“ቄሮና ቀሬ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጅተዋል”

“ቄሮና ቀሬ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጅተዋል” – አቶ ኃይሉ አዱኛ የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ


ትላንት በድንጋይና በዱላ አሸባሪውን ሲፋለም የነበረ ቄሮና ቀሬ ዛሬ ዘመናዊ ጦር መሣሪያ በመታጠቅ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል መከላከያ ሠራዊት ጎን መቆማቸውን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ ፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አሸባሪው ሕወሓት ደደቢት በረሃ ከገባ ጀምሮ የሀገር ሉዓለዊነትና አንድነትን ከቻለ ማፍረስ ካልቻለ ለማተራመስ አቅዶና በማኒፌስቶው አካቶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡

አሸባሪው ቡድን ሥልጣን ከያዘበት ዘመን ጀምሮ የሀገሪቱን ሕዝቦች በትናንሽ ልዩነቶች በመከፋፈልና በማባላት የተዳከመች ኢትዮጵያን ለመፍጠር አልሞ ሲሠራ መቆየቱን የገለጹት የኮሙኒኬሽን ኃላፊው የሀገሪቱን መከላከያ ሠራዊት በመበተንና የአንድ ብሄር የበላይነት የሰፈነበት የመከላከያ ሠራዊት በመገንባት የተዳከመች ሀገር ለመፍጠር መሞከሩን ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶ ኃይሉ ገለጻ፤ በኢኮኖሚውም በኩል በዓለም ዓቀፍ ፋይናንስ ተቋም መረጃ መሠረት የተቆናጠጠውን ሥልጣን በመጠቀም 30 ቢሊዮን ዶላር በመዝረፍ የኢትዮጵያን ካዝና ባዶ አስቀርቷል፡፡ በሀገሪቱ የሚገኙ እስር ቤቶች አፋን ኦሮሞ የሚነገርባቸው እስኪመስሉ ድረስ የኦሮሞ ወጣቶችን በስፋት ሲያስር ቆይቷል፡፡

ከሥልጣን ከተባረረ በኋላም በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ያልተረጋጋ ክልል እንዲሆን የተለያዩ ሴራዎችን ሲያቀነባብር መቆየቱን አቶ ኃይሉ ተናግረው በመጨረሻም ሀገሪቱን ለመበተን በማሰብ የሰሜን ዕዝን ከኋላው በመውጋት አሳፋሪ ታሪክ መሥራቱን ጠቁመዋል፡

EPA

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2654 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply