Site icon ETHIO12.COM

ብልጽግናን ለመሰንጠቅ እቅድ ወጣ፤ በትግራይ ፓርቲዎች ከወዲሁ “በድርድር አለሁበት” እያሉ ነው

ቅድሚያ ሪፈረንደም እንዲደረግ በሚፈልጉና የደቡብ አፋሪቃና ሩዋናዳ አይነት ዕርቀ ሰላም ቅድሚያ መደረግ አለበት በሚሉ ወገኖች መካከል አለመግባባቱ ምን ደረጃ እንደደረሰ የሚያሳዩ መረጃዎች ባይኖሩም “ዕርቀ ሰላም ይቅደም” የሚለው ቡድን ብልጽግናን ሰንጥቆ በልዩነቱ ውስጥ እድል ለማግኘት ስልት መንደፉ ተሰማ። በዚህ እርቅ ይቅደም በሚለው ቡድን ላይ ሌሎች ፓርቲዎች ” አለንበት” የሚል ድምጽ አሰምተዋል።

ቡድኖቹን በስም ለይተው ሳይጠሩ ሁለት ሃሳብ እንደሚቀነቀን ከትህነግ አመራሮች ጋር በሚደረግ የጎንዮሽ ንግግር መስማታቸውን የገለጹ እንዳሉት ድርድር እንዲደረግ የሚፈልጉት ወገኖች ብልጽግናን ለመሰንጠቅ እቅድ አስቀምጠዋል። እቅዱ በሌሎች አቅም ባላቸው አገሮችና የዚህ ልምድ ባላቸው ተቋማት እንደሚታገዝም ታውቋል። ዕቅዱ በየደረጃው እንደሚወርድ ተሰምቷል። በዋናነት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለይቶ በመምታት ላይ ያተኮረ ነው።

የሽግግር መንግስት እንዲቋቋምና ትህነግ የመሪነቱን ሚና እንዲጫወት ብልጽግናን ለመፈርከስ ቀደም ሲል በከፍተኛ ደረጃ ሲሰራ የነበረ ቢሆንም ሕዝብ አንድ መሆኑ ቀዳዳውን እንዳጠበበው፣ በተለይም በኦሮሚያ በድንገት በተወሰደ ማጥራት ዕቅዱ ሊከሽፍ እንደቻለ መረጃውን የሰሙት አመልክተዋል። የብልጽግናን ከፍተኛ አመራሮች ከአገር እንዲወጡ ምልጃና ማበባያ በማቅረብ ስማቸው ያልተገለጸ ጥቂቶች ቪዛ እስከመውሰድ ደርሰው እንደነበር አቶ ታዬ ደንደአ ከትህነግ ዳግም መመታት በሁዋላ መግለጻቸው የሚታወሰ ነው።

አሁን ባለው የጦርነት አውድ ትህነግ የማሸነፍ አቅሙ መዳከሙን ተከትሎ በእርቅ ተስታኮ በሚፈጠር ግንኙነት ቀደም ሲል የነብረውን ሰንሰለት በመተቀም ብልጽግናን ለመሰንጠቅና አመራሮቹን በማስፈራራት ስራቸውን እንዳይሰሩ የማድረግ ንድፍ መዘጋጀቱ ይፋ ሆኗል። መረጃውን የነገሩንና ይህ ሲባል የነበሩ እንዳሉት ትህነግ በወልቃይት በኩል ያሰበውን ያኽል መሄድ ስላልቻለ በወዳጆቹ ተደግፎ መንግስትን በመከፋፈል አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት አዳዲስ ሊታመኑ የሚችሉ ሚዲያዎች እንደሚከፈቱም ታውቋል።

ቀደም ሲል እንደ እነ አቶ ለደቱና የሚታወቁት ለትህነግ የሚሰሩ ሚዲያዎች ተጽዕኖ የሚያምናቸው በመጥፋቱ፣ የትግራይ ሚዲያዎች ” የትግራይ ዋና ከተማ መቀለ ነች” ቢሉ እንኳን የሚያምናቸው ስለሌለ አዳዲስ ሚዲያ እንደሚቋቋም፣ ሚዲያዎቹም በአዲሱ የፌዴራል ሃይሎች ጥምረት በሚባለው የግለሰቦች ስብስብ በየብሄረሰቡ ቋንቋ እነደሚሆን ከመረጃ ሰዎቹ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።



ኦባሳንጆ በኬንያ ወደ ሩሲያ ማምራታቸው የሰላሙን አካሄድ ተስፋ ሰጪ አድርጎት ይሁን በሌላ መነሻ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የተባሉ ፓርቲዎች ” ትግራይ አስመልክቶ በሚደረግ ውይይት ህወሓት ብቻውን ሊፈፅመው አይገባም፣ ዘላቂ ሰላም የሚመጣው የክልሉ ሁሉንም ፓርቲዎች ባካተተና ሁሉም የትግራይ ኃይሎች ባሳተፈ መልኩ ሊፈፀም ይገባል” ማለታቸውን አሜሪካ ሬድዮ ዘግቧል።

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ ባይቶና እንዲሁም ውድብ ናፅነት ትግራይ የተባሉ ሦስት የክልሉ ፓርቲዎች ባወጡት የፅሑፍ መግለጫ የዓለም ማኅበረሰብ ጦርነቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲቋጭ የሚያደርጉት ጥረት እንደሚያደንቁ አስታውቀው በሰላም ድርድር ውስጥ እንዲካተቱ ጠይቀዋል። ፓርቲዎቹ የትህነግ አመራሮች ወደ ቆላ ተንቤን በወረዱበት ወቅት አብረው ሆነው አዲስ የተቋቋመውን ሰራዊት ጋር አብረው ሲሰሩ መቆየታቸውና ጦሩ ውስጥ እጃቸው እንዳለ ሲገለጽ እንደነበር ይታወሳል። በመሆኑም አብዛኞቹ በመገንተል የሚያምኑ እንደሆኑ ይታወቃል። ዓላማቸው መገንተል የሆነው የዘር ፓርቲዎች መደራደር ከሚፈልገውና በሰላም ውስጥ ብልጽግናን ለመፈርከስ ከሚሰራው ቡድን ጋር ያላቸው ልዩነት ሊሰፋ እንደሚችል ግምት የሰጡ አሉ።

ብልጽግናን መሰንጠቅ የሚለውን ዕቅድ ደርሶበት ይሁን በሌላ ምክንያት የኦሮሚያ ክልል ዳግም ራሱን ሊያጸዳ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተመልክቷል። ኦሮሚያ ብልጽግና እዛና እዚህ የሚጫወቱ መለየታቸው ተሰምቷል። መቼና እንዴት እንደሆነ አይታወቅም እንጂ ክልሉ ሁሉንም እንቅስቃሴና ጨዋታ መለየቱን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እየገለጹ ነው።

Exit mobile version