Site icon ETHIO12.COM

በስብሓት ነጋና በሱ የቅርብ ሰዎች ከእስር ቤት ተነጥሎ መፈታት ከአማራ ይልቅ ትልቅ ኪሳራ የሚያደርሰው በወያኔ ላይ ነው

በስብሓት ነጋና በሱ የቅርብ ሰዎች ከእስር ቤት ተነጥሎ መፈታት ከአማራ ይልቅ ትልቅ ኪሳራ የሚያደርሰው በወያኔ ላይ ነው። ከሰራው ወንጀልና ከአማራ ጠልነቱ አንፃር የስብሓት ነጋ ከእስር ቤት መውጣቱ መላው አማራንና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን ማስቆጣቱ የሚጠበቅ ቢሆንም ውሳኔው ወሽመጣቸውን የቆረጠው የተከዜ ማዶ ሰዎች ነው። ህወሓቶች ያልጠበቁት ነገር ስለሆነ ቅስማቸውን የሚሰብር የማይታረቅ መከፋፈልን እንደሚፈጥር በመስጋታቸው ሌሊቱኑ በወሎ እና ጎንደር አዲስ ጦርነት ከፍተዋል። የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ፅሑፍም የሚያመላክተው በወያኔ ጓዳ ሕመም መኖሩን ነው። ከሌሎቹ የወያኔ ሰዎች ጽሁፎች መረዳት እንደቻልነው የስብሃት ቤተሰብ ከሺዎች የህወሓት እስረኞች ተነጥሎ መፈታት ለዛውም በፍፁም ባልተጠበቀ ሰዓት ችግር እንደፈጠረ የሚያሳይ ነው

ለአማራም ሆነ ለኢትዮጵያ ትልቁ ግብ የሕወሓት መዳከም ከተቻለ መክሰም እንጅ አንድ ሐሙስ የቀረው ስብሓት ነጋ ከእስር ቤት መለቀቅ አይደለም። ስብሓት መፈታት ባይገባውም ለአማራ ግን የተለየ ስጋት ሊሆን የሚችል ሰው አይደለም። ፈፅሞ።



ሊያጠፋን በእብሪት የተነሳን ጠላት ማስተንፈስ፣ ማንበርከክ እና እጣፈንታውን በራስህ እጅ ማድረግ መቻልን የሚመስል አሸናፊነት የለም። እንደ ስዩም መስፍን ወይም አባይ ፀሓዬ ገ*ሎ መጣል ይቻል ነበር። ሞት ለማናችንም የማይቀር ፀጋ ስለሆነ እንደ ስብሀት ያሉ ሰዎችን ከመግደል እንዲህ አቆይቶ የራሳቸውን ቡድን ለማዳከም መጠቀሙ ብልህነት ነው።

እምዬ ሚኒሊክ የጣልያን ምርኮኞችን በፈረስ ተንከባክበው የሸኙት ጠላት ስላልነበሩ ወይም ስለማይሆኑ አልነበረም። ንጉስ ጦናንና ንጉስ ተክለሃይማኖትን በከፍተኛ ጦርነት አሸንፈው ምህረት ከማድረግ አልፈው መልሰው የሾሟቸው በጠላትነት ስላልተዋጉ አልነበረም። ማሸነፍ ማለት ትርጉሙ ጠላትን አገልጋይ ማድረግም ስለሆነ ነው። አለም ላይ የተደረጉ ጦርነቶች መጨረሻቸው ድርድርና ሰላም መፍጠር መሆኑን ማንም የሚስተው ጉዳይ አይደለም። በእኛ ሐገር ያለውና ወደፊት የሚኖረውም የጦርነቱ መደምደሚያ አዲስ ክስተት ይዞ ሊመጣ አይችልም። በጦርነት ያሸነፈ አካል ያሸነፈውን እጣፈንታ መወሰን የሚያስችል የአሸናፊነት ማንበርከኪያ ቁልፍን በእጁ ላይ ከማስገባት በላይ አሸናፊነት ወይም የድል ማድመቂያ የለም!

የስብሓት ነጋ መፈታት እንደማንኛውም አማራ ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ክፉኛ ቢያስቆጣኝም ቀጣዩን ወደ መመልከት ተሸጋግሬያለሁ!

Thomas Jejaw Molla – ቶማስ ጀጃው ሞላ]


Exit mobile version