“የፍጻሜ ዋዜማ” ድል ተመዘገበ፤ የመቀለ መንገድ ተቆረጠ፤ ለቀጣዩ ዘመቻ ቁልፍ ቦታዎችን መከላከያ ተቆጣጠረ፤ ከተሞች ነጻ ወጥተዋል

የኢትዮ ጅቡቲን የአውራ ጎዳናና መንገድ እንደሚቆርጥና አዲስ አበባን አንቆ ለመደራደር ቀናት እንደቀሩት፣ አንዳንዴም ዕቅዱ እንድተሳካ ሲያስታውቅ የነበረው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ከወልደያ ጋር የሚያገናኘው ጎዳና መቆረጡ ተገለጸ። በርካታ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸው አካባቢዎች ነጻ ወጥተዋል። ከቀን በፊት ” … እንደጀመረው በአጭር ጊዜ የጠላት ዕድሜው ያሳጥራል” ሲል የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ወታደራዊ ድል እያስመዘገቡ መሆኑንን አመልክቶ ነበር። ግን ቦታና አካባቢ አልገለጸም።

Image

አዲስ አበባን ለመቆጣተር ሰዓታት የቀሩት ተደርጎ ሲነገርለት የነበረው ትህነግ፣ በታክቲክ ለውጥ ያለ ውጊያ ከተሞችን እየለቀቀ መውታቱን ለደጋፊዎቹ ሲያስታውቅ ማርቲን ፕላውት ሃሳቡን ደግሞ “ሊገባኝ ግን አልቻለም” ብሎ ነበር። በሁለት ሳምንታት ውስጥ የያዘውን ሁሉ ያስረከበውና ተከቦ መውጫ እንዳጣ ሪፖርት የሚቀርበበት ትህነግ ባያምንም ዛሬ “ውድ” የተባሉ ድሎች እንደተመዘገቡበት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመልክቷል። ዝርዝር ስፍራዎችን ጠቅሶ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ሰሞኑንን ዳግም ወደ ዳንሻ መስመር ጥቃት ለመሰንዘርና በላሊበላ በኩል መውጫ ለማግኘት ሲታገል የነበረው ሃይል መደምሰሱ ተመልክቷል። የወልደያ መቀለ መንገድ በመዘጋቱ የትግራይ ወራሪ ሃይል ከገባበት መውጣት አመማቻሉ ብቻ ሳይሆን የዘረፈውን እየረጨ በየጥሻው በነብስ አውጪኝ ላይ መሆኑ ተመልክቷል። የመንግስት ኮሙኒኬሽ አገልግሎት መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል።

የጠላት ዕድሜ በአጭር ጊዜ ለመቋጨት… የሰራዊት አመራሮችፋሽስቱ አብይ ቡድን እንደ ሰማይ የራቀውን ድል አሰፍስፎ ለማዲያ ፍጀታ ለማዋል ሲፍጨረጨር ጀግናው የትግራይ ሰራዊት ደግሞ የጠላትን ሃይል የተለያየ ወታደራዊ ስልት ተጠቅሞ በማዳከም ከዚህም ከዚያም የተሸመቱ የጦር መሳሪያዎች እየተረከበው መሆኑ የትግራይ ሰራዊት አመራሮች ገለፁ ሲል ትግራይ ቴለቪዥ ዘግቧል። አመራሮቹ ሰራዊቱ

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ በአሸባሪው ወራሪ ላይ በሰነዘሩት ክንደ ብርቱ ማጥቃት፣ በምሥራቅ ግንባር ስትራቴጂያዊ የሆኑትንና ወራሪው በፍጻሜ ዋዜማ ላይ መሆኑን የሚያሳዩትን የዞብል ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የአርጆ፣ ፎኪሳ እና ቦረን ከተሞችን ተቆጣጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን በመቆጣጠር የወልድያ መቀሌ ዋናውን አውራ ጎዳና በመቁረጥ ጠላት መውጫ አጥቶ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ ግንባር የድሬ ሮቃና የሶዶማ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ከተሞችና ተራሮች በመቆጣጠር ጥምር ጦሩ ወደ ሐራ ከተማ እየገሠገሠ ይገኛል፡፡

See also  Adwa Victory Celebrations 2021

በውጫሌ ግንባር ደግሞ የአምባሰል ከፍተኛ ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ የሮቢትና የጎልቦን፣ በወረባቦ ወረዳ የሚሌ ኮትቻን፣ በሐብሩ ወረዳ የኮልቦን፣ የመርካታና የፋጂን አካባቢዎችን በመቆጣጣር ወደ መርሳ ከተማ እየገሠገሠ ነው፡፡

በእነዚህ ግንባሮች በተደረገው ኦፐሬሽን በአሸባሪው የጠላት ኃይል ላይ በተሠነዘረበት ማጥቃት ጠላት ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ ሆኗል፡፡ የወገን የመካናይዝድ ኃይልና ንሥሮቹ የአየር ኃይሉ በጥምረት ባካሄዱት ኦፐሬሽን የጠላት ኃይል ምንም ዓይነት ተሸከርካሪ እና ከባድ መሣሪያዎችን ይዞ እንዳይንቀሳቀስ ስላደረጉት፣ ጠላት በየአቅጣጫው ጥሎ ለመፈርጥጥ ተገድዷል፡፡ ለበርካታ ቀናት ያከማቻቸውን ቁስለኞችንም ጥሎ ፈርጥጧል፡፡ የዘረፈውን ንብረትም በየቦታው እያዝረከረከ እግሬ አውጪኝ በማለት ላይ ይገኛል፡፡

ጠላት ዋናው የቆቦ ወልድያ መንገድ ስለተዘጋበት በድንብርብር በጋሸና ላሊበላ በኩል ለማምለጥ ከፍተኛ ትንቅንቅ ቢያደርግም በወገን ጥምር ጦር እንደ ቅጠል ከመርገፍ አልተረፈም፡፡ በወረራ ውስጥ የቆየው ኅብረተሰብ በከፍተኛ ወኔና ጀግንነት በመነሣሣት ከወገን ጦር ጋር ተባብሮ በመሰለፍ አኩሪ ተጋድሎ ፈጽሟል፡፡ አሁንም ክንደ ብርቱውን የወገን ጥምር ጦር መቋቋም አቅቶት በየጢሻው የተበተነውን የአሸባሪውን ጀሌ፣ የየአካባቢው ሕዝብ በመማረክ፣ እምቢ ያለውንም በመደምሰስ የጀግንነት ተግባሩን እንዲፈጽም መንግሥት ጥሪ ያቀርባል፡፡

ነጻነታችንን የምናረጋግጠው በተባበረ ክንዳችን ነው!

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከሁለት ቀን በፊት ይህንን ቢልም ቦታና ስም ጠቅሶ አላስተባበለም።

“የጠላት ዕድሜ በአጭር ጊዜ ለመቋጨት… የሰራዊት አመራሮችፋሽስቱ አብይ ቡድን እንደ ሰማይ የራቀውን ድል አሰፍስፎ ለማዲያ ፍጀታ ለማዋል ሲፍጨረጨር ጀግናው የትግራይ ሰራዊት ደግሞ የጠላትን ሃይል የተለያየ ወታደራዊ ስልት ተጠቅሞ በማዳከም ከዚህም ከዚያም የተሸመቱ የጦር መሳሪያዎች እየተረከበው መሆኑ የትግራይ ሰራዊት አመራሮች ገለፁ ሲል ትግራይ ቴለቪዥ ዘግቧል። አመራሮቹ ሰራዊቱ እንደጀመረው በአጭር ጊዜ የጠላት ዕድሜን ያሳጥራልም ብለዋል።ትግራይ ታሸንፋለች”


Leave a Reply