የጎንደር ከተማ የጸጥታ ምክር ቤት ጥብቅ መመሪያ ማስተላለፉን አስታወቀ። በመመሪያው እንደተጠቀሰው ጤናማ፣ በሥነ ምግባር የታነጸ ትውልድ ለመገንባት ሲባል በከተማዋ ከጫት ጋር በታያያዘ ደንግጓል። ድንጋጌውን የሚተላለፉ እንደሚቀጡ ይፋ ተደርጓል።
ሀገርን ከጥቃት እና ከወረራ እንዲሁም ከጥፋት መታደግ የሚቻለው ከሱስ የፀዳ በሥነ ምግባር የታነፀ በመሆኑ ይህንን ትውልድ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት መነሻ በማድረግ የጎንደር ከተማ የጸጥታ ምክር ቤት በጫት አቅራቢዎች አጓጓዦች፣ አከፋፋዮች፣ ቸርቻሪዎች፣ አስቃሚዎችና ተጠቃሚዎች ላይ የክልከላ ውሳኔዎችን አስተላልፏል ።
አሸባሪው የትህነግ ቡድን እና የትግራይ ወራሪ ከሌሎች ፅንፈኛ ፀረ ኢትዮጵያ ኀይሎች ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የክልላችን ሕዝብ ህልውናን አደጋ ላይ በመጣል ሕዝባችንን በወረራቸው አካባቢዎች በሙሉ ሁሉንም አይነት ግፎች እየፈፀመ ይገኛል።
ይህ ኃይል ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ለማፈራረስ ካለው ህልም ባሻገር ከአማራ ሕዝብ ላይ የማወራርደው ሒሳብ አለኝ በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ መነሻ በማድረግ ወረራ በፈፀመባቸው የክልሉ አካባቢዎች በሕዝቡ ላይ የበቀል በትሩን ማሳረፍ ጀምሯል።
ይህን በማገናዘብ ወረራውን ሊመክት የሚችል የአካባቢውን ሰላም እና ደኅንነት አስተማማኝ እንዲሆን የሚያደርግ መንፈሰ ጠንካራ ወጣት ኀይል በሥነ ልቦና የተገነባ ትውልድ ደግሞ ሀገርን ከጥቃት እና ከወረራ እንዲሁም ከጥፋት መታደግ የሚቻለው ከሱስ የፀዳ በሥነ ምግባር የታነፀ በመሆኑ ይህንን ትውልድ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት መነሻ በማድረግ የጎንደር ከተማ የጸጥታ ምክር ቤት በጫት አቅራቢዎች አጓጓዦች፣ አከፋፋዮች፣ ቸርቻሪዎች፣ አስቃሚዎችና ተጠቃሚዎች ላይ የክልከላ ውሳኔዎችን አስተላልፏል ።
በመሆኑም ከነሐሴ 28/2013 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ ጫት ከሌላ አካባቢ ማጓጓዝ፣ መቸርቸር፣ ማከፋፈል፣ ማስቃምና መቃም ተከልክሏል። በመሆኑም ከነገ ጀምሮ ምክር ቤቱ ክልከላ ባደረገባቸው ተግባራት ላይ ሲሳተፍ የሚገኝ ተሽከርካሪ ግለሰብም ሆነ ድርጅት በሐረግ የሚጠየቅ መሆኑን ምክር ቤቱ በአክብሮት ይገልጻል።
ይህንን የከተማዋ የጸጥታ ኀይል ተከታትሎ እንዲያስፈፀም ታዟል።በጫት ንግድ የተሰማራችሁ የከተማችን የኅብረተሰብ ክፍሎች ዘርፍ ቀይራችሁ በሌሎች የንግድ የአገልግሎት እና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ለመሰማራት ባቋቋምነው ግብረ ኀይል አማካኝነት አስፈላጊውን ጥረት እና እገዛ የሚደረግ መሆኑን እናሳስባለን።
የጎንደር ከተማ ኮምዩኒኬሽን