Site icon ETHIO12.COM

እጃቸውን መስጠት የሚፈልጉ የትህነግ ከፍተኛ ሃላፊዎች መኖራቸው ተሰማ፤ ሸኔን “በቃኝ” ያሉ አመራሮች በቅርቡ ራሳቸውን ይፋ ያደርጋሉ

የግንባር ላይ ውጊያው የበላይነት መቀየሩን ተከትሎ በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር/ ትህነግ ከፍተኛ አመራሮችና የጦር መኮንኖች ዘንዳ ልዩነት መፈጠሩ እየተሰማ ባለበት በአሁኑ ወቅት እጅ መስጠት የሚፈልጉ መኖራቸው ተሰማ። ኦነግ ሸኔን “በቃኝ” ያሉ በቅርቡ ራሳቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የኢትዮ 12 የዋሽንግቶን ተባባሪ በትግራይ ካለው ቡድን ውስጥ ቤሰብ ካላቸው መስማቱን ጠቅሶ እንዳለው ሁኔታዎች ሁኔታዎች ቢመቻቹላቸው እጅ መስጠት የሚፈልጉ አሉ። በተለይ የጦር መክንኖች ከሆኑት ውስጥ በስም ጠቅሶ ቤተሰቦቻቸው ሁኔታ እንዲያመቻቹላቸው የጠየቁ እንዳሉ አመልክቷል።

ምንም እንኳን ትህነግ ጦርነቱን እንደሚገፋበት፣ አሁን ስልታዊ ማፈግፈግ እንዳደረገ፣ ማዕከላዊ መንግስቱን የሚገረሰስበት ጊዜ መቃረቡን እያስታወቀ ቢሆንም፣ በተደጋጋሚ በተለያየ ቋንቋ ይህን ሲያስታውቅ እንደቀድሞው ደጋፊዎቹ እየሰጡት ያለው መልስ ቀደም ሲል ከነበረው እጅግ የቀነሰ መሆኑ ታይቷል።

የትግራይ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ደርጅት መሪ ከሆኑ መካከል በዓላማ የሚመሳሰሏቸውን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ወጣቶች እንደሞቱ እየገለጹ ነው። እየተገለጸ ያለው ቁጥር እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ነገሩ መወያያ ከመሆኑም በላይ ” ስልታዊ ማፍግፈግ አድርጊያለሁ” በሚል ትህነግ ይፋ ከተናገረ ወዲህ ” ልጆቻችን የት አሉ” የሚል ጥያቄ የተነሳበት አግባብ መኖሩ ታውቋል። ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆኑ የክልሉ ተወላጆችም ጥያቄው በመላው ትግራይ እንዲቀጣጠል እየሰሩ መሆኑንን እየተነገረ ነው። በአደባባይም እየተገለጸ ነው። በዚህና በጦር ሜዳ ባልተገመተ ፍጥነት አዲስ አበባ ሊደርስ ነው የተባለው ትህነግ መቀለ ስለመሰንበቱም ጥርጣሬ እያየለ ባለበት ዛሬ ላይ ነው እጃቸውን መስጠት የሚፈልጉ በተዘዋዋሪ በውጭ አገር የሚኖሩ ቤተሰቦቻቸውን መገናኘት መጀመራቸውን ተባባሪያችን ያመለከተው።

ነዋሪነቷ በዋሽንግቶን የሆነ የትግራይ ተወላጅ ” ለምን ወደ አማራና አፋር ክልል ይህን ያህል ዘልቀው መግባት እንደፈለጉ አልገባኝም። በድርጊቱ ደስተኛ አልነበርኩም። በትግራይ በተፈጸመው አዝኜ ስታገል ነበር። አሁን አማራና አፋር ክልል የተፈጸመ ተብሎ የሚቀርበው አሳዝኖኛል። እንደ አንድ ቸዋ ቤሰብ ያሳደገው ሰውና ሴትነቴ አፍሪያለሁ።” ስትል በይፋ የማይመዘገብ አስተያየት መስጠቷን ተባባሪያችን ጨምሮ ገልጿል።

በሌላ ዜና የኦነግ ሸኔ ዋና ሴል የሚባለውና አሁን ላይ ኬንያ ውስጥ የሚገኙ ” በቃኝ” በሚል ራሳቸውን ያፋ ሊያደርጉ እንደሆነ በአንድ ታዋቂ ሚዲያ የሚሰራ ምስክር ለኢትዮ12 አመለከተ። ይኸው ተቀማጭነቱ ኬንያ የሆነ የሚዲያ ባለሙያ ዜናውን የሰማው ከኦነግ ሸኔ ሰዎች መሆኑንን አመልክቷል። ኬንያንም የማያምኑበት ደረጃ መድረሳቸውም ተመልክቷል።

በዋናነት ከትህነግ ጋር ከሚሴ ላይ ከገጠሙ በሁዋላ በከሚሴና አካባቢው ነዋሪዎች ላይ የተፈጸመው በደል በትህነግና በኦሮሞ መካከል ቀድሞውንም የተጀመረው ግንኙነት ልክ እንዳልነበረ ከስምምነት ከተደረሰ በሁዋላ ” በቃኝ” ያሉ መበራከታቸውን ነው የመረጃው ባለቤት ያስታወቀው። በከፍተኛ አመራር ደረጃ ትህነግና ኦነግ ሸኔ ያላቸው ውለታ በራሱ ምን እንደሆነ የማያውቁ መኖራቸውም ተጠቅሷል። ምን እየሆነ እንደሆነ የማያውቁና ያልገባቸው፣ ማብራሪያ ጠይቀው ያላገኙ እንዳሉም በመገረም እንደነገሩት፣ ከሚሰራበት ሚዲያ ወቅታዊ አመልካከት አንጻር የሰማውን ማተም እንደማይችል ገልጾ መረጃውን እንዳካፈለን ከሆነ በቅርቡ “በቃኝ” ያሉ የኦነግ ሸኔ ሰዎች አደባባይ ይወጣሉ።

የኦሮሚያ ክልል ሚዲያዎች የኦነግ ሸኔ አባላትና ተዋጊዎች ይቅርታ እየጠየቁ መግባት መጀመራቸውን ጠቅስው መዘገባቸው፣ በአንድ ወር ብቻ ከ400 እርምጃ እንድተሰውሰደባቸውና ክ160 በላይ እጅ መስጥታቸው መዘገባቸው ይታወሳል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር በሳምንቱ መጀመሪያ ኦነግ ሸኔ ፖለቲካዊ አላማና ግብ የሌለው የወሮ በላ ድርጅት እንደሆነ ጠቅሰው ” ይህ ነው የሚባል አቅም የሌለውና በየጫካው እየተሹለከለከ ንጹሃንን የሚገድል የትህነግ አገልጋይ ነው” ማለታቸው አይዘነጋም።

በርካታ የክልሉ ምሁራንና ነዋሪዎች ኦነግ ሸኔ በኦሮሚያ እንዲሆን የሚፈልገውንና ለሕዝብ ይበልጥ ይጠቅማል የሚለውን ሃሳብ ይዞ ከህዝብ ጋር መታገል እየቻለ፣ ከትህነግ ጋር አብሮ የኦሮሞ ልጆችን ለማደን መወሰኑና በርካታ ንጹሃንን መግደሉን አጥበቀው በመኮነን ጀርባ እንደሰጡት በተደጋጋሚ መናገራቸውና አሁንም እየተናገሩ ናቸው።


ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

Exit mobile version