Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ውጭ አማራጭ ገበያ እየፈለገች ነው

አሜሪካ የኢንዱስትሪ ምርቶች ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገሯ ገበያ እንዲገባ ይፈቀድ የነበረው ስምምነት (AGOA) እንዲቋረጠ በፕሬዜዳንቷ ጆ ባይደን አማካኝነት ውሳኔ ማሳለፏ ይታወሳል። ይህ የአሜሪካ ውሳኔ በርካቶችን ከስራ ውጭ የሚያደርግ ውሳኔ መሆኑ በተደጋጋሚ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በAGOA ምክንያት ይገኝ የነበረው የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት አማራጭ ገበያ እየፈለገች መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ፥ ” የገበያ መዳረሻዎቻችን በሪፎርም ስራዎች ውስጥ አንዱ ዋና ስራ ተደርጎ ከተወሰዱት የገበያ መዳረሻዎች ማስፋት ነው። ከዚህ አኳያ AGOA በተሰጠን እድል መሰረት አሜሪካ ያለንን የገበያ እድል ሌላ ጋር መፈለግ ማለት ነው። ሌሎች ሀገራት በዚህ አይነት ሁኔታ የተጠቀሙ ብዙ አሉ። ጫናና ማዕቀብ ሲጣልባቸው ከሌሎች ሀገራት ጋር ተደራድረው ያንን ምርቶቻቸውን ሌሎች ሀገራት የተቀበሏቸው አሉ። ኢትዮጵያም ያንን እያሰበችበት ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ አክለው ፤ በኮቪድ-19 ጊዜ የአለም ገበያ ሲዘጋ ለኤክስፖርት ተብለው የተመረቱ እቃዎች በሀገር ውስጥ መሸጥ እንዲችሉ እድሉን መንግስት አመቻችቶ ነበር ይሄም አንዱ መታየት ያለበት መሆኑን አንስተዋል።

ዶክተር ፍፁም አሰፋ ፥ ጦርነቱ ኢትዮጵያ ልማት ላይ ልታውል ያቀደችውን ገንዘብ ለጦርነት እንዲውል ስለሚደረግ ኢኮኖሚያዊ ጉዳቱ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ዜጎች ኢኮኖሚውን ለመደገፍ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ግኝት ለማሳደግ በህጋዊ መንገድ ገንዘብ እንዲልኩ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia

ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
 ቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ …
የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ …
ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት
ዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ …
የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡም
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራንስፖርት ስምሪትና የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር ሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ …
መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ
የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ ምክንያቱም “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ …
“ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረው
የሚነሳው ጉዳዩ ልብ ሰባሪ ነው፣ ያስቃል፣ ያዝናናል፣ ያስገርማል፣ ያሳዝናል፣ ይቀፋል፣ ያሳፍራል፣ ለማመን …
Exit mobile version