Site icon ETHIO12.COM

“እንቅርት አንድ አደረገን” አብይ አሕመድ

“እንቅርት አንድ አደረገን” ሲሉ ጁንታው ለወደፊት ትውልድ ማስተማሪያ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሠረታዊ ወታደርነት ያሰለጠናቸውን ምልምል አባላት ባስመረቀበት ወቅት ነው።

የኢትዮ 12 ዩቲዩብ ገጽን ላይክና ሰብስክራይብ ያድርጉ

በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን የሚጠላ እና ራስ ወዳድ ቡድን መሆኑን ተናግረዋል። አሸባሪው ህወሓት ለኢትዮጵያ እንቅርት ሆኖባታልም ነው ያሉት። እንቅርት ሌላውን አካል ሳይጎዳ በጥንቃቄ እንደሚወገድ ሁሉ ለመጪው ትውልድ ማስተማሪያ እንዲሆን ተደርጎ እንደሚወገድ አመልክተዋል። ለዚህም ዝግጅት እያደረግን ነው። ሳይነኩት የሚፈራ መከላከያ እንገናባለን። ኢትዮጵያ ከልመና ነጻ ትወጣላች።

ኢትዮጵያ ፈተና ላይ መሆኗን በማንሳትም ይህን ፈተና በብልሃትና አንድነት ማለፍ እንደሚገባና ለዚህም ቆራጥነት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል። አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እና አንድነቷን ለመበተን እየሰራ ቢሆንም በተቃራኒው ኢትዮጵያ ዳግም አንድ እንድትሆን አድርጓታልም ብለዋል፡፡

የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ በበኩላቸው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ዛሬ ሰልጥናችሁ በመመረቃቻሁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን ፈተና አለንልሽ ለማለት ስለቆማችሁ እናመሰግናለን ያሉት ጄኔራል ብርሃኑ፥ ተመራቂዎቹ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ህወሓት ለመመከት ስለምትቀላቀሉ ትልቅ ምስጋና አለን ብለዋል።

እራሱን እየሰዋ ያለውን የኢትዮጵያን የቁርጥ ቀን ልጆች ለመቀላቀለል ስለወሰናችሁ እንኳን ደስ አላችሁም ነው ያሉት ጄኔራል ብርሃኑ።

ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተወጣጥተው በመሰልጠን ዛሬ የተመረቁት ምልምል አባላት በስልጠና ቆይታቸው ዘመናዊ ንድፈ ሀሳብ በተግባር የተደገፈ ወታደራዊ የሙያ ትምህርት ተከታትለዋል።

በ1972 ዓ.ም. በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የተመሠረተው የሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለሀገር ሉአላዊነት መረጋገጥ ና ለአለም ሰላም መከበር አስተዋጽኦ ያበረከቱና በማበርከት ላይ የሚገኙ የሠራዊት አባላት ያፈራ አንጋፋ ተቋም ነው።

Exit mobile version