ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ውጭ አማራጭ ገበያ እየፈለገች ነው

አሜሪካ የኢንዱስትሪ ምርቶች ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገሯ ገበያ እንዲገባ ይፈቀድ የነበረው ስምምነት (AGOA) እንዲቋረጠ በፕሬዜዳንቷ ጆ ባይደን አማካኝነት ውሳኔ ማሳለፏ ይታወሳል። ይህ የአሜሪካ ውሳኔ በርካቶችን ከስራ ውጭ የሚያደርግ ውሳኔ መሆኑ በተደጋጋሚ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በAGOA ምክንያት ይገኝ የነበረው የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት አማራጭ ገበያ እየፈለገች መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ፥ ” የገበያ መዳረሻዎቻችን በሪፎርም ስራዎች ውስጥ አንዱ ዋና ስራ ተደርጎ ከተወሰዱት የገበያ መዳረሻዎች ማስፋት ነው። ከዚህ አኳያ AGOA በተሰጠን እድል መሰረት አሜሪካ ያለንን የገበያ እድል ሌላ ጋር መፈለግ ማለት ነው። ሌሎች ሀገራት በዚህ አይነት ሁኔታ የተጠቀሙ ብዙ አሉ። ጫናና ማዕቀብ ሲጣልባቸው ከሌሎች ሀገራት ጋር ተደራድረው ያንን ምርቶቻቸውን ሌሎች ሀገራት የተቀበሏቸው አሉ። ኢትዮጵያም ያንን እያሰበችበት ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ አክለው ፤ በኮቪድ-19 ጊዜ የአለም ገበያ ሲዘጋ ለኤክስፖርት ተብለው የተመረቱ እቃዎች በሀገር ውስጥ መሸጥ እንዲችሉ እድሉን መንግስት አመቻችቶ ነበር ይሄም አንዱ መታየት ያለበት መሆኑን አንስተዋል።

ዶክተር ፍፁም አሰፋ ፥ ጦርነቱ ኢትዮጵያ ልማት ላይ ልታውል ያቀደችውን ገንዘብ ለጦርነት እንዲውል ስለሚደረግ ኢኮኖሚያዊ ጉዳቱ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ዜጎች ኢኮኖሚውን ለመደገፍ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ግኝት ለማሳደግ በህጋዊ መንገድ ገንዘብ እንዲልኩ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia

ተጨማሪ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሊደረግ ነው
የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ክፍተት በማጥበብ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ የሚያስችል ተጨማሪ …
ከአርሰናልና ከሲቲ የተሻለ ዕድል ለማን? አሃዛዊ መረጃዎች ወዴት ያደላሉ
ከሚታወቅበት ጥለዛ በየጊዜው መሻሻል እያሳየ ውብ ኳስ ባምስኮምኮም ላይ ያለው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር …
የበዓሉ ግርማ ኦሮማይ – ዛሬ ለምን?
ትህነግ የሚመራው ኢህአዴግ በውስጡ በተፈጥሩ ሃይሎችና በህዝብ ተቃውሞ ተደጋጋፊነት ከስልጣን ሲወርድ በቅጽበት …
የበታችነትና የበላይነት ስቃይ “እኩል የኢትዮጵያ ስጋት ናቸው”መባሉ ጫጫታ አስነሳ?
ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በግልጽ አላፊነት የማይወሰድበትና ባለቤቱ ግልጽ ወጥቶ የማይመራው መተራመስ ህዝብን …
ሩሲያ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቿን ቤላሩስ ውስጥ ልታጠምድ ነው
ሩሲያ ስልታዊ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቿን በአጋሯ እና በጎረቤቷ ቤላሩስ ውስጥ በማንኛው ጊዜ …
ኦሮሚያ በአራት ወር መቶ ሺህ ዘመናዊ የገጠር መኖሪያ ቤቶች ሊገነባ ነው
በቀጣዮቹ አራት ወራት በኦሮሚያ ክልል 100 ሺህ ዘመናዊ የገጠር መኖሪያ ቤቶች ግንባታ …

Leave a Reply