ETHIO12.COM

” ፈርሷል” የተባለው የአገር መከላከያ በሁሉም ግንባሮች እያጠቃ ይዞታውን እያሰፋ ነው

የአገር መከላከያ አስቀድሞ ባስገባቸው ሰርጎ ገቦችና ሲቪል በለበሱና ከተማ ውስጥ ነበሩ በተባሉ “ባንዳዎች” አማካይነት ጥቃት ለማድረስ የሚከሩትን ሃይሎች በከፍተኛ ተጋድሎ መክቶ ወደ ማጥቃት መዛወሩ ተገለጸ። በጋሽና፣ ጭፍራና መሰል ግንባሮች የአገር መከላከያ ሰራዊት የማጥቃት አድማሱን ማስፋቱ ተመለከተ። አቶ ጌታቸው በትላንትናው ዕለት ማርፈጃው ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ባሰራጩት ቲውተር ” የአገር መከላከያ ተብዬው ተበትኗል” ሲሉ ሁሉም ነገር ማብቃቱን አስታውቀው ነበር።

የአገር መከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች አሸባሪውን ወራሪ የትህነግ ሃይል በመደምሰስ ላይ ነው

አቶ ጌታቸውን ተከትለው ልክ እንደ 1983 የደርግ ሰራዊት በሚል እየጠሩ እንዳፈረሱት ሃይል ትናንት ወዲያውኑ ” መከላከያ ተበትኗል። አለቆች ሸሽተዋል። ጀነራሎች ተማርከዋል። ሰራዊቱ እጅ ሰጥቷል” በሚሉ ማጀቢያዎች ደሴ ሙሉ በሙሉ በትህነግ ሰራዊት ቁጥጥር ስር እንደዋለች ደጋፊዎችና የሚታወቁ ሚዲያዎች ሲዘግቡ ነበር። አዲስ አበባ የተቀመጡ የውጭ ሚዲያዎችም በተመሳሳይ ይህንኑ ዜና አቶ ጌታቸው ረዳን በመጥቀስ ” ታሪካዊዋ የደሴ ከተማ በትህነግ እጅ ወደቀች” በሚል ዘግበዋል። አቶ ጌታቸው “ትግራይ ታሸንፋለች” በሚለው ማሰረጊያቸው ” ተብዬው” ያሉት መከላከያ ሲያበቃለት ተጨማሪ ጥሪ መቀረቡን በመጠቆም የሚሆነው ይታያል ዓይነት ሃሳብ አስፍረው ነበር። ይህ ሲጻፍ አቶ ጌታቸው 15 ሰዓታት ተቸማሪ መረጃ ስለ ደሴም ሆነ ” ፈረሰ ስላሉት የኢትዮጵያ መከላከያ” ተጨማሪ ያሉት ነገር የለም።

ባለፈው ሳምንት የትህነግ አመራሮች ተሰባስበው በሁለት ሃሳ ከተወያዩ በሁዋላ “ባለ በሌለ ሃይላችን የሞተው ሞቶ ደሴን ለመቆጣጠር ደርምሠን እንግባ” በሚል ከተስማሙ በሁዋላ በደሴን ግንባር ሰርጎ ገብ አስገብተው የሚከሩት ጥቃት በልዩ ኮማንዶ፣ በልዩ ሃይል፣ በመከላከያና በፋኖ ጥምረት በመከቱ ወዲያው ተዘግቦ ነበር። ይህን ያሉ ወገኖች ግን ጦርነቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀውም ነበር።

ይህ ክንድያ ያሰራጩት አንዱ ማሳያ ነው ትብሏል። የራሳቸው ሰዎች “አንሳው” ብለዋቸዋል

“መከላከያ ሠራዊቱ በሁሉም ግንባሮች የአሸባሪውን ወራሪ ሃይል እየደመሰሰ ነው” ሲል ያስታወቀው የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት “የአገር መከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች አሸባሪውን ወራሪ የህወሃት ሃይል በመደምሰስ ላይ ይገኛል” ብሏል። ሮይተርስን ጨምሮ በርካታ የውጭ አገር መገናኛዎች፣ መረጃ ቲቪና ሌሎች ሚዲያዎች ይህንኑ ዘገባ ሲያስተጋቡ፣ የመንግግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት “ደሴ በመንግስት ቁጥጥር ስር ነች” ሲል ቢያስታውቅም የዜናቸው አካል ሊያደርጉት አልፈለጉም ነበር።

ዛሬ ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በሰጡት መግለጫ እንዳረጋገጡት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያን የማዳን ተልዕኮውን በጀግንነትና በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

“ትናንት በደሴ ግንባር አሸባሪው ቡድን ቀድሞ ባስገባቸው ሰርጎ ገቦችና ሲቪል ለብሰው ከተማዋ ውስጥ በነበሩ ባንዳዎች አማካኝነት ሠራዊቱ ላይ ጥቃት ለመፈጸም መሞከሩን ገልፀዋል።የመከላከያ ሠራዊቱ የተከፈተበትን ጥቃት በከፍተኛ ተጋድሎ መክቶ የማጥቃት ዘመቻ ላይ ይገኛል” ሲሉም አብራርተዋል። ” ባንዶች” ያሉዋቸውን ግን በዝርዝር አላስታወቁም።

እሳቸው ባይገልጹትም ከፍተኛ የማስተባበር ስራ በመስራት ላይ የሚገኙት የአብን አመራሮች፣ እንዲሁም ከፍተኛ የጦር መሪዎች ያረፉበት ሆቴል በከባድ መሳሪያ መመታቱ ታውቋል። ይህም ከተማ ውስጥ ሆኖ የሚያስተኩስ ሃይል እንዳለ ማረጋገጫ መሆኑ በተደጋጋሚ ከስፍራው ሲዘገብና የአብን አመራር ኢብራሂም በገሃድ በማህበራዊ ገጻቸው ያሰፈሩት ነው።

ሠራዊቱ ትናንት በደሴ ግንባር ታላቅ ተጋድሎ መፈጸሙንና ሕዝቡም ደጀንነቱን በተግባር ማስመስከሩን ያስታወቁት ዶክተር ለገሰ ቱሉ፣ የመከላከያ ሠራዊቱ በጭፍራ፣ በጋሸና እና በሌሎች ግንባሮች እያደረገ በሚገኘው ተጋድሎ ይዞታውን በማስፋት ላይ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።

“ሰላማዊ መስለው ደሴ ከተማ ከተፈናቃዮች ጋር ተመሳስለው የገቡ ሰርጎ ገቦች ደሴ ከተማን በወያኔ እንደተያዘች ለማስመሰል ብዙ ስራ ሰርተዋል ሆኖም በከተማ ውጊያ በሚገባ በሰለጠኑ በሪፕሊካን ጋርዶች ቤትለቤት አሰሳ ከተማዋ ፀድታለች።” ሲል የአብን አመራር አቶ የሱፍ ኢብራኢም ምስክርነታቸውን ከቦታው ሰጥተዋል።

በሬዲዮ የትህነግ ሃይሎች ያደረጉት ምልልስ ተጠልፎ ይፋ የተደረገ ሲሆን በዚህ የድምጽ ምልልስ ” እየተጎዳን ነው አልቻልንም። ወደፊት መሄድ ከብዶናል” የሚል ይዘት ያለው መልዕክት ከግንባር ሲላክ መቀለ ያለው ሃይል ” እንደምንም ብለህ ግባ” የሚል መመሪያ ሲሰጥ የሚሰማበት ነው።

በዚህ መካከል በተሰማ ዜና ” ተበተነ፣ ፈረሰ፣ ተብዬው፣ የአብይ ሰራዊት …” የሚባለው የአገር መከላከያ ከአማራ ክልል ሰፊ ድጋፍ እየተላከለት መሆኑ፣ ሰቆጣና ዋግ አካባቢን ዘልቆ መቆጣጠሩ እንዲሁም በጭፍራ በኩል እየገፋ መሆኑንን የቅርብ ምስክሮች እያስታወቁ ነው። ምን አልባትም በቀናት ውስጥ የጦር ሜዳ ዜናው ሊቀየር እንደሚችል እየተናገሩ ነው።

ይህ በአንዲህ እንዳለ አሜሪካ የትህነግ ሃይል ከገባበት የአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ ጠይቃለች። አሜሪካ ደሴን የመቆጣጠሩ ሙከራ ከከሸፈ በሁዋላ ነው በይፋ ጥሪ ያቀረበችው። አሜሪኪአ ሰፊ የጎንደር ክልል በተወረበትና ሰፊ ማህበራዊ ቀውስ ሲፈጸም ምንም አላለችም ነበር።

ትህነግ ደሴን የመያዙ ዘመቻና እቅዱ ሲከሽፍ አቤቱታ ማሰማት እንደጀመረ በመህበራዊ ገጽ የሚያተላልፋቸው መረጃዎች ምስክር ናቸው።

በተመሳሳይ አየር ሃይል የጦርነት ዜና በመቀሌ አቅራቢያ የሚገኘው የአሸባሪው ህወሃት አጉላእ ታጣቂ ማሠልጠኛ ተቋም ዛሬ በአየር ሃይል መመታቱን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።ተቋሙ በርካታ የቡድኑ አባላት ለሽብር ተልእኮ ተመልምለው የሚሠለጥኑበት እንደሆነም ተገልጿል። አቶ ጌታቸው ይህን አስመልክቶ ይህ እስከታተመ ያሉት ነገር የለም።


Exit mobile version