Site icon ETHIO12.COM

በሶማሌ ክልል ከ80 በላይ ወረዳዎች በድርቅ መጎዳታቸው ተገለጸ

በሶማሌ ክልል ዘጠኝ ዞኖች ስር የሚገኙ ከ80 በላይ ወረዳዎች የሚኖሩ ዜጎች በድርቅ መጎዳታቸው ተገለጸ፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ ለተጎዱ ዜጎች እየተደረገ ስላለው አስቸኳይ ድጋፍ አቅርቦት በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ ጂያን ፍራንኮ ሮቲግሊያኖና ለስራ ባልደረቦቻቸው ገለፃ አድርገዋል፡፡

የዩኒሴፍ ተወካይ ጂያን ፍራንኮ ሮቲግሊያኖና በክልሉ የተከሰተውን ድርቅ መቋቋም እንዲቻል ድርጅቱ እና ሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች የበኩላችንን ለመወጣት እንሰራለን ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች አፋጣኝ እርዳታ ለማድረስ የሶማሌ ክልል ካቢኔ አባላት 200 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን በማስታወስ አሁንም ድርቁን ለመቋቋም ከመቼውም ጊዜ በላይ እየሰራን ነው ብለዋል።

የዜጎችን ህይወት ለመታደግ፣ በድርቁ ወቅት የሚደርሰውን የምግብ እጥረት መከላከል እና ግንዛቤ የማስጨበጡ ሥራ ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በአመራሮች ክትትል እየተደረገበት እንደሚገኝ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። (ዋልታ)

አብይ አሕመድ ከፕሬዚዳንት ባይደን ጋር በስልክ መከሩ፤ ዜናው የተለያዩ ስሜቶች ፈጥሯል

የግል ባንኮች ሰባ ከመቶ የውጭ ምንዛሬ ገቢያቸውን ለብሄራዊ ባንክ ገቢ ገቢ እንዲያደረጉ ታዘዘ

Exit mobile version