Site icon ETHIO12.COM

ታከለ ኡማ – ኢትዮጵያ ማዕድን እንዳታመርት ትህነግ በሚስጢር በህግና አዋጅ አስሯት ነበር፤ 35ሺህ የኦነግ ጦርን ማን በላው?

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ “ኢትዮጵያ በማዕድን ማምረት እድገት ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ አያስፈልጋትም” በሚል በአውጅና ህግ ተቀርቅሮባት እንደኖረች አስታወቁ። “የሽፍታ ስብስብ አገሪቱን ይመራ ነበር” ሲሉ ይህ ማነቂያ ህግና አዋጅ ለምን እንዲወጣ እንደተፈለገ አስረድተዋል። ሰላሳ አምስት ሺህ የኦነግ ጦርን ማን በላው ሲሉም ጥያቄና መልስ ሰጥተዋል።

“ቅድሚያ” አሉ ታከለ ኡማ፣ “ቅድሚያ አዋጅና ህጉ የሚታወቀው በስራ አስፈሳሚና በማእከላዊ ኮሚቴ ደረጃ ነበር” ይህን ካሉ በሁዋላ ኢትዮጵያ በከርሷ የያዘችውን ማዕድን እንዳታመርትና እንዳትጠቀም የተቀረቀረባት ማእድናቱ የሚገኙት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር “አዳጊ” በሚላቸው ክልሎችና የኦሮሚያና አማራ ቆላማ ስፍራዎች በመሆኑ ነው። ዛሬ ይህ አሳሪ አዋጅ ተሽሮና ተጥሎ የአገሪቱ እድገት በማእድን ዘርፍ እመርታ እንዲያሳይ በአስሩ ዓመት መሪ እቅድ ሰነድ ተካቶ በትኩረት እየተሰራበትና በአጭር ጊዜ ለውጥ ያስመዘገበ መሆኑ አመልተዋል።

ኢትዮጵያ በርካታ ማዕድን እንዳላት ዘርዝረው ያስታወቁት ታከለ ኡማ ይህን ያሉት በቀይ መስመር ” የኢኮኖሚ አርበኞች” በሚል ርዕስ ስር ከትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ጋር በመሆን በሰጡት ማብራሪያ ወቅት ነው።

“ኢትዮጵያን በህግ ሃብቷን እንዳትጠቀም ቀርቅረውባት እነሱ ግን ወርቅ የከበሩ ማዕድናት ያመርቱ ነበር” ያሉት ሚኒስትሩ፣ ቢኒሻንጉል፣ ኦሮሚያ ጉጂ ዞንን እንደምሳሌ በማንሳት ምርቱ ወደ ውጭ ተልኮ ሲሸጥ ግን መንግስትም ሆነ ብሄራዊ ባንክ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ አመልክተዋል። ኢትዮጵያ ላይ በህግ ቆልፈው ራሳቸው በግል የሚከብሩበትና የውጭ ምንዛሬ በሽፋን የሚሰበስቡበት አግባብ እንደነበር ገልጸው ” አያሳካም እንጂ ይህ ሲቀር ነው ዛሬ አገሪቱን ሊያፈራርሱ የተነሱት” ብለዋል።

ምሳሌ ሲያጣቅሱ ያነሱት አፍዴራን ነው። የአፍዴራ ሃይቅ ሙሉ በሙሉ ጨው መሆኑንን አመልክተው ” የአፋር ልጆች ወሃውን ወደ ሜዳ መልሰውት ሲደርቅ ድንጋዩን ለቅመው እነሱ የ’ትህነግ’ ሰዎች አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ ይሸጡታል” ሲሉ አካሄዱን አሳይተዋል። አክለውም በአካል ተገኝተው ይህን ሲያዩ ድርጊቱ በኦሮሞ ወጣቶች ላይ ሲፈጸም ያየሁት ስለነበር ህመሙን ለመረዳት ጊዜ አልወሰደባቸውም።

“እናም” አሉ ታከለ ኡማ ” እናም ይህን ምንም ቴክኖሎጂ የማይጠይቅ የጨው ምርት ስራ ነጥቀን ለአፋር ልጆች ሰጠናቸው” ሲሉ በቅጽበት የተወሰደውን እርምጃ አመልካተዋል። በዚህና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች እንደ ሌሎች ወገኖቹ የአፋር ሕዝብ ዳግም “ሽፍታ” ያሉትን ትህነግ ለመጋፈጥ ብዙ ምክንያቶች አሉት።

በንግግራቸው መካከል ” ወሮ በላ፣ ሽፍታና ዱርዬ” እያሉ የሚጠሩት ትህነግ ከሸኔ ጋር የገጠመውን ጋብቻም ዳሰዋል። በሽግግር መንግስት ምስረታው ዋዜማ 35ሺህ የኦሮሞ ልጆችን ካምፕ አስገብቶ ያስበላ ማን እንደሆነ ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ እንደሚያውቅ ካስታወሱ በሁዋላ ” አንድ ኦሮሞ ነኝ የሚል ሰው ወንድሞቹን ካምፕ ከቶ በክህደት ከጨረሰ ሃይል ጋር ማበሩ እንቆቅልሽ ነው። ቀድሞውንም አብረው እንደነበሩ ያሳያል” ብለዋል። በክብር አዲስ አበባ ከተቀበልናቸው መካከል አፈንግጠው ዛሬ ትህነግን የተሸከሙት የሸኔ ሰዎችን ” ተላላኪነት ሲጠናወት እንዲህ ነው። ክፉ አመል ” በሚል ርካሽ ተግባር እየፈጸሙ መሆኑንን አመልክተዋል።

“ደካማ ደካማን ተሸከም፣ ወሮ የሚበላ ወሮ ከሚበላ ጋር ተስማማ፣ እውር እውርን መራ” ሲሉ ህብረታቸው መጥፊያቸውን ከማጣደፍ የዘለለ ምንም እንደማይፈይድ ታከል ኡማ አስታውቀዋል። ” ዛሬ ኦነግ ከኔ ጋር ካቢኔ ሆኗል” ያሉት ታከለ ኡማ ” ይህ እውነት እያለ ዛሬ ኦሮሞ ነፍጥ ይዞ ጫካ የሚገባበት አንዳችም ምክንያት የለም” ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ በተግባር የታየው ወሮ በላ መንግስት የሰራቸውን የፖሊሲ ጭንገፋና ሐጸጾች በማስተካከል በዚህ ሶስት ዓመት ውስጥ እጅግ ሰፊ ስራ መሰራቱ አመልክተው በቅርቡ ጦርነቱ ተጠናቆ ወደ ሙሉ ልማት ስራ ትኩረት እንደሚደረግ ገልጸዋል። ታከለ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ለሚያውቅና አብሯቸው ለሰራ ቃላቸውን የሚተብቁ ናቸውና ግንባር መሄዳቸው ቢያኮራቸውም በሳቸው ላያ ካላቸው እመነት የተነሳ እንዳልገረማቸው ጠቁመዋል። ሆኖም ግን በትግሉ ላይ የፈጠረው መነቃቃትና ሃይል ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ዓለምን እንዳናጋው ታይቷል ብለዋል።

Exit mobile version