በአሜሪካ ብልጽግናን ተክቶ አራት ኪሎ እንዲገባ ” ዳግማዊ ኢህአዴግ” እንደገና እየተበጀ ነው፤ መንግስት ሙሉ መረጃው አለው

በአሜሪካና በተለያዩ አገራት የሚገኙ ስደተኛ ፖለቲከኞች ብልጽግናን በመተካት አራት ኪሎ ለመግባት አሜሪካንን እያባበሉ መሆኑ ተሰማ። እንደ ዜናው ከሆነ አቶ ለማ መገርሳ፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና የትህነግ የአሜሪካ ህዋስ አሉበት። ስብስቡ ” ዳግማዊ ኢህአዴግ” የሚል ስም በአንዳንድ ተጋባዦች እየተሰተው ነው።

ለውጡን በሙሉ አቅሟ ደግፋ የነበረችው አሜሪካ በቅጽበት የብልጽግናን መንግስትና መሪውን ዶክተር አብይ አሕመድን ለማስወገድ የተነሳሳችበትን ምክንያት በግልጽ አላስታወቅችም። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ፣ኤርትራና ሶማሊያ በጋራ በቀይ ባህር ላይ የደረሱበት የጋራ ስምምነት ዋናው ምክንያት እንደሆነ በርካቶች ጽፈዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስን ለመንቀል የማትተኛው አሜሪካ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት በታደንቅም፣ ኢሳያስ አፉወርቂና አብይ አህመድ መሻረካቸውን አልወደደችም። በዚሁ መነሻ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ኢሳያስ እስከሚነቀሉ ድረስ መጥፋት የለበትም የሚል አቋም በመያዟ ሳቢያ አሜሪካ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን መንግስት ለማስወገድ መወሰኗን በወቅቱ በርካታ ነች ፖለቲከኞች አስታውቀው ነበር።

ይህ የአሜሪካ አቋም ያስጎመጀው ትህነግ ጥሎት የሄደውን አራት ኪሎ ዳግም ለመረከብ መከላከያን በተኛበት በክህደት ከመውጋት ጀምሮ ይሆናል ያለውም ሁሉ አደረገ። ጊዜ ሲጠብቁ የነበሩት ኢሳያስ አፉወርቅ አጋጣሚውን ተጠቅመው በክህደት ከተመታው የኢትዮጵያ መከላከያ ጋር በመሆን ትህነግን ተበቀሉት። ኢሳያስ ሲጠብቁት የነበረው አጋጣሚ በትህነግ የችኮላ ሂሳብ መከላከያን በመተንኮሱ ሳቢያ ተሳካ።

በአትላንቲክ ካውንስል የአፍሪካ ማዕከል ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ብሮንዊን ብሩቶን ይህ ለብዙዎች ደብዝዞ የሚታያቸውን ጉዳይ ግሩም ትንታኔ በመስጠት Ethiopia and Eritrea Have a Common Enemy በሚል ርዕስ ተሟጋች መጣጥፍ በለውጡ ማግስት ማቅረባቸው የሚታወስ ነው። ጽሁፉን እዚህ ሊንክ ላይ ተጭነው ያንብቡ ዓቢይ አሕመድና ኢሣያስ አፈወርቂ በፍጥነት ወደ ሰላም እየተጓዙ ነው፤ ምክንያቱም ለሁለቱም የጋራ ስጋት የሆነ ቡድን አለ፤ አክራሪው የህዝባዊ ትግራይ ሓርነት ግምባር (ህወሓት)።

ወደ ትግራይ አፈግፍጎ የነበረው ትህነግ ዳግም ወደ አፍርና አማራ ክልል በስፋት ሲገሰግስ አሜሪካ መረጃ በመስጠት፣ በዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ሚዲያዎች የኢትዮጵያ መንግስትን ራስን የመከላከል መብት ሲወነጅሉና ሲከሱ ቆይተው፣ ትህነግ አዲስ አበባ ሊገባ ሱሉልታ መድረሱን የሃሰት ምስል በመጠቀም ሁሉ ቢያሰርጩም ያሰቡት ሳይሳካ ቀርቶ ዛሬ ላይ ተደርሷል።

ትህነግም አሜሪካን አምኖ ጉድ እንደተሰራ ይፋ የገባው ጦርነቱ በኪሳራ ወደማብቃቱ ሲቃረብ ” አዲስ አበባ ግቡ፣ ከያዛችሁት ቦታ ልቀቁ …ስትል የነበረችው አሜሪካ ናት” በሚል ምክንያት ሲያቀርብ ነበር።

See also  ሱዳን በኢትዮጵያ ያሉ አምባሳደሯን መጥራቷ ተሰምቷል

የትህነግ ጉዳይ በሰላም መሳሪያ አስረክቦ ዕድሜውን ማትረፍ ብቻ ሆኖ ጦርነቱ አበቃ። በመላው አፋርና አማራ ክልል በትኖ ያስጨረሳቸውን ምስኪኖች መርዶ ነግሮ በመላው ትግራይ የሃዘን ቀን በማወጅ ታሪኩን ሊዘጋ እየሰራ ነው። ትህነግ ለምን ዓላማ የትግራይን ህዝብ እንዳስፈጀ፣ ትግራይን ወደ ሁዋላ መልሶ ህዝቡን ለስቃይ እንደዳረገ፣ በወረራ እስከ ደብረ ብርሃንና የአፋር ሰፊ ክልል እስከ ጎንደርና ባህር ዳር መዳረሻ ምን ፍለጋ እንደመጣ እየታወቀ ” ሰማዕታት” በሚል ማደናገሪያ የሃዘን ቀን የሚያውጀው ትህነግ ቀጣይ ዕቅዱ ባይታወቅም አቶ ጌታቸው እንዳሉት ” አጋጣሚውን ተጠቅመን ወልቃይትን እንያዝ” የሚል ሃይል እንዳለ ሰሞኑንን በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸውን በርካቶች ያሰምሩበታል። ከትህነግ ባህሪ አንጻር ሊመረመር የሚገባ እንደሆነም ያምናሉ።

አሁን የተሰማው አዲስ ጉዳይ ደግሞ እነ ፕሮፌሰር ሕዝቄል ገቢሳ የአቶ ለማ መገርሳን ቡድን ይዘው አቶ ገዱ ከሚመሩት ሃይል ጋር በመሆን “ብልጽግናን ተክተን ሰላም እናወርዳለን” በሚል ሩጫ ላይ ናቸው።

አቶ ለማ ከፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ገቢሳ በተጨማሪ ሄኖክ ገቢሳ፣ የራሳቸው ሰራዊት አደራጅተው የነበሩት የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ባለቤት ድንቁ ደያስ የመሳሰሉትን በማሰባሰብ ለአሜሪካ ሁለት ሴናተሮች ዕቅድ ማቅረባቸውን አንድ ወደ ህብረቱ እንዲገቡ የተጠይቁና ፈቃደና ያልሆኑ ለኢትዮ አስራ ሁለት ገልጸዋል።

አቶ ገዱና አቶ ለማ ቀደም ሲል መልካም የሚባል ግንኙነት እንደነበራቸው ይታወቃል። በኦሮማራ ጥምረት ወቅት መስራች ባይሆኑም ሰፊ ተሳትፎ እንዳላቸውም በይፋ ሲገለጽ ነበር። ሚዲያው በቲፎዞ ከስራቸው በላይ ቢያወራላቸው የማይናቅ ሚና እንደነበራቸው የሚያውቁ እንዳሉት ሁለቱ የቀድሞ የትህነግ ካድሬዎች አብረው እየሰሩ ነው።

በአቶ ገዱ በኩል ያሉትን ወገኖች ለጥንቃቄ ሲባል አሁን ላይ ለመግለጽ እንደሚቸገሩ የገለጹት ክፍሎች ” በአሜሪካን በአደባባ የጋላ መንግስት በሚል መግለጫ ሲያወጡብን የነበሩ አካላት ጋር እነ ለማ ምን ዓይነት ህብረት ነው የሚፈጥሩት የሚለው ጥያቄ ስለጉዳዩ በቂ እውቂያ ባላቸው ኦሮሞዎች ዘንዳ ጥያቄ ሆኗል” ብለዋል።

ትህነግ ወደ ደብረ ብርሃን ሲጠጋ የሽግግር መንግስት ለማቋቋም ከተመለመሉት ዘጠኝ “ድርጅቶች” ውስጥም እዚህ ጥምረት ውስጥ እንዲገቡ የተጋበዙ መኖራቸውን አንድ ነዋሪነታቸው ሚኖሶታ የሆነ የሶማሌ ክልል ተወላጅ ገልጸዋል። እሳቸውም ሃሳቡ ቀርቦላቸው ” እነ አቶ ሙስጣፊ በሶማሊ ክልል በቂ ተቀባይነት አላቸው። እነሱን ማደናቀፍ ለክልሉ አይጠቅምም” የሚል አቋም በመያዝ ለጊዜው “ይለፈኝ” ማለታቸውን አመልክተዋል።

See also  ለማ መገርሳ አዲስ አበባ ተመለሱ፤ ከድርጅታቸው ጋር መቀጠል ይፈልጋሉ

ወልቃይትን ፈርመው አሳልፈው በመስጠት የክህደት ታሪክ የሚነሱት አቶ ገዱ በቅርቡ በመንግስት ሃይሎች ተይዘው ስላካቸው መበርበሩ ተገልጾ በማህበራዊ ሚዲያዎች መዘገቡ ይታወሳል። ጉዳዩ ከዚህ እንቅስቃሴ ጋር ስለመያያዙ እስካሁን ፍንጭ የለም። ይሁንና አቶ ገዱ አዲስ አበባ ሆነው ከእነ ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ጋር ይስሩ ከሌሎች ጋር ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም።

ይህ አሜሪካንን ” ተተኪ መንግስት አድርጊን” የሚለው ጥምረት ምን ያህል የተሳካ እንደሚሆን ባይታወቅም ” አሜሪካ ብልጽግናን እጅ ለመጠምዘዝ ድሮ ያላቻለችውን አሁን ያቻላታል? ክልሎችስ እሺ ይላሉ? አሁን ጥምረት ፈጠሩ የተባሉት ሃይሎችን ብሄር ብሄረሰቦች ከራሳቸው ህልውናና ፍላጎት አንሳር ምን አይነት ስፍራ ይሰጡዋችዋል? በኦሮሚያስ የሸዋና መካከለኛ ኦሮሚያ ተወላጆችን የመግፋቱ አካሄድስ ያዋጣል” የሚሉትና ሌሎች ተመሳሳይ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው።

እነ አቶ ለማ አሜሪካ ከሚገኘው የትህነግ ህዋስ ጋርም ግንኙነት መፍጠራቸው ቀደም ሲል የተሰማ ጉዳይ መሆኑ ነው። እነ አቶ ገዱ፣ አቶ ለማና ትህነግ ከገጠሙ አቶ ለማ ” መፍረስ የለበትም” ያሉት ኢህአዴግ ዳግም መሰራቱ ከሁሉም በላይ አስገራሚ ሆኗል። ግብዣው የደረሳቸውና ያልተቀበሉ እንዳሉት ” ዳግማዊ ኢህአዴግን መመስረት እንዴት ለአማራና ኦሮሞ ፖለቲካዊ አማራጭ ይሆናል?” ብለዋል።

ለመንግስት ቅርብ የሆኑ ወገኖች እንደሚሉት ሁሉም እንቅስቃሴ ይታወቃል። አሁን ላይ በአማራ ክልል የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ በሽግግር መንግስት ማዕቀፍ ወደ ስልጣን ለመምጣት ያለሙ ወገኖችን እነማን እያሰባሰቧቸው እንደሆነ መንግስት ያውቃል ያሉት ወገኖች የመንግስትን አቋም አላብራሩም።


Leave a Reply