Site icon ETHIO12.COM

“እኔ አላማረኝም ” ብል ሟርት ይሆን ? ማጭድ ከፊት መድፍ ከሁዋላ!!

አንድ ጨዋታ አዋቂ ወዳጄ በንግግሩ መካከል ” እኔ አላማረኝም ” ማለት ይወድ ነበር። ብዙዎች የአገራችን ሰዎች ” ሲያልቅ አያምር” ይላሉ። ዛሬ እኔ እነዚህ ሁለት አባባሎች መካከል ነኝ። አላማረኝም። ምክንያቱም እዛ ቤት ያለው ማእበል እዚህም ቤት በብዛት አለ። እዛ ቤት ያለው ክፋት ልክ ሲያልፍ እዚህም ይሆናል። ገደብ አልፏልና መቼ ይጀመራል የሚለው ጉዳይ ካልሆነ በቀር ሕዝብ አምርሯል። የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ማንን ነጻ ለማውጣት ቀደም ሲል ጀምሮ አማራ፣ ኦሮሞንና ሶማሌ፤ አሁን ደግሞ በተለይ የአማራን ቀጥሎ የአፋርን፣ ቀጥሎ … እያለ ለማጥፋት እንደሚክለፈለፍ ደጋፊዎቹ ከሚያውቁት በላይ ሕዝብ አውቋል።

ይህን ሳስብ ነው ” እኔ አላማረኝም ወይም ሲያልቅ አያምር” ለማለት የተገደድኩት። የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ የትግራይ ሕዝብን አይከስም። የትግራይ ሕዝብ በሚጠይቀውና ሊሆን በሚፈለገው ጉዳይ ላይ አስተያየት አይሰጥም። የትግራይ ህዝብ ፍላጎት ከሆነ መገንጠል ያለ ሪፈረንደም በ24 ሰዓት እንዲወሰናላቸው ይመኛል። የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ዋና ዓላማ ስጋቱን መግለጽ፣ ከዚያም ባለፈ ትህነግ የሚባል የዲያቢሎስ ሽንት ለምን ያህል ዘመን ደም እየጠጣ መኖር እንደሚመኝ መጠይቅ ነው። ከዛም አልፎ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ሆኖ ለምን ከክልሉ አልፎ ወሎዬን ይጨፈጭፋል? ለምን ጎንደሬን ይጨፈጭፋል? ለምን አፋርን ይጨፈጭፋል? ለምን ልክ እንደ ጋምቤላ፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ቢኒሻንጉል … ክልሉን እየመራ አይኖረም? ለምን ከፍጥረት እስከ ግንዘት ክፋትን እየጋተ ሕዝብ ሲያተራምስ ይኖራል? ለምን ግማሽ ምዕተ ዓመት ሙሉ ኢትዮጵያና ሕዝቧን ሰላም ነስቶ መኖርን ይመኛል? ለምን የማይወዳትን ኢትዮጵያ አይፋታም? ለምን ለቋት አይሄድም? ለምን የሌሎችን የመኖር መብትና እየዘረፉ ሳይሆን ዶሮ እያረቡ እንዳይኖሩ ያደርጋቸዋል? ለምን ይወራቸዋል? ለምን ይዘርፋቸዋል? እንዴት ቡሃቃ ገልብጦ ሊጣቸውን ይጠጣባቸዋል…. የሚሉትን ጉዳዮች ማንሳትና ወደፊት ምን ይሆናል? የሚለውን ስጋት ማሳየት ነው።

ዛሬ ከሃዲያንና ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ የቆሙ ወገኖች ናቸው እየተፋለሙ ያሉት። ጦርነቱ መደበኛ ጦርነት አይደለም። ከፊት ማጭድ የተሸከሙ አጫጆችን ያሰለፈ ሃይል ነው። ዓላማው የደረሰ እህል በመዝረፍ ወደ ትግራይ ማጋዝ ሲሆን ሕዝቡ ቀዬውንና ንብረቱን ለቆ እንዲሸሽ ከሁዋላ ያለው ሃይል ከባድ መሳሪያ በመተኮስ ንጹሃንን ያሸብራል። ይገላል። ከፊት ለዝርፊያ ማጭድ ያነገበው ዘራፊ እየዳኸ የደረሰ ሰብል ያጭዳል። ከብት ይነዳል። ይህ በይፋ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት የተገለጸ፣ የሸሹ የአካባቢው ነዋሪዎች የመሰከሩት እውነት ነው። ይህን መስማት በንዲህ ያለ የእህል ሌባና ሌቦች ስንመራ የነበርነበትን ዘመን እያሰቡ ከማልቀስና ከመቆጨት በላይ የሆነ ስሜት ይፈጥራል።

ከፊት የሚያሰልፋቸው ማጭድ የያዙ ሌቦች አዛውንት፣ ሴት፣ ወንድ… አይለይም። አንዱ ወገን ለዝርፊያ፣ ሌላው ወገን ለጭፍጨፋ እንደ ማዕበል ደቡብ ወሎን ወረዋል። ሁለት ሚሊዮን የሚሆን ሃይል ያዘጋጀው አጥፍቶ ጠፊ እንደ ትል እየተርመሰመሰ እህል በማጭድ ያወድማል። በቀያቸው የተቀመጡ ንጹሃንን ይጨፈጭፋል። ንብረታቸውን ያግዛል። አጋፋሪዎቹ አውሮፓና አሜሪካ ሆነው በማህበራዊ ገጻቸው ቱልቱላ ይነፋሉ። የሊጥና እንኩሮ ሌቦች ልጆች መሆናቸው ረስተው እንደ ጀግና ያለሃፍረት ያቅራራሉ። ለጊዜው ተሳክቶላቸዋል ሊባል ይችላል። ግን ነገሩ ሲያልቅ አያምር ነው።

በሰሜንም ሆነ በደቡብ ጎንደር ነዋሪዎች ” ዘራፊና ቅንቅናም” ሲሉ የሚጠሩት ሃይል በተመሳሳይ የሕዝብ ማዕበል አስነስቶ ከወረረ በሁዋላ የቻለውን ዘርፎ በማጋዝ፣ ሊጥ ሲጠጣ፣ አሻሮ ሲቅም፣ ችጋሩን ሲያራግፍ፣ አሸቦ ሲልስና የአቅመ ደካሞች ሌማት ሲያደርቅ፣ መሰረተ ልማት ሲያቃጥልና ሲወድም ቆይቶ ተውቅጦ የወጣው በህዝብ ማዕብለ ክተት ታውጆበት እንደሆነ ይታወቃል።

“ኢትዮጵያን የምታባለው አገር እኛ እንዳሻን እየዘረፍን ካልመራናት እናፈርሳታለን” በሚል የህዝብ ማዕበል አስነስቶ በሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ እንዲሁም በአፋር ጭፍራ በኩል ወረራ እያካሄደ ያለው የትግራይ ነጻው አውጪ ቡድን ለምን አካባቢው፣ አገሩ፣ እርስቱ ያልሆነውን መንደርና ጎራ ወሮ ሊያወድም እንደተነሳ፣ ለምን የአፋርና የአማራን ህዝብ ሊጨርስ እንዳቀደ፣ ምን እንደሚፈልግ በግልጽ አስታውቋል። ሲኦል ግብቶም ቢሆን ኢትዮጵያን እንደሚያፈርስ በገሃድ ተናግሯል። ይህን ሲያደርግ ዓለም ” በርታ፣ አይዞህ፣ ጨፍጭፍ … የመንግስት እጁን እናዝልልሃለን፣ በችግር እንቀስፈዋለን” እየተባለ ነው። ችጋሩን መሳሪያ አድርጎ ስቃይ እያሳየን ነው።

ይህ በችጋር መነገድ ባህሉ የሆነ፣ ከችጋር ጋር የተቆራኘ፣ ችጋርን ልዩ ምክቱ አድርጎ የተነሳ፣ ካለችጋር መኖር የማይችል፣ ህዝቡን ብችጋር ቀስፎ ተስፋ ቢስ ያደረገ፣ በሌሎች መበልጸግ የሚቃጠል፣ ደግነት የነጠፈበት፣ ሴራና ክፋት የሞላው፣ ክህደትና ማጭበርበር ባህሉ የሆነ ቡድን የከፈተው ጦርነት የማይመለከተው ኢትዮጵያዊ የለም። ከእያንዳንዱ ሕዝብ አብራክ የወጣውን መከላከያ ያረደ፣ ሴቶቹን ጡታቸውን የቆረጠ፣ ሃያ ሁለት ዓመት ሲጠብቁት እንዳልነበር ዋጋቸው ቢላ ሆኖ፣ አስከሬናቸውን እራቁት አድርጎ ለጅብ ያስበላ አረመኔ ቡድን፣ በዚህ ተግባሩ ከበሮ እየመታ ሲጨፍር አዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ ተበትነው እስክስታ ሲወርዱ የነበሩትን ህዝብ ያውቃቸዋል። ህዝብ አይቶ ዝም ቢልም ወረራው በዚህ ከቀጠለ ይህ ዝም ያለ ሃይል ራሱን የሰው ማዕበል እንደማያደርግ ጥርጥር የለም።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ከስልጣን የተወገደው በሕዝብ አመጽ ነው። ሕዝብ በቃኝ ብሎ ነው የገለበጠው። ገሎ፣ ፈጅቶ፣ አስሮ፣ ቶርቸር አድርጎ፣ እስር ቤቶች ሁሉ ቋቋቸው ኦሮሚኛ እንዲሆን አድርጎ ስላልቻለ የሕዝብ ዓመጽ በላው። እንግዲህ ሶማሌ ክልል ግብቶ አቶ ሙስጣፌን አውርዶ ሊነግስ ነው? ኦሮሚያ ገብቶ ሽመልስ ወንበር ላይ ተቀምጦ ሲያኮላሸው የነበረውን ሕዝብ ሊመራ ነው? አማራ ክልል የበላይ ሊሆን ነው? ሲዳማ ” ለምን ክልል እሆናለሁ አልክ” እያለ ሲቀጠቅጥ እንዳልነበር አሁን ሲዳም ወነበር ላይ ፊጥ ሊል ነው? የጋምቤላን ምስኪን ሕዝብ መሬታቸውን እየነጠቀ ሲያስለቅስና ሲገድል እንዳልነበር ዳግም ሄዶ የተረፈውን መሬት ሊቸበችብ ነው? አፋር ገብቶ ጨው ሊነግድ? “ሲያልቅ አያምር ” የሚባለው ይህኔ ነው።

አዲስ አበባ ወይም ሌሎች ከተሞች ያሉ ወገኖች ዘመዶቻቸው በየክፍለሃገሩና የገጠር ከተሞች ነዋሪ ናቸው። እነሱን በየክፍለሃገሩ እያረዱ፣ እየዘረፉ፣ እየደፈሩ፣ እየፈናቀሉ አዲስ አበባ ለመግባት ማሰብ ትርፉ ኪሳራ ነው። ጭራሽ ሊሆን የማይችል ስሌት ነው። በዚህ የእውር ጉዞ ስኬታማ ለመሆን ማሰብ እብደት ነው። ይህ ቡድናዊ እብደት የማይመለከተው ቢኖር ከእነሱ ጎን ያልተሰለፉትን ብቻ ናቸው። በነገራችን ላይ አለመቃወምም ድጋፍ እንደሆነ ህዝብ እያወራ ነው። ወሬው ውስጥ ውስጡን ሳይሆን በገሃድ ሆኗል። አዲስ አበባ ውስኪውን እየጨለጠ “ደሴ ልትያዝ ነው፣ ትህነግ ዳግም አዲስ አበባ ሊገባ ነው” እያለ የሚያሟሙቀውን ሕዝብ … ብቻ ሳስበው ሳስበው ደግሜ ሳስበው “አላማረኝም”።

መንግስት “የሕዝብ ማዕበል ጦርነት በመሆኑ ሕዝባዊ ማዕበል መፍጠር ግድ ነው” በሚል የደቡብና ሰሜን ወሎ፣ እንዲሁም የአፋር ሕዝብ ክተት ብሏል። በየማሳህ፣ በየቀዬህ፣ በየሰፈርህ፣ በየጓሮህ የሚርመጠመጠውን እርምጃ ውሰድበት ተብሏል። ታጠቅ፣ ተደራጅ፣ ሲል መንግስትም ጥሪ አቅርቧል። አዲስ አበባና ሰፋፊ ከተሞች ቁጭ ብለው ለወራሪው የሚሰሩትን ተከታተሉ ብሏል።

በአማራና በአፋር የሚገኝ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሕዝባዊ ማዕበል ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳውን ሃይል ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን መክት ተብሏል። ይህን ጥሪ ተከትሎ ወሎዬ ወደ ግንባር እየተመመ ነው። የሚያሳዝን ቢሆንም የህዝብ ማእበል ከዚህ ወገንም እንደ መብረቅ እየተተኮሰ፣ እንደ ንብ ሊናደፍ እየተመመ ነው። የአሁኑ አያያዝ ነገሩ ቀበሌና ሰፈር የሚቆም አይመስልም። ያስፈራል።

” ኢትዮጵያ ለትግራይ ስጋት እንደማትሆን እስኪረጋገጥ እናጠቃለን” ሲል ጌታቸው ረዳ ደጋግሞ አስታውቋል። ” አጆሃ ጀጋኑ” እየተባለ በሙቀት ” ሲኦልም ወርደን ቢሆን ኤትዮጵያን እንበትናታለን” ብሏል። ደብረጽዮን በበኩል ” እንደ አባቻቸው ጨፍጭፈን …” ሲል በግልጽ ህዝብ ለመጨረስ መነሳታቸውን አመልክቷል። ስለዚህ ” ትህነግ ለኢትዮጵያ ስጋት እንዳይሆን ተደርጎ ካልተመታ” በሚል ሌሎች ቢነሱ ፍትህ ማዛባት አይሆንም። “መቱኝ” እያሉ ማለቃቀስም ትርጉም አይኖረውም።

“ጉልበት ያላቸው በሙሉ በማዕበል የተነሳውን አጥፊ የትህነግ ወራሪ ሃይል ደምስስ” ሲል በወሎ ዙሪያ ያሉ አስተዳዳሪዎች ያቀረቡትን ጥሪ ተቀብሎ ሕዝብ እየተመመ ነው። ልክ በጋይንት፣ በደብረ ታቦር፣ እንደሆነው በወሎ ግንባር የማይሆንበት ምክንያት የለም። ከሆነም ” ሲያልቅ አያምር” እንዲሉ መሆኑ አይቀርም።

ዓላማቸው ደሴና ኮምቦልቻ ገብተው መዝረፍና አውድሞ ባዶ ማድረግ እንደሆነ ታውቋል። ይህ የተረዳውና መፈናቀል የታከተው ሕዝብ ተነቃንቋል። መንዜው እየተዘጋጀ ነው። ደራው ተደራጅቷል። ሸዋ ሮቢት ማማው ላይ ነው። አሁን በየአቅጣጫው ሕዝብ እየተዘጋጀ ነው። ሕዝብ ስላንገፈገፈው እየተቆጣ ነው። የኢትዮጵያን መከላከያ ዳግም ለማፍረስ፣ አየር ሃይሉንና እንደ አዲስ የተዋቀረውን አየር ወለድ ለመበተን ” የአብይ ሰራዊት” የሚለው ባንዳ ንጹሃንን ከዛም ከዚህም ወገን እያስበላ ነው። በተተነፈሰ ቁጥር የትግራይ ሕዝብ ላይ እያላከከ ሕዝቡን ወዳጅ አልባ አድርጎ የሞት አቡሸማኔ እየሰገረና እያሰገረ ነው።

ርስትህን፣ ግቢህን፣ ሃብትህን፣ ንብረትህን ጠብቅ። ጦርነቱ የተከፈተው በሁሉም ግንባር ነው። ዓለም ዓቀፍ ጫናው አለ። በሚል በተላለፈው ጥሪ መሰረት ክተቱ አይቀሬ ሆኖ ከዚህም ማእበሉ እየጎረፈ ነው። ይህ ሁሉ ሲሆን ድንጋጤ የለም። ሃያ ሰባት ዓመት የተዘረፈውና የተሰበሰበው አልበቃ ብሎ ለዳግም ዝርፊያ …

የ16ኛው ክፍለዘመን የህዝብ ማዕበል ( የሰውን ልጅ በጅምላ የመማገድ) ጦርነት አንድ ወገን ስለጠላው ብቻ አይቀርም። ሴጣንን በምሱ ነውና ለመጪው ትውልድ፣ ለልጆቻቸን ማረፊያና መኖሪያ ለማበጀት ወደፊት እንጂ ወደሁዋላ የለም የሚሉ የምሬት ድምጽ እያሰሙ ነውና እባካችሁን ከቅዠት ንቁ። ክልላችሁን አስተዳድሩ። የድንበርና የማንነት ጥያቄ ካላችሁ በአገርና ዓለም ዓቀፍ ህግ እንዲዳኝ አድርጉ። ሕዝብ አታስጨርሱ። የስካሁን ይበቃችኋልና ቂምን አትቆልሉ። የናቡከደነጾር ዘመን በደጅ ናት። ለድሆች አስቡ። ለሕዝብ አስቡ። ችጋርን መጠቀሚያ አድርጋችሁ …. ይብቃችሁ። ያስፈራል። እኔ ፈርቻለሁ። ይብላኝ ለተላላኪውም !!

ስዩም ሃይለማሪያም ከሸዋ ሮቢት

ጽሁፉ የዝግጅት ክፍሉን አቋም አያንጸባርቅም። የጸሃፊው አመለካከት ብቻ ነው!!

Exit mobile version