች።

ኔልሰን ማንዴላ፦ “ ምንጊዜም በምናቤ ልዩ ስፍራ ያላት አገር ናት። ኢትዮጵያን መጎብኘት ፈረንሳይን፣ እንግሊዝንና አሜሪካን በድምሩ ከመጎብኘት

ይበልጣል። “ብሎ ያቆለጳጰሳት ኢትዮጵያ ትነሳለች።

ክዋሜ ንክሩማህ ” ያች የአፍሪካ አንጸባራቂ እንቁ፤ ከኮረብታዎች ሁሉ ከፍ ብላ የተቀመጠች፣ የማይነጥፈው የአባይ ወንዝ ወላጅ እናት ኢትዮጵይ –

ትነሳለች። የጥበበኞች አገር፤ የአፍሪካ የጥንት አስተዳደር ስር መሰረት፤ የባህላችን ምንጭ የሆነችዋ ጠበበኛዋ ኢትዮጵያ ተነስታ የአፍሪካን ተስፋና

እጣ ፋንታ ትወስናለች።” ሲል ትንቢት የተነገረላት ኢትዮጵያ ትነሳለች። Ethiopia shall rise!

በየዘመኑ የተነሱ ሃይሎች ሁሉ ኢትዮጵያን ለመጨበጥ ሞክረዋል። ሁሉም ግን እጃቸው እየተለበለበ ተመልሰዋል። ዛሬም የኢትዮጵያን እጅ

ለመጨበጥ የሚክለፈለፈው ብዙ ነው። እነሱም በተራቸው እጃቸው እየተለበለበ ይመለሳሉ።

ቀደምቶቹ ሃያል አገራት ወደ ጥንት ሃያልነታቸው የሚመለሱበት ጊዜ እየመጣ ነው። የጥንት ቦታችንን የምንይዘበት ጊዜ ከፊታችን ተዘርግቶ እያየነው

ነው።

የእጃችንን ግለት ለፍየሎቹ ለማሳየት አጼ ዮሐንስን ከሞት መቀስቀስ አይጠበቅብንም። እኛ ጉራና ጉንደት ላይ ፍየሎቹን ( ግብጾቹን) ዶጋሊና አድዋ

ላይ በሬዎቹን( አውሮፓውያንን) የለበለቡት እጆች ወራሾች ነን።

እኛ የአባቶቻችንን ታሪክ አንረሳም። የአባቶቹን ታሪክ የሚረሳ ልጅ፣ ታሪክ ለመስራት ያልታደለ ነውና። እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም በዙሪያችንን የከበቡንን

ሁሉ አንድም በጥበብ ሌላም በሚያቃጥለው እጃችን አሸንፈን የአገራችንን ትንሳኤ እናውጃለን። ከእኛ የሚጠበቀው ትንሹ ነገር መተባበር ነው። አንበሳ

እርስ በርሱ ተፋልሞ ሲዳከም፣ ፍየል በቀንዷ ወግታ ልትገለው ትችላለች። የእርስ በርስ ፍልሚያውን ለነገ እናሳድረውና እንተባበር። አይሻልም ወገኖቼ?

Fasil yenealem አስተያየታችሁ👉 t.me/fasilyenealem 👈በዚህ ይደርሰኛል #ሼር

Exit mobile version