Site icon ETHIO12.COM

“የአሸባሪውን ህወሓት ሴራ የሚያጋልጥ ምስጢራዊ መረጃ አፈትሎኮ ወጣ”

የአሸባሪው ህወሓት ከፍተኛ አመራር የሆነው ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት የተፈጸመበትን አንደኛ አመት በማስመልከት በውጭ ሀገር ከሚኖሩ የቡድኑ አባላትና ደጋፊዎች ጋር በቪድዮ ኮንፈረንስ ያደረገው ሚስጢራዊ ውይይት በተመለከተ ከታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ደርሶናል፡፡

አሸባሪ ቡድኑ የውጭ ሃይሎችን እገዛ በመጠቀም በዘረጋው የግንኙነት መስመር ከአባላቱና ከደጋፊዎቹ ጋር ያደረገውን ውይይት የመራው ደብረጽዮን ህወሓት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመክፈት ግጭቱን መቀስቀሱን በቅርቡ የቡድኑ አመራር ጻድቃን ገብረትንሳይ እንዲሁም ጌታቸው ሴኮቱሬ አስረግጠው የሰጡትን ምስክርነት በመካድ በዕለቱ በትግራይ ክልል ላይ ጦርነት ታወጇል ብሏል፡፡

ህወሓት በአሁኑ ወቅት ከሸኔና ከሌሎች ሃይሎች ጋር ግንባር ፈጥረናል ያለው ደብረጽዮን፤ የቡድኑ የመጀመሪያ ተልዕኮ ስርዓቱን አስወግዶ ትግራይ የራሷን እድል በራሷ እንድትወስን ማድረግ እንጂ በቀጣይ በኢትዮጵያ ስለሚኖረው ስርዓት እንደማያሳስበው ለአባላትና ለደጋፊዎች አሳውቋል፡፡ ኢትዮጵያ የመረጠችውን ልትሆን ትችላለች ዋናው የኛ ተኩረት የራሳችን ጉዳይ ላይ ይሆናል ያለው ደብረጺዮን የሚመሰረተው የሽግግር መንግስትም የትግራይን ጥቅም በሚያስጠብቅ መንገድ እንዲመራ ይደረጋል በማለት ተናግሯል፡፡

ህወሓት አዲስ አበባን ሲቆጣጠር በሁሉም አካባቢ የተወሰዱ ንብረቶችን እንደሚያስመልስ፤ ለደረሰው ኪሳራ ካሳ እንደሚያስከፍልና የትግራይን ህዝብ ተጠቃሚነት እንደሚያስጠብቅ ለአባላቱና ለደጋፊዎቹ አረጋግጧል፡፡
አባላቱና ደጋፊዎቹ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም የትግራይን ጉዳይ እስከ ጸጥታው ምክር ቤት በማድረስ አለም አቀፍ አጀንዳና መወያያ እንዲሆን በማድረጋቸው ምስጋናውን የገለጸው ደብረጽዮን አሁንም ከልጅ እስከ አዋቂ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣትና የገንዘብ እገዛ በማድረግ ድጋፉን እንዲያጠናክር አሳስቧል፡፡
አሸባሪው ህወሓት ላይ በሁሉም ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች በአፋርና አማራ ክልል በሰራዊቱ፣ በልዩ ኃይሎች፣ በፋኖና ሚሊሻ እርምጃ እየተወሰደበት እንደሚገኝ ምንጮቻችን ጨምረው ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያለንበት ጦርነት መሰረታዊው ጦርነት ጥይቱ ሳይሆን የሀሰት ወሬው ነው ማለታቸው ይታወሳል።

ENA

Exit mobile version