Site icon ETHIO12.COM

ሱዳን እየጠናተች ነው፤ በርካታ ሞተዋል፤ ተቃውሞው እየሰፋ ነው

ምን አዲስ ነገር እንደተገኘ ዝርዝር መናገር ባይቻልም፣ ምዕራባዊያኑና አሜሪካ ከሱዳን ጋር እርጥብ እናቃጥል ብለዋል። በዚሁ ፍቅራቸው ሳቢያ የንጹሃን ሞትና እስር ለመብት ጥሰት መሰርት እንደማያሟላ ተቆጥሮ ለዘገባው ሳይቀር ቃላት የሚመረጥለት ደረጃ ተደርሷል። ዓለም ባንክም ብር ሃበትናል። ግብጽም የቤት ስራ ተሸካሚ አድርጋቸው ከወዲህ ወዲያ ቢገለበጡም ውስጣቸው ሊረጋ አልቻለም።

ዘወትር እያገረሸ የሚነሳው የሱዳን ተቃውሞና የህዝብ እንቢተኛነት እየጋለ ሲበርድ ኖሮ ዛሬ ቤተመንግስቱን ወሮ እስከማስጨነቅ ደርሷል።በነጮቹ አቆጣጠር የጥቅምት ሃያ አምስቱን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ታሳቢ በማድረግ ዛሬ ሰፊ ቁጥር ያለው ሕዝብ አደባባይ ወጥቷል። ሰልፉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰው ቁጥር የተሳተፈበት ሲሆን የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተኩሰዋል። በርካታ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ገለዋል።

መንግስ ውስጥ ወታደራዊ አካላት ፍጹም እንዲወጡና የሲቪል መንግስት እንዲቋቋም በተደጋጋሚ ሲጠየቅ እንደነበር ይታወሳል። የተገፈተሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዱክ ባለፈው ወር በጫና ወደ ስልጣናቸው እንዲመለሱ ቢደረግም፣ የሲቪል መንግስት እንዲቆም የሚቀርበው ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የተደረገበትን ቀን በማስታወስ ካርቱም በተቃውሞ እየተናጠች መሆኑ ከየአቅጣጫው እየተዘገበ ነው።

በዚሁ መነሻ የተነሳው ተቃውሞ እንደቀተለ ሲሆን ቢቢሲ የመለዮ ለባሹ ሃይል መግለጫ እስኪያወጣ ተቃውሞ የወጣው ሕዝብ ቤተመንግስቱን ከቦ እየተጠባበቀ መሆኑንን አመልክቷል። ተቃዋሚዎች በመንግስት ውስጥ ምንም አይነት ወታደራዊ ተሳትፎ እንዳይኖር ላቀረቡት የከረረ ጥያቄ ምን መልስ እንደሚሰጥም እየተጠበቀ ነው።

ዛሬ የቀድሞው መሪ ኦማር አልበሽር ከስልጣን እንዲወርዱ ምክንያት የሆነው ህዝባዊ እምቢተኝነት የተነሳበት ሶስተኛ አመት ምክንያት አድርገው ነው ተቃዋሚዎች ወደ አገሪቱ ፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግስት የተመሙት። መትመም ብቻ ሳይሆን ” ህዝቡ ጠንካራ ነው ፤ ማፈግፈግ የማይታሰብ ጉዳይ ነው ” በሚል ድምፃቸውን የሚያሰሙት ከቤተ መንግስቱ እጅግ ቅርብ ርቀት ላይ መሆኑንን ዘገባዎች አመልክተዋል። የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ሰልፉን ለመበተን በመኦከሩበት ወቅት ሰልፈኞች ራሳቸውን ለማስተንፈስ በጎዳና ላይ ሲሯሯጡ ታይተዋል።

የጸጥታ ሃይሎች ከሰልፉ ቀደም ብሎ በመዲናይቱ ዋና ዋና መንገዶችንና ድልድዮችን ቢዘጉም እንዳሰቡት ሰልፉን መቆጣጠር አልቻሉም። ሰልፈኞቹ ጀነራል ቡርሃን ለፍርድ ካልቀረቡ በስተቀር ወደ ሁዋላ የለም ብለዋል። ተቃውሞው ወደፖርት ሱዳንም ተሸጋግሯል። በከተማው የሚገኙ የመንግስት ተቋማት በሙሉ በሚባል ደረጃ በሰልፈኞች ቁጥጥር ስር መውደቃቸው ተሰምቷል።


Exit mobile version