ETHIO12.COM

ዝናሽ ታያቸው – ስኬታማዋ ቀዳማዊ እመቤት

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ መሪነት መምጣታቸውን ተከትሎ የታውቁት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በልማትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ግንባታ ላይ እያሳዩ ያሉት ተሳትፎና ትጋት ” ስኬታማዋ ቀዳማዊ እመቤት” ያሰኛቸዋል።

ባላቸው ህይወታቸው እስኪያልፍ ቀዳማዊ እመቤት የነበሩትና ባለቤታቸው ” ትንታግ” የሚሏቸው ወ/ሮ አዜብ ሁለት አስርት ዓመት በያዙት ክብር ምን እንደሰሩበት በውል የሚዘረዘር መረጃ የለም።

የበላይ ተጣባቂ በነበሩበት የቅዱስ አማኑኤል አዕምሮ ሆስፒታል ታካሚዎች አንሶላ አጥተው፣ ቱሃን መኝታ ከልክሏቸው ” ታንከኛ አላስተኛ አለን” ብለው ሲያማርሩ ወ/ሮ አዜብ ምላሽ አልነበራቸውም። የዚህ ዜና ጸሃፊ በውቀቱ አዲስ አበባ እህል ተራ ያለውንና ገፈርሳ አካባቢ ያለውን ማገገሚያ መመልከቱንና ያየውን በወቅቱ መዘገቡ ጩኸት እንዳስነሳ ያስታውሳል።

ወ/ሮ ዝናሽ እንደ ካድሬ ሳይሆን እንደ አንድ መላክም እናት የሚናገሩ፣ ሲናገሩ የካድሬ ቃላት በድንገት እንኳን ከአፋቸው የማይወጣ፣ ሰው ሰው የሚሸቱ፣ በተባለበት ጊዜ ፕሮጀክታቸውን የሚያስረክቡ፣ መሆናቸውንና በዚህ የጭንቅ ሶስት ዓመታት ውስጥ አሰርተው ያስረከቡትን የለማትና የአገልግሎት ተቋማት ላየ ምስጋና የማይበዛባቸው፣ ክብር ሊቸራቸው የሚገባቸው ድንቅ ሴት ናቸው።

ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ያስገነቡትን የዳቦ ፋብሪካ አስረክበዋል። ፋብሪካው በቀን አንድ ሚሊዮን ዳቦ የሚያመርት ሲሆን ለበርካታ አቅመ ደካሞችም የስራ ዕድል እንደሚሰጠ ተጠቁሟል። ባለቤታቸው የስንዴ ማሳ በመመልከት የመስክ ክትትል ሲያደርጉ እሳቸው ዳቦ ፋብሪካ አስረክበዋል።

ለስድብና ለማሽሟጠጥ የሚኖሩ ዛሬ ማታ ምን ብለው እንደሚተነትኑ የሚታውቀ ቢሆንም ንጹህ ህሊና ያላቸው ወገኖች መልካሙን በማድነቅ ክብር ሊሰጡዋቸው ግን ግድ ነው። ከደሃ ጉሮሮ የሚዘርፉ፣ ስጋ ከሌለው ደሃ ላይ አጥንቱን የሚግጡ በኖሩበት መቀመጫ ላይ እንዲህ ዓይነት ተግባር የሚፈጽሙ ሲገኙ ማድነቅ ሌሎችንም ማበረታታት ነውና ዝግጅት ክፍላችን ለቀዳማዊት እመበቤት ዝናሽ ታያቸው ምስጋና ያቀርባል።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የዳቦ ፋብሪካውን ቁልፍ ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት አስረክበዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዳቦ ፋብሪካው ርክክብ ወቅት እንደገለጹት በከተማዋ የኑሮ ውድነትን መንስኤ የአቅርቦት እና ፍላጎት አለመጠጣም ችግር ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያን የመለወጥ እና የማበልጸግ ጊዜ ላይ እንገኛለን ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማችን የኑሮ ውድነቱን ለማቃለልም የቀዳማዊ እመቤት ጽ/ቤት የደሀውን ማህበረብ ተጠቃሚ ዳቦ ፋብሪካ ከፍተው በማስረከባቸው በከተማዋ ነዋሪዎች ስም አመስግነዋል።

ፋብሪካው ከዳቦ ማምረት ባለፈ ለእናቶች የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸው የገለፁት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለእናቶች የመሸጫ ቦታ በማዘጋጀት ዳቦው በቀላሉ የሚሰራጭበትን ሁኔታ እንደሚመቻች ይደረግላቸዋል ብለዋል።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በበኩላቸው ይሄ የዳቦ ፋብሪካ የስንዴ አቅርቦት ችግር እንዳይገጥመው ከክልል የስንዴ አምራች ገበሬዎች በቀጥታ የሚያገኝበት ሁኔታ ይመቻቻል ብለዋል።

ይህ ፋብሪካ ተገንብቶ በዚህ ደረጃ እውን እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

በቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት 217 ሚሊየን ብር በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ6ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የተገነባው ዳቦ ፋብሪካው በቀን 1 ሚሊዮን ዳቦ በማምረት አቅም ያለው ሲሆን ለ450 ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር ይሆናል።

Exit mobile version