Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ ለታሪክ የሚቀመጥ መግለጫ አወጣ – “[ለሕዝባዊነታችን] ነብሰጡር እናቶች ብቻ በቂ ማስረጃ ናችው”

የትግራይ ሰራዊት ለጊዜዉ ተቆጣጥራቸዉ ከነበሩት ማለትም ሰሜን ሽዋ አካባቢዎች እንዲሁም ደሴና ኮምቦልቻ ሲለቅ ለበለጠ ድል መሆኑ በዉል የተረዳዉ የአካባቢዉ ህዝብ ለሰራዊታችን ያደረገዉ ትብብርና ድጋፍ የትግራይ ሰራዊት ምን ያህል ህዝባዊና ትክክለኛ ዓላማ ይዞ እንደሚዋጋ ህያዉ ምስክር ነዉ። በመሆኑም የትግራይ መንግስት በትግራይ ህዝብና ሰራዊት ዓቅም በፈቀደዉ መጠን አስፈላጊዉን ትብብር ላደረጉት የአፋርና አማራ ክልል ህዝቦች ያለዉ ክብር የላቀ መሆኑ ሲገልፅ ትላንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ የትግራይ ህዝብና ሰራዊት አራት ኪሎ ከመሸገዉ አጥፍቶ ጠፊ ፋሽሽት ቡድንና ተስፋፊው የአማራ ክልል አመራር ካልሆኑ በስተቀር ከማንም ህዝብ ጋር አንዳችም የጥቅም ግጭትም ሆነ ቁርሾ እንደሌለዉ ዳግም ያረጋግጣል።

ከትግራይ መንግስት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

በማደናገርና በማጭበርበር የሚገኝ ድል የለም!!

ወደር የለሽ የትግራይ ሰራዊት ተፈጥሮኣዊና ሰዉ ሰራሽ ችግሮች ሳይበግሩት ባለፉት ኣምስት ወራት ዘመናዊ የጦር መሳርያ የታጠቀ የፋሽሽት አብይ አሕመድ ቅጥረኛ ታጣቂ ሓይል በአማራና አፋር መሽጎባቸዉ የነበሩት በኮንኩሪት የተሰሩ ምሽጎች ደረማምሶ እንዲሁም የተለያዩ ገደላማ ተራሮችን ጥበብ በተሞላበት ኣኳሃን ተሻግሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂ እንዳልነበረ ኣድርጎታል። ይህ ዓለም ያስደመመዉ የትግራይ ሰራዊት ግስጋሴ አራት ኪሎ የመሸገዉ ምንድኛ አጥፍቶ ጠፊ ሓይል የሚይዘዉ የሚጨብጠዉ አጥቶ እንደለመደዉ ሰፊና ተከታታይ የበሬ ወለደ ዉሸት በማሰራጨት ተጠምዶ ከርመዋል። አሁንም በቁሙ የሚቃዥለት በእዉን ግን ያላገኘዉ ድል እንዳገኘ በማስመሰል እንደለመደዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለማደናገር በመፍጨርጨር ላይ ነዉ።

ነገር ግን መሬት ላይ ያለዉ እዉነታና የጥፋት መልእክተኛዉ ፋሽሽት አብይ አሕመድ ቡድንና ጋሻ አሻጋሬዎቹ የበሬ ወለደ ነጭ ዉሸት ለየቅል ናቸዉ ብቻን ሳይሆን የሰሜንና የደቡብ ዋልታዎች ያህል የተራራቁ ናቸዉ ቢባል እዉነታዉ መናገር እንጂ ማጋነን አይደለም።

ይኸዉም የፋሽሽት አብይ አሕመድ ቡድን ደሴና ኮምቦልቻ ጨምሮ በአፋርና በአማራ የሚገኙ የተለያዩ ቦታዎችን በዉግያ እንደተቆጣጠረ አድርጎ ያለምንም ይልኝታ እያሰራጨዉ ያለዉ የፈጠራ ወሬ ስለመሆኑ እኛ ብቻ የምንናገረዉ ሳይሆን የትግራይ ሰራዊት ተቆጣጥርአቸዉ በነበሩት ቦታዎችና ከተሞች የሚኖሩ የአፋርና የአማራ ህዝቦች እና የፋሽሽት ደጋፊዎች የሚመሰክሩት እዉነታ ነዉ። የኢትዮጵያ ሁኔታ የሚከታተለዉ የአለም አቀፍ ማህበረሰብም በሳተላይት ምስል የሚያረጋግጠዉ ሓቅ ነዉ።

በአጭሩ የትግራይ ሰራዊት ቀደም ሲል ይዞአቸዉ ከነበሩት አንዳንድ የአማራና አፋር ቦታዎች የወጣዉ የትግራይ ማእከላዊ ኮማንድ በወሰነዉ ዉሳኔ መሰረት መሆኑ ወዳጅም ጠላትም በዋነኛነት የኢትዮጵያ ህዝብ እዉነታዉ በዉል ሊያዉቅ ይገባል።

የላይኛው ፎቶ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል፤ ሁለተኛው ደግሞ ሸዋ ሮቢት ነው

እዚህ ላይ የትግራይ ሰራዊት ለጊዜዉ ተቆጣጥራቸዉ ከነበሩት ማለትም ሰሜን ሽዋ አካባቢዎች እንዲሁም ደሴና ኮምቦልቻ ሲለቅ ለበለጠ ድል መሆኑ በዉል የተረዳዉ የአካባቢዉ ህዝብ ለሰራዊታችን ያደረገዉ ትብብርና ድጋፍ የትግራይ ሰራዊት ምን ያህል ህዝባዊና ትክክለኛ ዓላማ ይዞ እንደሚዋጋ ህያዉ ምስክር ነዉ። በመሆኑም የትግራይ መንግስት በትግራይ ህዝብና ሰራዊት ዓቅም በፈቀደዉ መጠን አስፈላጊዉን ትብብር ላደረጉት የአፋርና አማራ ክልል ህዝቦች ያለዉ ክብር የላቀ መሆኑ ሲገልፅ ትላንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ የትግራይ ህዝብና ሰራዊት አራት ኪሎ ከመሸገዉ አጥፍቶ ጠፊ ፋሽሽት ቡድንና ተስፋፊው የአማራ ክልል አመራር ካልሆኑ በስተቀር ከማንም ህዝብ ጋር አንዳችም የጥቅም ግጭትም ሆነ ቁርሾ እንደሌለዉ ዳግም ያረጋግጣል።

በመጨረሻም የጥፋት ቡድኖች የትግራይ ሰራዊት ተቆጣጥራቸዉ በነበሩት አካባቢዎች የፈፀሙት በደሎችና ግፎች እያሉ የሚዘረዝሩት ጥላሸት የመቀባት አባዜያቸዉ ስለሆነ በተግባር ግን ምን ያህል የትግራይ ሰራዊት ህዝባዊ ሰራዊት መሆኑን በያንዳንዱ አካባቢዎች በሰራዊታችን የህክምና ማእከል አገልግሎት ያገኙ ነብሰጡር እናቶች ብቻ በቂ ማስረጃ ነዉ። ከዛም በተጨማሪ የህዝቡ ሃብትና ንብረት እንዳይዘረፍ እንዳይወድም ከወንጀለኞች በስተቀር ተራ የመንግስት አገልግሎት የሚሰጡ ሲቪል ሰርቫንት ተረጋግተዉ ህዝባቸዉ እንዲያገለግሉ እንዲሁም በየአካባቢዉ ያሉት ታጣቂዎችን ትጥቃቸዉ ሳያራግፉ የአካባቢዎችን ፀጥታ እንዲጠብቁ በተደጋጋሚ የትግራይ መንግስት በግልፅ አስተላልፈዋል።

ስለሆነም ፋሽሽትና ወራሪ ሓይሎችን እያቀረቡት ያሉትን ግፍና በደል የሚሉት የትግራይ መንግስት ቀደም ሲልም ለህዝቡና ለአለም ማሕበረሰብ እንደገለፀው በደሎች ካሉ በገለልተኛ አካል ተጣርቶ እስከ ተረጋገጠ ድረስ አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ በመውሰድ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት እያስታወቀ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝቦች የትግራይ ህዝብና መንግስት እያካሄዱት ያሉት ህዝባዊ ትግል ሕጋዊና ፍትሃዊ ትግል መሆኑን በዋነኝነት ደግሞ በህልዉና የተጋረጠበት አደጋ የመመከት ትግል ወሳኝ ምእራፍ መድረሱን በመገንዘብ በሚደረገዉ ፍልሚያ የበኩላቹህ ድርሻ እንድትወጡ የትግራይ መንግስት ያሳስባል።

የትግራይ መንግስት
ህዳር 29/2014

ፎቶና የቲውተር መረጃዎቹ መግለጫውን ለማመጣተን እንዲረዳ የተጨመረ ነው

Exit mobile version