Site icon ETHIO12.COM

ጄፍሪ ፊልትማን እየዋሸን ነው!(ኢንጅነር ጌታሁን ሄራሞ)

በአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆነው አምባሳደር ጄፊሪ ፊልትማን ኖቬምበር 1, 2021፣ የአሜሪካ የሰላም ተቋም ባዘጋጀው መድረክ ላይ በአሁኑ ወቅት በአሜሪካና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው ግንኙነት ሰፋ ያለ ማብራሪያ መስጠቱ ይታወሳል። ገለልተኛና ነፃ ተቋም ስለመሆኑ የሚምለው ይህ ተቋም በአሜሪካ ኮንግሬስ አማካይነት የተመሠረተው እ. ኤ. አ. በ1984 ዓ.ም. ነበር።

ታዲያ በዚህ ማብራሪያው ላይ ፊልትማን በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት “Civil War” ስለመሆኑ አስረግጦ ከመግለፁም በላይ ጦርነቱ እልባት ካልተገኘለት ለ20 ዓመታት ያህል ሊዘልቅ እንደሚችል ጥናቶች ያረጋግጣሉ በማለት ለማስረዳት መሞከሩ ይታወሳል።

“Studies show the average modern civil war now lasts 20 years. I repeat: 20 years. A multi-decade civil war in Ethiopia would be disastrous for its future and its people.”

ጥያቄው በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት “Civil War” ነው ወይ? የሚል ነው። በአጭር ቃል ጦርነቱ “Civil War” አይደለም።

የ20ኛውን ክ/ዘመን መገባደጃንና የቀዝቃዛውን ጦርነት ማክተም ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተካሄዱ ያሉ አብዛኞቹ ጦርነቶች ሲቪል ጦርነቶች ሊባሉ እንደማይችሉ ብዙ ጥናቶች ያረጋግጣሉ። ለዚህም በ980ዎቹና በ1990ዎቹ ለየት ባለ መልኩ ያቆጠቆጠው ግሎባላይዜሽን እንደ አንድ ምክንያት ይቆጠራል። በዘመነ ግሎባላይዜሽን ውጭ/ውስጥ የሚለው ነባር ግድግዳ በእጅጉ ሳስቷል፤ በሀገራት መካከል ያለው ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ ፣ ወታደራዊና ባሕላዊ ትስስር በእጅጉ ናኝቷል። በአንድ ሀገር የሚከሰት የትኛውም ሁነት ሌላውን የመንካት ዕድሉ ከፍተኛ ሆኗል፤ ደሴታዊነት ታሪክ ሆኗል። ስለዚህም ይህን ተከትሎ ጦርነቶችም ቅርፃቸውና ይዘታቸው ተቀይሯል። ቀድሞ “Civil Wars” ይበሉ የነበሩ ጦርነቶች ወደ ታሪክነት ተቀይረው “Old Wars” የሚለውን ስያሜ ተጎናፅፈዋል።

እናም አምባሳደር ጄፍሪ ፊልትማን የኢትዮጵያን ጦርነት “Civil” ብሎ ሲጠቅሰው ይህን ሳያውቀው ቀርቶ አይመስለኝም። በእንደዚህ ዓይነት ጦርነቶች ዕድሜ መራዘም የአሜሪካ እጅ እንዳለበትም ተሰውሮበት አይደለም። ይልቁን ዓላማው ጦርነቱን የውስጥ ጦርነት ብቻ እንደሆነ በመጠቆም ላይ ያነጣጠረ ነው። ዓላማው…ጦርነቱ ውስጥ የኛ እጅ የለበትም፤ የናንተው ጣጣ ነው… የሚለውን መልዕክት ማስተላለፍ ነው።

እንግሊዛዊቷ ሜሪ ካልዶር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአፍሪካና በማዕከላዊ እስያ የሚደረጉትን ጦርነቶችን ቅርፅና ይዘት በተመለከተ በምታደርጋቸው ጥናቶቿ ትታወቃለች። ጄፊሪ ፊልትማን “Civil War” የሚለውን ስያሜ ለሰጠው ለኢትዮጵያ ጦርነት ሜሪ ካልዶር “New War” የሚለውን ነው የምትመርጠው። የብሪስቶል ዩኒቨርስቲው ፕሮፈሰር ማርክ ደውፊልድ ደግሞ “Postmodern Wars” የሚለውን ስያሜ ይጠቀማል። እንግሊዛዊው ዴቪድ ክን ደግሞ Informal War” ይለዋል። አሜሪካዊው ፕሮፈሰር ክሪስ ሄብል ግሬይ ” Virtual Wars and Wars in cyberspace” የሚለውን ስያሜ ሲመርጥ፣ ፍራንክ ሆፍማን ደግሞ “Hybrid Wars” በማለት ይጠራል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ራሺያና አሜሪካ ሶሪያ ውስጥ እያደረጉ ያለው ጦርነት የውክልና ጦርነት (Proxy War) ተብሎ እንደሚጠራ ብዙዎቻችን የምናውቀው እውነት ነው።

ከላይ የጠቀስኳቸው የዘመኑ የጦርነት ዓይነቶች ፊልትማን “Civil War” ብሎ ከጠራው ከበፊቶቹ ጦርነቶች የሚለዩበት አንዱና ዋናው ነጥብ ጣልቃ የሚገቡ የዓለም አቀፍ ተዋንያን መብዛታቸው ነው። እንደ አሜሪካ ካሉ ከምዕራባውያን ሀገራት በተጨማሪ በሌላ ሀገር ጦርነት ውስጥ በልዩ ልዩ ምክንያት (ለምሣሌ በሰብዓዊ ጣልቃ ገብነት) ጣልቃ የሚገቡ ዓለም አቀፍ ተዋንያን ዝርዝር ይህን ይመስላል፦

▶️ ዓለም አቀፍ ዘጋቢዎች

▶️ ቅጥር አልሞ ተኳሾች

▶️ ሚሊተሪ አማካሪዎች

▶️ ወዶ-ገብ ዲያስፖራዎች

▶️ እንደ “USAID, OXFAM, SAVE THE CHILDERRN, HUMAN RIGHTS WATCH, UNHCR, EU, UNICEF, AU, UN” ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት (NGO)

በእርግጥ ጦርነቱ ጅምር ላይ “Civil War” ሊመስል ይችላል….. https://bit.ly/30OtaLr

Exit mobile version