Site icon ETHIO12.COM

በኦሮሚያ ወቅቱን ያገናዘበ የልማት ስራና የሸኔን ሃይል ሙሉ በሙሉ የማጥራ ዘመቻ – 7500 የሸኔ ታጣቂዎች ተያዘዋል

በኦሮሚያ አገሪቱ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ያገናዘበ የልማት ስራ በከፍተኛ የስራ ዲሲፒሊንና ቁርጠኛነት እየተሰራ ሲሆን፣ ጎንለጎን ሸኔን እስከ መጨረሻው በመደምሰስ የኦሮሚያ ክልልና የኢትዮጵያን ሰላም የማረጋገጥ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ በወቅታዊ የክልሉ የልማትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈርጀ ብዙ ጦርነት በአሸናፊነት ለመወጣት የኦሮሚያ ክልል መንግስትና ህዝብ በሁሉም ግንባር ኢኮኖሚውንም ሆነ ለጦር ግንባር ጀግኖች ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመዋል።

በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከህዝብ ጋር በመተባበር የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው የተቀናጀ ዘመቻ ከ1500 በላይ የሸኔ የሽብር ቡድን አባላት ተደምሰዋል ብለዋል።

በከተሞች ውስጥ የተደራጁ የአሸባሪው ሸኔና ህወሓት የሎጂስቲክ እንዲሁም የመረጃ ስራ የሚሰሩ ከ7500 በላይ አባላቶቻቸው በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ ስለመሆኑም በመግለጫው ተገልፆል።

በኦሮሚያ ክልል በመኸር እርሻ በዘር ከተሸፈነው 6.3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት 4.8 ሚሊየኑ መሰብሰቡን አቶ ኃይሉ አዱኛ ግልጸዋል፡፡

በግብርናው ዘርፍም ሃገሪቱ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ያማከለ የልማት ስራዎች በተለይም ስንዴን በሁለት ዙር በስፋትና በእጥፍ የማምረት ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆናቸውም አንስተዋል።

በክልሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ግዜውን ያማከለና በህዝብ ዘንድ በዘርፉ የተነሱ ቅሬታዎችን በፍጥነት ለማስተካከል ክልሉ ግብረ ሃይል አቋቁሞ ወደ ስራ በመግባት ተጠያቂነትን ናያስቀደመ አሰራር እንዲሰፍን ከፍተኛ ቁጥጥር እንደሚደረግም ተገልፆል።

በኮሰን ብርሃኑ via EBC


Exit mobile version