Site icon ETHIO12.COM

የኦነግ፣ የኢዜማና የአብን አመራሮች ካቢኔ ሚኒስትር ሆኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ባቋቋሙት አዲስ ካቤኔ የኢዜማ መሪ ዶክተር ብርሃኑ ነጋን፣ የኦነግ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ቀጀላ መርዳሳ ቱሉና የአብን ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላ የካቢኔ ሚኒስትር አድርጎ ሾመ።

ከሃያ ሁለቱ የካቢኔ አባላት ውስጥ ሶስቱ የሃላፊነት ደረጃዎች ለተቀዋሚ ፓርቲ አመራሮች ሽመት ሲሰጥ እንደተጠቆመው ዶክተር ብርሃኑ የትምህርት ሚኒስትር ሆነዋል። አቶ ቀጀላ ቱሉ የስፖርትና ወጣቶች ሚኒስትር፣ አቶ በለጠ ሞላ ጌታሁን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነዋል። ሁለት ተቃውሞና አስራ ሁለት ድምጸ ተአቅቦ ነው ሹመቱ የጸደቀው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሹመቱን ይፋ ከማድረጋቸው በፊት “አደራ ሌብነትንና ልመናን ታገሉ፣ በህዝብና በፓርላማው ስም አደራ እላችሁዋለሁ” ብለዋል። ልመና አንገት የሚያስደፋ ክፉ ነገር መሆኑንን በማንሳት ከልመና እንድነወጣ በመያያዝ መስራት እንዲገባ ለምነዋል።

“ሚኒስትር ስትሆኑ የኢትዮጵያ ሚኒስትር ናቹህ” ሲሉ የብሄርና የሰፈር እሳቤን እንዲጥሉ አመላክተዋል። ከሁሉም በላይ በሃሳብ ልዩነት ውስጥ ተባብሮ አገርን ማገልገል አስፈላጊ መሆኑንን ለመጪው ትውልድ ለማስተማር መንገድ መጥረግ እንደሚገባ፣ ለዚሁም በዋናናት ይህ ካቢኔ ሃላፊነቱን ሊወስድ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

ሹመቱ እንዲሁ የይስሙላ እንዳልሆነ ከሹመቱ በሁዋላ ማብራሪያ ሲሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት የቲክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስትር በአስሩ ዓመት ከተያዙት ቁልፍ እቅድ ማስፈጸሚያ አምስት ምሶሶዎች ውስጥ አንዱ መሆኑን በመጥቀስ አቶ በለጠ ሞላ ለዚህ ሃላፊነት መታመናቸው ብልጽግና አብሮ የመስራት እመነቱ ከፍተኛ መሆኑንን የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸዋል።

ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በኢኮኖሚክስ ሶስት ዲግሪ ያላቸው በመሆኑ በሙያቸው መመደብ ይገባ እንደነበር ለተጠቆመው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመልሱ የተማሩት በኢኮኖሚክስ ዘርፍ ቢሆንም እድሜያቸውን ያሳለፉት በትምህር ባለሙያነት በመሆኑ የትምህርት ሂደቱን ለማዝመንና ለማሻሻል ታላቅ ድጋፍ እንደሚሆኑ እምነት እንዳላቸውና ይህ ተገምግሞ ሃላፊነቱ እንደተሰጣቸው አመልክተዋል።

ሌሎች ያልተካተቱ ምርጥ ባለሙያዎች በመኖራቸው በሚኒስትር ዳኤታነት ተካተው አዲሱ ካቢኔ ጠንካራ እንዲሆን እንደሚደረግ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አመልክተዋል።፡

Exit mobile version