የኦሮሚያን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የኦሮሚያ ብሐየራዊ ክልላዊ መንግስት የጀመረውን ዘላቂ ሰላም የማስፈን ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል” ያሉት አቶ ኃይሉ “ለሰላም የተዘረጉ እጆች አይታጠፉም” በማለት መንግስታቸው ችግሮችን በሰላማዊ መንግድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት አስገንዝበዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል የሚደረጉ ግጭቶን በሰላማዊ መንግድ እልባት እንዲያገኙ መንግስት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ፡፡የክልሉ መንግስት የኮሚዩኒኬሽን ጉዳይ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሲሰጡ እንደተናገሩት፣ በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል አዎንታዊ ሚና መጫወት አለበት፡፡በክልሉ ወባ እና ኮሌራ ወረርሽኝ በተከሰቱባቸው አከባቢዎች ሕክምና ለማደረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አቶ ኃይሉ አስታዉቀዋል።
የኦሮሚያ የመህር ምርት እቅድ
የ2016 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ ክንውን ላይ አተኩረው መግለጫውን የሰጡት የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ፤ መግለጫቸውን የጀመሩት ስኬታማ ባሉት የክልሉ የልማት እንቅስቃሴ ነው፡፡ በዚህም በዓመቱ 9.2 ሚሊየን ሄክታር በተለያዩ አዝርት ተሸፍነው ከዚሁ የመሄር እርሻ 265 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ አስረድተዋል፡፡ በኢትዮጵያ እምብዛም ባልተለመደው ከሩዝ እርሻ እንኳ ከ44 ሚሊየን ኩንታል የላቀ ምርት እንደሚጠበቅ ነው ኃላፊው ያስረዱት፡፡ በዓመቱ 2.6 ሚሊየን ሄክታር መሬት በበጋ ስንዴ ለመሸፈን ውጥን መያዙንም እንዲሁ፡፡

በክልሉ ሰላምን የማስፈን ውጥን
በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የክልሉ መንግስት እየሰራ ነው ስላሉት እቅድም ያብራሩት የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ፤ ከዚህ አኳያ መንግስታቸው ያለውን ቁርጠኝነት አስረድተዋል፡፡
“የኦሮሚያን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የኦሮሚያ ብሐየራዊ ክልላዊ መንግስት የጀመረውን ዘላቂ ሰላም የማስፈን ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል” ያሉት አቶ ኃይሉ “ለሰላም የተዘረጉ እጆች አይታጠፉም” በማለት መንግስታቸው ችግሮችን በሰላማዊ መንግድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት አስገንዝበዋል፡፡ “ለሰላም የተዘረጉ እጆች አይታጠፉም፤ ሊታጠፉም አይችሉም” በማለትም ሰላምን በሰላማዊ መንገድ የማስፈን ጥረቶች እንደሚቀጥሉ በመግለጽ የተለያዩ ማህበረሰብ አዎንታዊ ሚናንም ጠይቀዋል፡፡ ልዩነቶች በሰላም እንዲፈቱ እንፈልጋለን ያሉት ኃላፊው “ሌላውም ወገን እንደዚህ አይነት ቁርጠኝነት ማምጣት አለበት የሚለውን ማስታወስ እንፈልጋለን” ነው ብለዋልም፡፡
የኮሌራ እና ወባ ወረርሽኝ ግብረ መልስ
አቶ ኃይሉ በዛሬው መግለጫቸው ኮሌራ እና የወባ ወረርሽኝ በስፋት በክልሉ ተከስተው እንደነበር አብራርተዋል፡፡ ኮሌራ በ11 የኦሮሚያ ዞኖች ውስጥ በሰባት ከተሞች እና 83 ወረዳዎች ተከስቶ 10 ሺኅ ሰዎችን ማትቃቱን ነው ያነሱት፡፡ በሽታውን ከማከብ በተጨማሪ እንዳይስፋፋም ለ2 ሚሊየን ሰዎች የቅድመ መከላከል ክትባት እና መድሃኒት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡
በኦሮሚያ በስፋት ስለተከሰተው የወባ ወረርሽኝም አስመልክተው፤ ወረርሽኙ ሰባት የኦሮሚያ ዞኖች ላይ መከሰቱን ጠቅሰው፤ 5 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች በተደረገው ምርመራ ከ600 ሺህ በላይ በሽታው ተገኝቶ የህክምና አሰጣጥ ስራ ተከናውኗል ብለዋል፡፡ የበሽታውን መስፋፋት ለመከላከልም የአጎበር እደላን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት መከወኑን ገልጸዋል፡፡
ዘገባው የጀርመን ድምጽ ነው
- ሰው ሰራሽ ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን መቀላቀል የኢትዮጵያ ሌላ አማራጭ?አርተፊሻል ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ኢትዮጵያ የባህር በር ሊኖራት ይችላል፤ ይህ በአለም ላይ በኢትዮጵያ የአፋር ምድር ረባዳነት የተነሳ ተፈጥሮ የሰጠው እድል ነው! በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል አርተፊሻል ቦይ በመስራት ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት መሆን ትችላለች፡፡ እንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሊፈጠር የቻለው፤ የኢትዮጵያ የአፋር ቦታ ከባህር ወለል በታች እስከ 110 … Read moreContinue Reading
- ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ቁጥጥሩን አጠንክሮ እንደሚገፋበት አስታወቀ፤ ህገወጥ የወርቅ አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ በአገሪቱ የሚታየውን የዋጋ አለመረጋጋት ለመግራት የግንዘብ ስርጭት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ የተጀመረው ስራ ውጤት እያሳየ መሆኑ ተመለከተ፤ ተጠናክሮ ክምሩ እንደሚሰራበትና ግሽበትን በዓመቱ መጨረሻ 20 ከመቶ ለማድረስ መታቀዱ ተሰማ። ህገወጥ የወርቅ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና የማበረታቻ መደረጉ ለውጥ ቢያሳይም በቂ እንዳልሆነ ተመለከተ። … Read moreContinue Reading
- የኮሚሽኑ የቀድሞ ሠራተኞች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የሙስና ክስ ጋር ተያይዞ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ሆነየአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የቀድሞ ሠራተኞች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የአልባሳት ግዢ ጋር ተያይዞ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ተደረገ። ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ … Read moreContinue Reading
- መንግስት የነዳጅ ድጎማን በህገወጥ መንገድ ሲጠቀሙ ነበሩ ያላቸውን 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከስርአቱ አስወጣ፣ የሰርቁትን ይከፍላሉየታለመለት የነዳጅ ድጎማን ላልተገባ ዓላማ ሲጠቀሙ የነበሩ 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ስርዓቱ እንዲወጡና ዕዳ እንዲከፍሉ መደረጉን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ። ሚኒስትሯ ይህን ያሉት የመንግሥት የ2016 የመጀመሪያ የሩብ ዓመት አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት ነው። የግምገማው ተሳታፊዎች መንግሥት የነዳጅ ድጎማን ጨምሮ በርካታ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋገጡ ተግባራትን ማከናወኑን አድንቀው፤ ሆኖም” ድጎማው … Read moreContinue Reading
- በዓመት አምስት ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ የሚያመርተው ፋብሪካ ከመጋቢት በሁዋላ የሲሚንቶ ዋጋ ወደ ነበረበት የሚመልሰ ነውበቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንዲያመርት እቅድ ተይዞለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ እየተገነባ ያለውን የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የግንባታ በመጋቢት ወር ይጠናቀቃል። ምርቱ በተባለው ወር ሲጀምር የሲሚንቶ ዋጋ አሁን ካለበት በግማሽ እንደሚወርድ ይጠበቃል። ከመጋቢት በሁዋላ ፋብሪካው በ50 በመቶ የሲሚንቶ እጥረቱን ያስወግዳል። ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ኩባንያ … Read moreContinue Reading