ETHIO12.COM

በየማሳ አስከሬን እየተገኘ በመሆኑ ተሰብስቦ በአንድነት እንዲቀበር ከዲያስፖራው ጋር ቀጠሮ ተያዘ፣ ሃምሳ አዳሪ ት/ቤት ሊገነባ ነው

በጭና በተለያየ ቦታ የሚገኘውን አስክሬን ከዳያስፖራው ጋር በመሆን በአንድ ስፍራ የመቅበር ስርዓት ለመፈጸም ዕቅድ መያዙ ተገለጸ። ገበሬው ሲያሽድ፣ ሕጻናትና ሴቶች እንጨት ሲለቅሙ አስከሬን እንደሚያገኙ ተመልከከተ። የትህንግ ሃይል ዘጠኝ ክፍለጦር በአብዛኛው በመደምሰሱ በየቦታው በወጉ ያልተቀበረ አስከሬን በብዛት እንደሚገኝ ተገልጿል።

በሰሜን ጎንደር ዞን፣ ዳባት ወረዳ፣ ጭና ቀበሌ በአሸባሪው ህወሓት ተጨፍጭፈው በተለያየ ቦታ የተቀበረውን አስክሬን በማውጣት ከዳያስፖራው ጋር በመሆን አንድ ስፍራ ላይ የቀብር መርሃግብር እንደሚካሄድ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አስታወቁ።ዋና አስተዳዳሪው አቶ ያለአለም ፈንታሁን በስፍራው ለሚገኙት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች እንዳስታወቁት፤ የአማራ ክልል አስተባባሪ ኮሚቴ ሰሜን ጎንደር ዞንን በተለይ ዳባትንና ደባርቅ ወረዳን ዳያስፖራው እንዲያየው መርሃግብር ይዞለታል፡፡

በዚያን ወቅት ዞኑ ያቀደው ከዳያስፖራው ጋር በመሆን ጭና ላይ በአሸባሪው ህወሓት የተጨፈጨፉ ዜጎችን እና በጦርነቱ ምክንያት ተገድለው በየቦታው የተቀበሩትን አስክሬኖች በማሰባሰብ በአንድ ስፍራ የመቅበር ስርዓት ለመፈጸም ነው፡፡ እርሳቸው እንደገለጹት፤ የአካባቢው ማህበረሰብ ቤቱ የቀብር ስፍራ ሆኖበታል፤ በየደጃፉ ላይ አስክሬን ተቀብሮበታል፡፡

ይህንን ከየቤቱና ከየደጃፉ በመልቀም ወደአንድ ቦታ ለማምጣት በዞኑ ታስቧል፡፡ ይህ ስርዓት የሚፈጸመው ከዳያስፖራው ጋር በመሆን ነው፡፡ ዋና አስተዳዳሪው አቶ ያለአለም እንዳሉት፤ በአሁኑ ሰዓት አርሶ አደሩ እያጨደ ሳለ ድንገት አስክሬን ያገኛል፡፡ ህጻናት ደግሞ እንጨት ሲለቅሙ እንዲሁ አስክሬን ያገኛሉ፡፡ በወቅቱ ጠላት ይዞት የመጣው ዘጠኝ ክፍለ ጦር እንደመሆኑ ከዚህ ውስጥ ደግሞ አብዛኛው ከጠላት ወገን የሆነው በመመታቱ የአስክሬኑ ቁጥር ከፍ ያለ ነው፡፡

ይህንንም ለመቅበር ታስቧል።ዳያስፖራው ጭናን እና ቦዛን ማየት አለበት፡፡ እንዲሁም በጥቅሉ ትግል የተደረገባቸውን አካባቢዎች ማየት ይኖርበታል፡፡ የቀብር ስርዓቱን ጭና ላይ አድርገን ወደ ደባርቅ ወረዳ በመሄድ ቦዛን ደግሞ እናሳየዋለን ብለዋል የዘገበው ኢፕድ ነው።

“ትምህርት ሚኒስቴር 50 ዘመናዊ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ያስገነባል” -ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር

ብርሃኑ ነጋ

ትምህርት ሚኒስቴር በመላ ኢትዮጵያ 50 ዘመናዊ ደረጃቸውን የጠበቁ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት የሚያስችል ፕሮጀክት ማዘጋጀቱን የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ። በትምህርት ቤቶቹ የዲዛይን ዝግጅቱ ላይም ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኀበር ጋር ውይይት እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢንተርኔት አማራጭ የቪዲዮ መልዕክታቸው፤ በኢትዮጵያ 48 ሺህ ትምህርት ቤቶች ቢኖሩም ደረጃቸውን የጠበቁት 0 ነጥብ 01 በመቶዎቹ ብቻ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአጠቃላይም ስድስት ትምህርት ቤቶች ብቻ ናቸው ደረጃ አራት ላይ የሚገኙት። ስለዚህም ኢትዮጵያ ደረጃውን የጠበቀ የአካልና የአዕምሮ ማበልጸጊያ ትምህርት ቤቶች ያስፈልጓታል፤ ለዚህም ደረጃቸውን የጠበቁ አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን መገንባት አለብን ብለዋል።

የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኀበር በበጎ ፈቃደኝነት የትምህርት ቤቶቹን ግንባታ ዲዛይን ለማዘጋጀት ፍቃደኛ መሆኑን የገለጹት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፤ ለዚህ አገራዊ ፕሮጀክት ለመሳተፍ ፍቃደኝነታቸውን ላሳዩ ኢንጂነሮችም ምስጋና አቅርበዋል።

በፕሮጀክቱ አጠቃላይ ዝግጅት በተመለከተ የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኀበር አመራርና አባላት ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የመንግስት መገናኛዎች ዘግበዋል።

የአለውሃ ድልድይ በአዲስ የብረት ድልድይ የግንባታ ስራው ተጠናቆ ለትራንስፖርት አግልግሎት ከፍት ሆነ

May be an image of outdoors

በአሸባሪው የህወሓት ወራሪ ኃይል በፈንጅ እና በከባድ መሳሪያ ሰብሮት የነበረው የአላውሃ ድልድይ የግንባታ ሥራ ተጠናቅቆ ለትራንስፖርት አግልግሎት ክፍት ሆኗል።የአላውሃ ድልድይ ፕሮጀክት ሳይት መሃንዲስ ኢንጂነር ዮሐንስ አያሌው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የአለውሃ ድልድይ በአዲስ የብረት ድልድይ የግንባታ ስራው ከስምንት እስከ አስር ቀናት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ተደርጓል።

እንደ ኢንጂነር ዮሐንስ ገለጻ፤ በተለይ ወደመጨረሻ ቀናት ድልድዩን በመገጣጠምና በማጠናቀቂያ ጊዜ የነበረውን ዝናባማ የአየር ፀባይ በመቋቋም ሥራው በአስረኛው ቀን ተጠናቅቆ ለተሽከርካሪ (ትራፊክ) አገልግሎት ክፍት ማድረግ ተችሏል፡፡የብረት ድልድዩ እስከ 600 ኩንታል ወይም 60 ቶን ድረስ መሸከም የሚችል አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባ ሲሆን አጠቃላይ ርዝመቱ 54 ነጥብ 86 ሜትር መሆኑንን ኢፕድ ዘግቧል።


Exit mobile version