የኦሮሞ ፌድደራላዊ ኮንግረንስ ስራ አስፈጻሚ ጃዋር መሐመድ ኦሮሞ ብልጽግናን ለመቀላቀል እንቅስቃሴ ላይ እንዳለ የድርጅቱ አንድ ከፍተኛ አመራር ለኢትዮ12 ገልጹ። በጉዳዩ ዙሪያም በግልጽ ከጃዋር ጋር ንግግር መደረጉንም አመልክተዋል። የዳሬ ሰላሙ የሰላም አማራጭ ንግግር መግባባት እየታየበት መሆኑ ተሰማ።
በጃዋር ጥያቄ ይሁን በሶስተኛ ወገን መልዕክተኞች አማካይነት ጉዳዩ ሲቀነቀን እንደነበር ቁርጥ ያለ መረጃ ለመስጠት እንደሚችገሩ ያስታወቁት እኚሁ ሰው ” ጃዋር በኦፌኮ እንደቀድሞው ንቁ ተሳትፎ አያደርግም” ብለዋል።
“ሽማግሌው ባሉበት” አሉ የዜናው ባለቤት የኦፌኮ አመራር ” ሽማግሌው ባሉበት / መረራ ጉዲናን ነው/ ብልጽግናን ለመቀላቀል እንቅስቃሴ ላይ ነህ አይጠቅምህም። ከጠቀመህ ቀጥልበት” እንድተባለ አመልክተዋል።
ጃዋር ራሱን ብቻ ሳይሆን ኦፌኮን ይዞ ከብልጽግና ጋር አብሮ መስራት እንደሚፈልግ በተደጋጋሚ መረጃ ለድርጅቱ ይደርስ እንደነበር በማመልከት በዚህ ዙሪያ ግልጽ ውይይት መደረጉን አመልክተዋል።
ጃዋር አዲስ አበባ እያለ እንኳን እንደቀድም ቢሮ እንደማይመጣ ያመለከቱት የኦፌኮ አመራር፣ በቀጥታ ባይገልጹትም በኦሮሚያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ህብረት የሚያመሩበት አጋጣሚ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየሰፋ እንደሄድ አመልክተዋል።
ጉዳዩን አስመልክቶ የብልጽግና ኦሮሚያ ባለስልጣኖችን ለማነጋገር ቢሞከርም ምንም ፍንጭ ማግኘት አልተቻለም። ይሁን እንጂ ፓርቲው በክልሉ ካሉ ተቀናቃኞች ጋር ስምምነት ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ ታውቋል።
ጃዋር መሐመድ ከእስር ከወጣ በሁዋላ ” የአንድነት ሃይሎች ከዱኝ” በሚል ቅሬታ ካሰማ በሁዋላ የቀድሞ አቋሙን በመቀየር ” ሰላም” በማለት ሁሉም ወገኖች ለሰላም መገዛትና መስማማት እንዳለባቸው በገሃድ አቋም ይዞ መቅረቡ በርካቶችን አነጋግሮ ነበር። ከዚህም በላይ ዝምታን የመረጠው ጃዋር ” ምን እያደረገ ነው” የሚል ጥያቄም ከየአቅጣጫው እየተሰማ ነው።
የኦፌኮ አመራር ” ለዝምታው ቀጥታ ምላሽ የለኝም። ይሁን እንጂ የአቋም ለውጥ ማሳየቱን ማንም አይክድም። የሚጠይቀው ቢገኝ እሱም ያምናል” ብለዋል። አያይዘውም ” በፓርቲያችን የቀድሞ እይነት እንቅስቃሴ አያደርግም። በስልክ አንዳንዴ ከቢሮና ከፕሮፌሰር መረራ ጋር ሚያደርገው ግንኙነት ውጭ እንደ ፓርቲ አመራር የጎላ ሚና አያሳይም። ይህ ግርታን ፈጥሯል። በቅርቡ መጥራቱ አይቀርም” ብለዋል።
አንዳንዶች ጃዋር የሰላም ውይይት እንዲደረግ እያመቻቸ እንደሆነም አስተያየት ሲሰጡ ነበር። ከኦነግ ጋር ብዙም ፍቅር የሌለውና በከፍተኛ ደረጃ ሲተቻቸው እንደነበር የሚያስታውሱ ” እንዴት ጃዋር ሊሰሙት ይቻላሉ። የኦነግ ሰዎች ጃዋርን አይወዱትም። ክፉኛ አውግዟቸዋል” ይላሉ። አያይዘውም ኦነግ እያለ ኦፌኮን መምረጡ የዚሁ ውጤት በመሆኑ የሰላም አመቻች ነው መባሉን ብዙም አይቀበሉም። ይሁን እንጂ ፍላጎት እንዳለው ከእስር ከወጣ በሁዋላ ሲሰጣቸው ከነበራቸው የአደባባይ ንግግሮች ማረጋገጥ እንደሚቻል ገልጸዋል።
ጃዋር ከአቶ በቀለ ገርባ ጋር የነበራቸው ግንኙነት እንደቀድሞ እንዳልነበር የሚጠቁሙ፣ በሁለቱ መካከል የነበረው ፍቅር ምን እንደገባው አሁን ድረስ መረጃ አላገኙም። ይሁንና አቶ በቀለና ጃዋር አቶ ለማን መገርሳን ይዘው ብልጽግናን ለመጠቅለል ያደረጉት ሙከራ በዶክተር አብይ ድንገተኛ ውሳኔ ከከሸፈ በሁዋላ በሁለቱ መካከል መተማመን እንዳልነበረ ያወሳሉ።
ጃልመሮን ያካተተ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትና የመንግስት የሰላም አማራጭ ንግግር በዳሬሰላም እየተካሄደ መሆኑንን ገልጸን መዘገባችን አይዘነጋም። ጃልመሮ ካሉበት ጭካ በአደራዳሪዎች አማካይነት ሄሊኮፕተር ቀርቦላቸው ከደንቢ ዶሎ ወደ ዳሬ ሰላም መግባታቸውን ኢትዮ ስታንዳርድ ነው ቀድሞ የዘገበው። እንደ አንዳንድ ምንጮች ውይይቱ ግልጽ ባይወጣም ቀድመው የተሰሩ ስራዎች ስላሉና በህገመንግስቱ ማክበር ጉዳይ አማጺዎቹ በማስማማታቸው መልካም ውጤት ይጠበቃል።
በመጀመሪያው ንግግር ላይ ከማጺው ሃይል በኩል የተነሱት የህገመንግስት ጥሰት የታየባቸው ጉዳዮች ሙሉ በሙሉ ማስተካከያ ተወስዶባቸዋል። በዚህም መነሻ ንግግሩ በርካታ መሻሻል የታየበትና ለመግባባት የሚያስችል ቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ንግግር መጀመሩም ተሰምቷል።
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New Development Bank. In a media briefing regarding the… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከሃምሳ ሺህ በላይ… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊየን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን ተገለጸ። 1 ነጥብ 2… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን መንግስት አስታወቀ። መረጃው ቀድሞውንም ዜናው “ሴራ”… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው አፍሪካ ህብረትን ስጋት ላይ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች