Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ በሽሬና በመቀለ የዘርፈውን ነዳጅ በጥቁር ገበያ እየቸረቸረ መሆኑ ተሰማ

“አሸባሪው ሃይል በወረራቸው ከተሞች የነበሩ የነዳጅ ዴፓዎችን በመዝረፍ በሽሬና መቀሌ ከተሞች በጥቁር ገበያ እየተሸጠ ስለመሆኑ መንግስት መረጃ አለው” ሲሉ አቶ ምትኩ ካሳ አስታወቁ። ጉዳይን የመንግስታቱ ድርጅት እርዳታ ሰራተኞች በገሃድ እንደሚያውቁት ተመልክቷል።

የብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ እና የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ የኢትዮጵያን አስተባባሪ ካትሪን ሱዚ ናቸው በጋራ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ኮሚሽነር ምትኩ እንዳሉት በጦርነት ተጎጂ በሆኑ አካባቢ ለሚገኙ ዜጎች እርዳታ እንዲደርስ ሰብዓዊነትን ማዕከል ያደረገ የተኩስ አቁም መንግስት አድርጎ እንደነበር አስታውሰዋል። አለምአቀፍ የተራዕድ ድርጅቶች ባለፉት አምስት ወራት ህውሃት በወረራቸው የአማራ እና አፋር አካባቢዎች ምንም አይነት እርዳታ እንዳላደረሱም ተናግረዋል።

መንግስት የፍተሻ ኬላዎች ቁጥር እንዲቀንስ፣ የቪዛ ማራዘሚያ፣ የግንኙነት መሳሪያዎች ተደራሽ እንዲሆኑ እንዲሁም የገንዘብ አቅርቦት እንዲኖር በመፍቀድ በማድረግ የተመቸ ሁኔታን እንደፈጠረ ጠቅሰዋል። ሆኖም ግን አሸባሪው ሃይል ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ከቁብ ሳይቆጥር መንግስት የተኩስ አቁም ማወጁን ተከትሎ በአፋር እና አማራ ክልሎች ወረራን በመፈፀም ሰብአዊ ቀውሱ እንዲሰፋ አድርጓል ብለዋል። 

ከሰኔ ጀምሮ ወራሪው ሃይል በፈፀማቸው ወረራዎች በአማራ እና በአፋር ክልሎች1.8 ሚሊየን ህዝብ መፈናቀሉን ገልፀዋል። መንገዶችን በመዝጋት የምግብ እና ሌሎች የእርዳታ ቁሳቁሶች ተደራሽ እንዳይሆን በማድረግ ቀውሱ እንዲባባስ ማድረጉን አስታውቀዋል። እንዲሁም አሸባሪው ሃይል በወረራቸው አካባቢዎች በአጠቃላይ ከ8 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለምግብ እና ሌሎች ሰብአዊ ቀውሶች መጋለጡን ጠቅሰዋል።

ወትሮውም በምግብ እጥረት ተጋላጭ በሆኑት ሰሜን ወሎ እና ዋግህምራ አካባቢ ላሉ ሰዎች ባለፉት አምስት ወራት እርዳታ ማድረስ እንዳልተቻለ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል። አለምአቀፍ የተራዕድ ድርጅቶች ባለፉት አምስት ወራት ህውሃት በወረራቸው የአማራ እና አፋር አካባቢዎች ምንም አይነት እርዳታ እንዳላደረሱም ተናግረዋል።

የሽብር ቡድኑ በወረራቸው አካባቢዎች ሁሉ የሚፈፅማቸውን ሰብአዊ ጥፋቶች እና ዝርፊያዎች የመንግስታቱ ድርጅት አለማውገዙን ኮሚሽነር ምትኩ ተቃውመዋል። ኮሚሽነር ምትኩ ባለፈው ወር የእርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ የገቡ 203 የጭነት ተሽከርካሪዎች መመለስን አስመልክቶ ምንም ያደረገው እንቅስቃሴ አለመኖሩንም አንስተዋል።

የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ የኢትዮጵያ አስተባባሪ ካትሪን ሶዚ በበኩላቸው ተራዕዶን በሁሉም አካባቢ ላሉ ተጎጂዎች በእኩል ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ ተቋማቸው እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በአፋር እና አማራ ክልል ላሉ የጦርነቱ ተጎጂዎች የሰብአዊ እርዳታ እያደረግን ነው ብለዋል።

አስተባባሪዋ የሽብር ቡድኑ በእህል መጋዘኖች ላይ ተደጋጋሚ ዝርፊያ መፈፀሙን ያስታወቁ ሲሆን ከሰሞኑም በኮምቦልቻ ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ እህል መዝረፉን ተናግረዋል። 

የገንዘብ እና የነዳጅ እጥረት እንዲሁም በአፋር የነበረው የፀጥታ ሁኔታ አስፈላጊ እርዳታዎችን ትግራይ ለሚገኙ ተጎጂዎች ለማድረስ እንቅፋት እንደሆነ ካትሪን በመግለጫው ላይ ተናግረዋል። እርሳቸው እንዳሉት አሸባሪው ሃይል በወረራቸው ከተሞች የነበሩ የነዳጅ ዴፓዎችን በመዝረፍ በሽሬ እና መቀሌ ከተሞች በጥቁር ገበያ እየተሸጠ ስለመሆኑ መንግስት መረጃ እንዳለው ጠቁመዋል። 

እርዳታ ለማድረስ ወደ ትግራይ የሄዱ ከ1ሺህ በላይ የጭነት ተሽከርካሪዎች ዛሬም እንዳልተመለሱ እና አሸባሪው ሃይል እየተገገለባቸው እንደሚገኝም በጋራ መግለጫው ላይ ተጠቅሷል።

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

Exit mobile version