ETHIO12.COM

ዜና መገልበጥ – አዲሱ የማተራመሻ ስልት

“የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በሚሳተፉበትና ለአንድ ሳምንት በሚቆየው የአገራዊ ዘመቻ መረሃ ግብር ወቅት የሚስተጓጎለውን የትምህርት ሂደት ትምህርት ቤቶች በሚያወጡት የማካካሻ መርሃ ግብር አማካይነት እንዲካካስ ይደረጋል” ሲል ቢቢሲ ዜናውን ይቋጫል። ዜናው ሲጀመር ደግሞ ተመማሪዎች በጦርነት እንዲሳተፉ ጥሪ እንደቀልረበላቸው አታሞውን እዛው አዲስ አበባ ተቀምጦ ይደበድባል። ይህን ያዩ “ዜና መገልበጥ አዲሱ የማተራመሻ ስልት” ብለውታል።

ለአንድ ሳምንት የሚዘጉት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች፣ መምህራንና ሠራተኞች የሚያከናውኑት ተግባር ለአገር የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በመሆኑ ሁሉም አገራዊ ግዴታቸውን በመወጣት በአገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

“ቢቢሲ ትምህርት የተዘጋው ተማሪዎችን በጦርነቱን ለማሳተፍ እንደሆነ አድርጎ በተሳሳተ መንገድ መዘገቡ ኢትዮጵያን እንደማያውቃት በግልጽ ያሳየ ነው” ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በለስለሰ ቋንቋ ቢናገሩም፣ ሚኒስትር ዴኤታዋ ትምህርት ሚኒስቴር የደረሱ ሠብሎችን ለመሰብሰብ በሚል ለሳምት ትምህርት እንዲቋረጥ ማድረጉን በመግለጽ የቢቢሲ ልዩ ተልዕኮ አሳይተዋል።

May be an image of 5 people, people standing and text that says 'BBC NEWS WORLD BBC News (World) @BBCWorld Ethio a closes schools to boo st civil war effo BBC NEW bbc. Eth pia closes schools to boost civil or effort AM 12/3/21 SocialFlow'

ቢቢሲ የኢትዮጵያን ባህልና አኗኗር ካለማወቁ የተነሳ ተማሪዎችና መምህራን ወደጦርነት አንደሚገቡ አድርጎ የተሳሳተ መረጃ ማሰራጨቱ ፍጹም ስህተት እንደሆነ ሚኒስትር ዳኤታዋ አመልክተዋል። ይሁን እንጂ አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ አፉን በፈታበት ቋንቋ፣ አድጎ ባደገበት ባህልና ኑሮ፣ ሁሉን ዘነግቶ ” … ሰኞ ኅዳር 27 እስከ ታኅሣሥ 3/2014 ዓ.ም. ዝግ እንደሚሆኑና ተማሪዎች፣ መምህራንና ሠራተኞች እንደየአካባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ ለአገራዊ ትግል አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ መወሰኑ ተገልጿል” ሲል የዘገበውን የአማርኛውን ክፍል አስመልክቶ በገሃድ ያሉት ነገር የለም። ቢቢሲ አማርኛ በተደጋጋሚ “የዜና ሸፍጥ” የሚሰራ ሚዲያ እንደሆነ የሚታውቀና ማስጠንቀቂያ የተሰጠው መሆኑ ይታወቃል። ለሸፍጡ አንድን ዜና ሶስት አራቴ ርዕስ እየቀያየረ የሚዘግብ ሚዲያ እንደሆነ የሚታወስ ነው።

“ይህ በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት እንግሊዝ እየተደጎመ በተለያዩ የአገሪቱ ቋንቋዎች የትህነግን ካድሬና ተላላኪዎች አሰማርቶ በቅጥፈት ዜና ሽብር እየነዛ ያለ ሚዲያ ለምን አዲስ አበባ እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል? አይበቃም ወይ? እስከመቼ ነው ትዕግስት” ሲሉ በርካቶች ዜናውን ተከትለው ቅሬታቸውን ገልጸዋል። በቅጥፈት ዜና ኢትዮጵያን እያተራመሱ ካሉት ሚዲያዎች የጀርመን ድምጽ፣ የአሜሪካ ሬዴዮና ቢቢሲ ተቀጥረው ከሚያገለግሉት “ኢትዮጵያዊያን” መካከል አብዛኞቹ ልተቀጠሩበት ዓላማና ለተሰጣቸው ኢትዮጵያን በሚዲያ የማሸበር ተግባር ታማኝ መሆናቸውን መንግስት በገሃድ ለህዝብ ስራቸውን እየነቀሰ እንዲያቀርብ፣ ድብብቆሹ እንዲገታ የሚጠይቁም በርክተዋል። ለአገራቸው የሚቆረቆሩ ጥቂቶች ክብር የሚያሻቸው ቢሆንም ” ማንነቱ በውል የማይታወቅ ነብሰገዳይን ቃለ ምልልስ እያደረጉ ማስታወቂያ የሚሰሩ የትህነግ ተላላኪዎችን በይፋ ስማቸውን ጠቅሶ ከነስራቸው ለሕዝብና ለታሪክ ይፋ እንዲያደረጋቸው” ሲሉ በምሁራን ስብሰባ ተነስቶ እንደነበር ይታወሳል።

“ሰብል የደረሰበት ወቅት በመሆኑ ተማሪዎችና መምህራን ህብረተሰቡን እንዲያግዙ የሚደረግበት መንገድ አዲስ አይደለም” ያሉት ሚኒስትርዋ፣ ተማሪዎችና መምህራን የበጎፈቃድ አገልግሎት ለህብረተሰባቸው የመስጠት ልምዳቸው ለዘመናት የቆየ አስታውቀዋል። “ቢቢሲ ይህን ታሪክ ባለማወቁ የተዛባ መረጃ አሰራጭቷል” ብለዋል።

በኢትዮጵያ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ፣ ንፋስና ከፍተኛ ምርት በሚገኝበት ወቅት ዕድሜያቸው የደረሰ ተማሪዎችና መምህራን፣ እነዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ምርት በመሰብሰብ ስራ ላይ እንደሚሳተፉ ግልጽና የምተለመደ ባህል መሆኑ ይታወቃል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ቢቢሲ ዜናውን ገልብጦ ለሽብር ተግባሩ እንዳዋለው ነው የተገለጸው። የአማርና ክፍል ግልገል ልጁ የሆነው ቅጥረኛው ክፍል ደግሞ ባህልና ወጉን ቢረሳ ረስቶ ሳይሆን ድርጎ የሚከፍሉትን ለማስደሰት እንደ ፈጣሪው ዜናውን ገልብጦ አቅሯል። ዜናውን ሲቋጭ ደግሞ ሃቁን አስቀምጧል።

ቢቢሲ አማርኛው በሴራ የጀመረውን ዜና ” “የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በሚሳተፉበትና ለአንድ ሳምንት በሚቆየው የአገራዊ ዘመቻ መረሃ ግብር ወቅት የሚስተጓጎለውን የትምህርት ሂደት ትምህርት ቤቶች በሚያወጡት የማካካሻ መርሃ ግብር አማካይነት እንዲካካስ ይደረጋል” ሲል “በጨዋ መንገድ ጨርሶታል” በማለት የሸረደዱም አሉ።

Exit mobile version