Site icon ETHIO12.COM

የ3ኛ መብረቅ ኮማንዶ ሻለቃ የግዳጅ ውሎ

በልዩ ዘመቻዎች ሃይል 2ኛ ኮማንዶ ብርጌድ 3ኛ ኮማንዶ ሻለቃ በትግራይ በተደረገው ህግን በማስከበር ዘመቻ ጠላት የሚመከባቸውን ምሽጎች በሶሮቃ ፣ በዳንሻ ፣ በባአካር ፤ በቅራቅር ፤ በሁመራ ፤ በመሶበር ፤ በጨርጨርና በአይደፈር ተራሮች ላይ የተገነቡ የጠላት ምሽጎችን በመስበር የጠላትን ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን በመቆጣጠር የሰሩት ታሪክ የማይረሳው ገድል ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋር በደም የተፃፈ ወርቃማ መዝገብ ነው።

ይህ ኮማንዶ ሻለቃ በመጀመሪያው ዘመቻ ቅድሚያ መቀሌ ከተማን ከመቆጣጠር በተጨማሪ በከተማዋ ውስጥ የነበረውን የጠላት የጦር መሳሪያ ግምጃቤት በመቆጣጠር ለመንግሥት ገቢ አድርጓል።

በከተማዋ መሽገው የነበሩ የጁንታን ሴሎች ከመልቀም ጀምሮ የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ጋዜጠኞች ጋዜጠኛ ፍፁም ብርሃኔና የአይጋ ፎሮም ጋዜጣ ኢዲቶሪያልና የኢትዮጵያ ተወካይ ጋዜጠኛ ታምራት የማነን ጨምሮ በርካታ የሚዲያ ባለሙያዎችን ከየተደበቁበት በማውጣት ለህግ እንዲቀርቡ አድርጓል።

በመቀሌ ከተማ ለ24 ሰዓት ፖትሮሊንግ በማድረግ ህዝብን በማረጋጋት ከመላው ከኢትዮጵያ ህዝብ የሚደረገውን እርዳታ እጀባ በማድረግ ለህብረተሰቡ እንዲደርስ የራሱን ሚና ተጫውቷል።

በሚያዚያ 29 ቀን 2013 ዓ/ም ከሱዳን ሃምዳይት ግዛት የተነሳው የጠላት ታጣቂ ቡድን በአከባቢው ከተሰማራው ከልዩ ዘመቻዎች ሃይል ከ2ኛ ኮማንዶ ብርጌድ 3ኛ ሻለቃ ጋር ውጊያ በመግጠም ከነበረው 320 ጠላት የጁንታ ብርጌድ አዛዥ ኮ/ል በህረ ተበጄ እና የሻለቃው ዋና አዛዥ ሻምበል ተክለወይኒ ታረቀኝን ጨምሮ 100 ታጣቂ ማርኳል። ቀሪዎቹ ደግሞ በተደረገው ውጊያ ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል።

ከጠላት የተማረኩ ንብረቶች 103 ዘመናዊና አዲስ ሞቶሬላ ወታደራዊ መገናኛ ከእና ሙሉ አክሰሰሪና ቅያሪ ባትሪ ፣ 01 አይኮም ፤ ቶሪያ ስልክ 01 ፣ አለም አቀፍ ጥሪ ተቀባይ ሳምሰንግ ስልክ 02 ፣ ብሬን 01 ፣ ክላሽ 05 ፣ ማካሮቭ ሽጉጥ 01 ፣ በርካታ ጥይቶችና የህክምና ቂሳቁሶች በቁጥጥር ስር ውሏል።

የኮማንዶ ሻለቃው የግዳጅ ጉዞ በአንፀባራቂ ድሎች የታጀበ ሲሆን በሁመራ ኮሪደር በራውያን በተሰጠው ግዳጅም በሁመራ ፤ በሰላሲል ፤ በባዕከር ፤ በማይ ሎሚ ፤ በአዲረመፅ ፤ ለ24 ሰዓት በቀንና በሌሊት ፖትሮሊንግ ጥበቃ በማድረግ የጠላትን መግቢያ መውጫ በመከታተል የተሳካ ስራዎችን ሰርቷል።

ጠላት በድንገት በማይፀብሪ ግምባር ማጥቃት በመክፈት በአከባቢው በነበረው አማራ ልዩ ሃይል 24ኛ እግረኛ ክ/ጦርና 31ኛ እግረኛ ክፍለጦሮችን ለማጥቃት በቆረጣ ገብቶ አድርቃይን ሲቆጣጠር ፣ ለሻለቃው አስቸኳይ ግዳጅ ተሰጥቶት ከሁመራ ራውያን ከምሽቱ 5:00 ሰዓት በመነሳት በጎንደር በቀንና በሌሊት ተጉዞ ጨው በር ደርሰ።

በጨው በር ጠላት ጊዜያዊ ድል አግኝቶ ሲፈነጭ እስከ ደባርቅ እየገሰገሰ የነበረውን ጠላት የመከላከል ቁመና በመያዝ ውጊያ ገጠመ። ጠላት ያላሰበው አይቀጡ ቅጣት ተቀጣ። በጨው በር በቴሌ ታወር ተራራ ላይ ደፈጣ የያዘውን ጠላት የሻለቃው ሁለተኛ ሻምበል ደመሰሰ።

የሻለቃው 1ኛ እና 3ኛ ሻምበሎች ተራራውን በመያዝ ሁለተኛ ሻምበል ደግሞ እስፓልቱን በመዝጋት ከምሽቱ 12 ሰዓት የተጀመረው ውጊያ ጠላት በየሰዓቱ የሰው ሃይሉን እየተካ እየገበረ የጀግናው 3ኛ ኮማንዶ ሻለቃ አባላት ደግሞ በጠንካራ መከላከል በሃሺሽ ሰክሮ እየተለፈለፈ የሚመጣውን ጠላት በማነጣጠር እየለቀመ ቁጥር የሌለው ጠላት ረገፉ ፡፡ ሌሊቱ ነግቶ ያለማቆረጥ እስከ ጧቱ 2 ሰዓት ዘልቆ ለ13 ስዓት በተደረገው ውጊያ የጠላትን ቅስም በመስበር ጠላት ባለበት እንዲቆም አደረገ።

በዚሁ ውጊያ ከክፍላቸው ተለይተው ከኮማንዶ ሻለቃው ጋር በመሆን ለ4 ሰዓት በመዋጋት የጠላትን ሲናይፐር የማረኩና የላቀ ጀብዱ የሰሩ የአማራ ልዩ ሃይል 03 አባላትን ክፍላቸውንና በስም ባላውቃቸውም 01 ሴትና 02 ወንዶች የፅናት ተምሳሌት ናቸው።

አሁንም ለ4 ቀናት ጠላትን እንቅስቃሴ በመከላከል ከተገተገ በኋላ ግምባሩን ለእግረኛ ተዋጊ ለምዕራብ ዕዝ በማስረከብ ጉዞ ከጎንደር ከአየር ማረፊያ በአውሮፕላን ወደ ሰመራ ሆነ።

ከሰመራ ወደ ጭፍራ ተጉዞ ለአዳር ባረፉበት ተለዋጭ ትዕዛዝ መጣ። እሱም ጠላት በወልዲያ በኩል ማጥቃት በመክፈት ከተማዋን በከባድ መስሪያ እየደበደበ ስለሆነ በፍጥነት ድረሱ የሚል ነው። አይበገሬዎቹ በጉዞ የደከመው ሰውነታቸው ምንም ሳያርፉ በሽንጣ ረጅሞቹ አውቶብሶች ጉዞ ወደ ውጫሌ ተጀመረ።

ውጫሌ ታሪካዊዋ ከተማ በእጅጉ ተረብሻለች። ይስማ ንጉሥ የውጫሌ ውል ታሪካዊዋ ከተማ በተፈናቃዩ ህዝብና በተዋጊው ጦር እየተርመሰመሰች ነው። ጠላት መርሳን ሰላም አምባንና ልብሶን ከተሞችን በመቆጣጠር ግስጋሴውን ቀጥሏል።

ሁሉም የሻለቃው አባላት በአንድ ቃል ተስማምተዋል ፡፡ እኛ በህይወት እያለን እንዴት ጁንታ በወሎ ምድር ገብቶ በነፃነት ይጓዛል አሉ ፡፡ በፍፁም በጭራሽ አንፈቀድለትም በሚል ደመደሙ።

ሁሉም የሻለቃው አባላት ትጥቃቸውን አጠባበቁ። ተጫማሪ ሎዳቸውንም ከመደበኛ ውጭ ተረክበው ለቀጣይ ግዳጅ እራሳቸውን አዘጋጁ።

ነሐሴ 12/12/2013 ጉዞ ተጀመረ ፡፡ ተጨማሪ ጥይቶችን በግመል በመጫን በኡርጌሳ በመቁረጥ የሊቢሶ ከተማ ፤ ደራ ፤ ሰላም አምባ ፤ ኒኒ በር ፤ የመርሳን ሰንሰለታማ ተራሮችን በማቆራረጥ በመርሳ ከተማ በስተጀርባ በመግባት የወልዲያ መውጫ መንገድ በመዝጋት በጠላት ማዘዣ ጣቢያ ላይ ጥቃት በመሰንዘር የጠላትን ደጀን በማደባየት ሲጠቀምበት የነበረውን 02 ኮብራ የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ጊዜያዊ ስቱዲዮ ፤ 02 ኦባማ አይሱዙ የህክምና ቁስቁስና ትጥቅ ፤ 03 ሲኖትራክ ቀለብና ሲመካበት የነበረውን 02 ታንክ ፤ 02 ዙ-23 አየር መቃወሚያ እጅ በእጅ ውጊያ በቦምብ ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።

በዚህ ግዳጅ የልዩ ዘመቻዎች ሃይል ተጨማሪ ሻለቆችም ታሪክ ሰርተዋል። ጉና እና 3ኛ አየር ወለድ ሻለቆች የወልድያ መንገድ በመዝጋት ፤ ውጋጋን ኮማንዶ ሻለቃ ደግሞ በተራራው በመሆን ለ3ኛ ኮማንዶ ሻለቃ ለከተማ ለምታደርገው ውጊያ ሽፋን በመስጠት የሪፐብሊካን 01 ሻለቃ ደግሞ 3ኛ ሻለቃ ላይ በመደረብ ፈንቅል ሻለቃና ሁሉም በአንድነት በመናበብ በጠላት ላይ ያላሰበውን ጥቃት በመሰንዘር መርሳ ከተማን ተቆጣጥረውታል።

የደቡብ እና ሰሜን ዕዝ እግረኛ ክፍለጦሮች ደግሞ በውርጌሳ በኩል በመዋጋት እስከመርሳ ደርሰዋል። በዚህ ውጊያ አንድ የገረመኝ 3ኛ ሻለቃ 1ኛ እና 2ኛ ሻምበሎች ጥምረት ነው። ሁሉቱም በጋራ በመናበብ የመርሳ ከተማን ሙሉ በሙሉ ከመቆጣጠር በተጨማሪ የጠላትን ታንኮችንና አየር ማቆሚያዎችን ያቃጠሉት እነሱ ናቸውና!

መቶ አለቃ ታሪኩ ሻሜቦ
ከልዩ ዘመቻዎች ሃይል 2ኛ ኮማንዶ ብርጌድ ከ3ኛ ሻለቃ defence Facebook

Exit mobile version