Site icon ETHIO12.COM

ምንም ይሁን ምን ኢትዮጵያ በክህደት የታረዱ ልጆቿን አስባለች – አይረሳም!

የዛሬ ዓመት በትዕቢት ” አመድ አደረግናቸው” ሲሉ የተዛበቱ የሉም። ልክ የዛሬ ዓመት የአገር ክብር መሶሶ የሆነው መከላከያ ሰራዊታችን ለሁለት አስርት ዓመታት ከተኛበት ምሽግ ውስጥ እንዲታረድ ካዘዙት ውስጥ ይበልጦቹ አፈር ሆነዋል። የተቀሩትም ” የሞተው ሞቶ” በሚል የህዝብ ማዕበል አጉርፈው መንግስት እንደፈረሰ፣ አገር እንዳበቃላት እያወጁ ባለበት ወቅት ኢትዮጵያ ልጆቿን ” ነብስ ይማር ስትል” አክብራ አስባቸዋለች። አገር በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም ኢትዮጵያ ልጆቿን አልረሳችም። አትረሳም። ልትረሳም አይቻላትም። እስከወዲያኛው ይህ ታሪክ ይኖራል።

ክህደትና ውንብድና የተጣባው የትህነግ ሃይል የአገር መከላከያን በአርባ አምስት ሰዓት ከጥቅም ውጭ አድርጎ መሳሪያውን በሙሉ መረከቡን የተናገረበትና ይህንን የክህደት ጭፍጨፋ ሰብረው የወጡ አናብስቶች በአስራ አምስት ቀን እሳት እየተፉ የፈጸሙት ገድል በክህደት ከተፈጸመባቸው ግፍ ይበልጥ የሚያበራ ነውና ኢትዮጵያ አታዝንም። ግን በክብር ትዘክራቸዋለች። ሕዝብ ሁሉም ዜጋ ” አንረሳም” ብሏል። አይረሳም።

የክህደት ጭፍጨፋው ብቻ ሳይሆን፣ እድሜውን ሙሉ ሲጥበቃቸው ሲያገለግላቸውና እንደ ቤተሰብ ሲታዘዛቸው የነበረው መከላከያ ሲጨፈጨፍ የጨፈሩና እስክስታ የወረዱ ሁሉ ቀሪው ትውልድ ያስባቸዋል።መጪው ትውልድም ታሪካቸውን ሲማርበት ይኖራል።

ዛሬ ኢትዮጵያ በከሃጂዎች የዥዋዥዌ ጨዋታ ስቃይ ውስጥ ብትሆንም ቅን ፈራጅ አምላክ ብይን እንደሚሰጣት፣ የንጹሃን ደምና ነፍስ አምላክ ደጅ ጩኸት እንደሚሰማ፣ ሲሰማም እንደ መብረቅ የሚሆን ዋጋ እንደሚያስከፍል፣ ፍርዱ ሲደርስ እንጂ ለጊዜው ለተዘጋ ልብና አዕምሮ የአምላክ ፍርድ ልክን እንደ ተረት እንደሚመስል የታወቀ ነው።

መላው ኢትዮጵያ ሳያታሰር፣ ሳይገፋ፣ ሳይነዳ፣ ማስፈራሪያ ሳይደርስበት አምርሮ ወደ ግንባር እየተመመ ያለበትና ቁርጠኛነቱን ያሳየበት ቀን መሆኑም ” አንረሳችሁም ጀግኖቻችን” በሚል የተሰየወምውን የክህደት ቀን ልዩ ያደርገዋል። ኢትዮጵያን ለማፍረስ ብዙ ርቀት የተጓዙ ከሃጂዎች ይቅናቹህ!! አገር በማፍረስ ምን እንደምትጠቀሙ ወደፊት ልጅ ልጆቻቹህ ያስረዱናል። እናንተ ለማስረዳት ካልደረሰችሁ!! ሁሉንም እድሜ የሰጠው ያየዋል።

ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?
ያለፈውን ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ሥነ መንግሥት ታሪክ በጥሞና የተከታተለ …
የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
 አንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ …
የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
የስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት …
ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?
የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች …
Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
The Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to …
የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን …
Exit mobile version