Site icon ETHIO12.COM

የኢትዮጵያ ጥምር ሃይሎች በርካታ ከተሞች አስለቀው ወደ መርሳ እየገሰገሱ ነው፤ ” ጦርነቱ በዝግታ የሚደረገው ለምድን ነው?”

Members of the Ethiopian National Defense Force (ENDF) are seen on a truck in Shewa Robit, Ethiopia, on December 05, 2021. (Photo by Amanuel Sileshi / AFP)

ዛሬ ማምሻውን የመንግስት ኮሙኒኬሽ አገልግሎት በታላቅ የድል ዜና ይፋ እንዳደረገው በደሴ ግንባር ሐይቅ፣ ቢስቲማ፣ ባሶሚሌ እና ውጫሌ ከተሞች፣ በተንታ ግንባር በተካሄደው ማጥቃት ዓለም አምባ፣ መቅደላና ጎሽሜዳ ከተሞች ነጻ ወጥተዋል። ሠራዊቱም ወደ መርሳ እየገሠገሠ ነው። “የትግራይ ወራሪ ሃይል ከፈረሰ ጦነቱ ለምን ይዘገያል?” ለሚለው ጥያቄ አቶ ጌታቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

መከላከያና የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ በዘመቻ “በኅብረ ለብሔራዊ አንድነት” በወሰዱት ማጥቃት እርምጃ የተዘረዘሩትን ከተሞች ያስለቀቁት ጥምር ሃይሎች ወደ መርሳ እየገሠገሱ መሆናቸው ታውቋል። ትህነግ ” አውቄ ለቀኩ” ከሚለው ውጪ ዜናውን ተከትሎ ያለው ነገር የለም። ይልቁኑም እማኝ ሆኗል።

በተንታ ግንባር በተካሄደው ማጥቃት ዓለም አምባ፣ መቅደላና ጎሽሜዳ ከአሸባሪው የሕወሐት ወራሪ ነጻ እንደወጡ። በሁሉም ግንባሮች የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ወደ ውስጥ ዘልቀው በመግባት የተበታተነውን አሸባሪ ኃይል ቀለበት ውስጥ አስገብተው በመደምሰስ ፣ ወራሪው ኃይል የዘረፈውን ንብረት እንዲሁም የያዘውን መሣሪያና ትጥቅ ይዞ እንዳይወጣ እያደረጉት እንደሚገኙ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ ያስረዳል።

“የትግራይ ወራሪ ሃይል ከተበተነ ለምን ጦርነቱ ይዘገያል? ከተሞች ለምን ቶሎ ቶሎ ነጻ አይወጡም” በሚል አንዳንድ ወገኖች ለሚያነሱት ጥያቄ ” የኢትዮጵያ ሃይሎች ዋና ዓላማ ከተማ ማስለቀቅ ሳይሆን የገባው እንዳይወጣ ማድረግ ነው” ሲሉ ሃላፊዎችና የፖለቲካ አመራሮች አስታውቀዋል። እነዚህ ወገኖች በየፊናቸው እንደሚሉት ውጊያው የሚካሄደው ከሚፈረጥጠው፣ በሚዘገንን ሁኔታ ከሚረግፈውና በገፍ ከሚማረከው ሃይል ጋር እንደሆነ አስታውቀዋል። አክለውም ” እንድተባለው ከሚፈረጥጥ ሃይል ጋር ውጊያው የሚካሄድ ቢሆንም ከበባው እንዳሻው መፈርጠጥ እንዳይችል አድርጎት ተበትኗል። ይህን የተበተነ ሃይል መልቀም ጊዜ ይወስዳል። ጊዜ ቢወስድም ለቀማው ይቀጥላል። ነገ ተመልሶ ስጋት እንዳይሆን በገባበት የማስቀረቱ ስራ ከተሞችን በአፋጣኝ ከማስለቀቅ ይልቅ ቅድሚያ እንዲሰጥ አድርጓል። ከበባው ብመንም መልኩ አይላላም” ሲሉ ምክንያቱን አስረድተዋል።

ታግሶ ለሚጠብቅ ጉድ እንደሚያይ ያመለከቱት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ክፍሎች መሪው ዶክተር ደብረጽዮንም ” ከበባውን መስበር አልቻልንም” ሲሉ ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል። ይህን ተከትሎ በዩኔት የተደራጀ ሃይል ከከበባ መውታቱን አቶ ጌታቸው በዶክተሩ ላይ ማስተባበያ እንዲሆን ማድረጋቸውን አውስተዋል። ከሚዲያና መግለጫ ታቅበው የነበሩት የትህነግ መሪዎች ያዘነውን ደጋፊያቸውን ለማነቃቃት ” የትግራይ ሕዝብ በማንናውም መከራ ውስጥ ማለፍ ይችላል። ሰራዊቱም ከዚያ የወጣ ነው። በማንኛውም ግንባር ጥቃት መሰንዘር የሚችል አቅም አለን” ሲሉ ለዳግም ሌላ ጥቃት መዘጋጀታቸውን እያስታወቁ ነው።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በሁመራ፣ በጎምደር፣ በአፋርና በወሎ ግንባር ያደርገው የማጥቃት ሙከራ እንዳልተሳካም። በማይጠብሪ ግንባር ከሰላሳ ጊዜ በላይ ሞክሮ እንዳልሆነለት በተደጋጋሚ ሲነገር ነበር። አሁን ስልታዊ ማፈግፈግ ማድረጉን ያስታወሰው የትህነግ ሃይል በየት በኩል ዳግም ሊመጣ እንደሚችል ግምት ባይኖርም፣ በርካቶች እንደሚሉት ያለ የሌለ ሃይሉን ለመጨረሻ ጊዜ በአፋር በኩል ሊያዘመት እንደሚችል ግምት አለ። በማይጠብሪና በሁመራ በኩል ከቶውንም እንደማይሳካ እነዚህ ወገኖች ይናገራሉ።

በሌላ ወገን የሚሰማው ግን ትህነግ የመንግስት የተቀናጀ ሃይል ወደ መቀለ ሊመጣ እንደሚችል ፍርሃቻ ስላላቸው ” በሁሉም አቅጣጫ ጥቃት የመክፈት አቅም አለን” እንደሚሉና ሚስጢር የሆነው ሁለተናው የመንግስት ዘመቻ ለሁሉም ምላሽ እንደሚሰጥ አመልክተዋል።

Exit mobile version