‹‹እስከአሁን ወደላሊበላና ኮምቦልቻ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ የጠየቀ አንድም የዓለም አቀፍ ተቋም የለም››

‹‹እስከአሁን ወደላሊበላና ኮምቦልቻ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ የጠየቀ አንድም የዓለም አቀፍ ተቋም የለም›› – አቶ ምትኩ ካሳ የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነርየኢትዮጵያ መንግስት ወደላሊበላ እና ኮምቦልቻ አየር ማረፊያዎች የሰብዓዊ ድጋፍ በረራ ፍቃድ ቢሰጥም እስካሁን ድረስ ድጋፍ ለማድረስ የጠየቀ አንድም የዓለም አቀፍ ተቋም የለም ሲሉ የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ አስታወቁ።

ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች በአማራ ክልል የሚገኙትን የላሊበላ እና ኮምቦልቻ አየር ማረፊያዎችን መጠቀም እንደሚችል ቢያሳውቅም እስካሁን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች እርዳታ ለማቅረብ የጠየቀ አካል የለም።

በአካባቢዎቹ ለአምስት ወራት ድጋፍ ያላገኙና እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች አሉ ያሉት ኮሚሽነር ምትኩ፤ መንግሥት ሁኔታዎችን ሲያመቻች ገብተው ሰብዓዊ ድጋፍ የማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት ወደተግባራዊ እርምጃ አለመግባታቸውን ተናግረዋል።

አቶ ምትኩ እንዳስታወቁት፤ በሰሜንና ደቡብ ወሎ አካባቢዎች ከተፈናቀሉ በሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ ዜጎች ባለፉት ለወራት እርዳታ ሳይቀርብላቸው የቆዩ ከአራት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ይገኛሉ። ዓለም አቀፍ እርዳታ ድርጅቶች ወደአካባቢዎቹ እርዳታ ጭነው ቢሄዱ እና ሰብአዊ ድጋፍ ቢያቀርቡ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዜጎችን መታደግ የሚቻልበት አማራጭ አለ።

የዚህን ዜና ሙሉ መረጃ ለማግኘት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ
https://www.press.et/ama/?p=60572

See also  ‹‹በትግራይ ያለው ቀጣይ የእርሻ ስራ ትልቅ ትኩረትና አስቸኳይ እገዛ ይፈልጋል ›› ዶ/ር አባዲ

Leave a Reply