ETHIO12.COM

አጀንዳ “ጠላት ተከፋፍሏል ይህንን መከፋፈል እንዴት እናስፋው?” ትህነግ

ፋክት ቼክ የት ገባ። ለሃሰተኛ ዜና ስርጭትና መከፋፈልን ለመፍጠር፣ ትናንት የትህነግ ሰራዊት አዲስ አበባ ሊገባ አርባ ኪሎ ሜትር ላይ ደርሷል። ሲሉ የነሩት እነ ሲኤን ኤንና ኤፒ ትህነግ ትጥቅ ሳይፈታና ወታደራዊ ሃይሉ እጅ ሳይሰጥ ምንም ዓይነት ድርድር እንደሌለ በግልጽ በሚታወቅበትና፣ አሜሪካም ይህን ተቀብላ ለተግባራዊነቱ እንዲሰሩ እያሳሰበች ባለችበት ወቅት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትግራይ ሃይሎች ጋር ለመደራደር መዘጋጀታቸው መዘገቡ አንዱ የሃሰት ቅስቀሳው ማበብ ማሳያ እንደሆነ እየተገለጸ ነው።

ኤፒ አጣሞ የሰራውና የቅሰቀሳ፣ የልዩነት ማራቢያ ዜና ትክክለኛ ቃል ይህ ነው። በአጭሩ “ማንኛውም ድርድር ከህወሀት እጅ መስጠት ጋር በተገናኘ ብቻ መሆን አለበት ፣ መንግስት በሰላሙ ላይ ትልቅ እመርታ አድርጓል፣ አሁን ጉዳዩ ያለው ህወሃት እጅ እንደሆነ ይህም ወረራውን ማቆም እንደሆነ፣  ህወሀት ጥሪውን እምቢ እምቢ ብሎ አዲስ ጥቃት ሲጀምር ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ፈጽሞ ማድረስ እንደማይቻል ፣ በተባበረች ኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ ወደፊት ተስፋ እንደሌለው” ማለታቸውን አቶ መስፍን ተገኑ የገለጹት በዚህ መልኩ ነበር።

እንደ አዲስ የዲጂታል ዘመቻው በስፋት መንግስትና ሕዝብን፣ መንስትን እርስ በእርስ፣ ከሎችን ፌደራል መንግስትን … በሁሉም መስክ እንዲከፋፈሉ መስራትና ተፈጠረ ያሉትን መከፋፈል ማስፋት እንደሚገባ በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በኩል መገለጹ ተሰማ።

የቀድሞ የመከላከያ መኮንን ጄነራል አበበ /ጆቤ ለወያኔ ዲጂታል ክፍል በዙም ስልጠና ሲሰጡ የሚያሳየው ቪዲዮ “በጠላቶቻችን መካከል መከፋፈል እንዲፈጠር መስራት አለብን። ይህ ትልቅ ስራችን መሆን አለበት። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ መከፋፈል ተፈጥሯል። ይኼንን መከፋፈል እንዴት እናስፋው?” እያሉ ሲናገሩ ይሰማል።

መንግስት አሁን ላይ ማናቸውንም ጉዳዮች በመደበኛ የህግ አግባብ መቆጣጠር እንደሚቻል በማስታወቅ ለስድስት ወር የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ውሳኔውን ለተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት፣ እስረኞችን እየፈታና ለትህነግ አሜሪካ የተቀበለችው ቅድመ ሁኔታ አስቀምጦ ድርድር በጀመረበት በአሁኑ ወቅት ትህነግ ” ተፈጠረ” ያለው መከፋፈል በዝርዝ አልቀረበም።


ባለፉት 3 ዓመታት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ 49%ው በዲጂታል ወያኔ የተከፈቱ ናቸው

  • መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በወጣው መግለጫ 122,000 ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ ብሏል።
  •  17,000 የሚሆኑ ሀሰተኛ የቲዊተር አካውንቶችም በዲጂታል ወያኔ  ቡድን ተከፍተው ነበር
  • በአንድ ቀን ብቻ 25,000 የሚደርሱ መልዕክቶች በቲውተር ምህዳሩ

ትህነግ የሰሜን ዕዝ ላይ ” መብረቃው” ያለውን ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት በዲጂታል ወያኔና በትሥሥር አብረዋቸው ከሚሰሩ ተከፋይ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ አራማጆች አማካይነት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ከሕዝብ የመነጠል ዘመቻው የተሳካ ውጤት ማስመዘገቡን በስኬት ገምግም ወደ ቀጣዩ እርምጃ ለመዛወር የሚያስችለው ደረጃ ላይ መድረሱን ገምግሞ እንደነበር ይታወሳ።

የመከላከያ ትልቁ ሃይልና ከፍተኛ ቴክኖሎጂ የሚጠቅምባቸው መሳሪያዎቹ በአማራ ክልል ሱዳንና በሰሜኑ ግንባር አቅጣጫ ማስፈሩ፣ መንግስት በቂ ሃይል ባልነበረው ወቅት እንኳን “ቀይ ምስመር” ብሎ ያለውን ሃይል በዛ በኩል አከማችቶ መቆየቱን ጀነራል አበባው ታደሰ በይፋ ሲያስረዱ እየተሰማ አዲስ ለተጀመረው ቅስቀሳ ሰለባ ለመሆኑ የሚጣደፉ መኖራቸው አሳዛኝ እንደሆነባቸው ታዛቢዎች ይናገራሉ።

በተለይም በአማራ ክልል በተወሰኑ ግለሰቦች ሆነ ተብሎ የሚሰራጩ የልዩነት መረጃዎችን ማስፋት እንደሚገባ ነው በትህነግ በኩል እየተነገረ ያለው። ትህነግ በአማራ ክልል ካሉት የውስጥ አርበኞች ጋር የዘረጋው መረብ በስፋት እንዲነቃቃና ቀድሞ ወደነበረበት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እንዲያድግ ተወስኖ እየተሰራ መሆኑ ተሰምቷል።

በዚሁ መሰረት ወልቃይትና ራያ በህግ ለትህነግ እንዲሰጥ መንግስት መስማማቱ፣ በድርድሩ ትህነግ ተመልሶ ወደ መንግስት ሃላፊነት እንዲመጣ መንግስት መስማማቱ በስፋት እንዲሰራጭ “የልዩነት ማዕዘን” እንዲሆኑ መባሉ ታውቋል። ከዚህ ዘመቻ አጋሮች ጋር ግንኙነት ያላቸው እንዳሉት ” መንግስት ኮሎኔል ደመቀን ጠርቶ ወልቃይትን ለማስረከብ ተዘጋጁ” በሚል መመሪያ እንደተሰጣቸው ተደርጎ በስፋት እንዲወራ አቅጣጫ ተቀምጧል።


“ከትግራይ ሃይሎች ጋር ድርድር” አቶ መስፍን በኤፒ ከማሳበቅ በአገር ቤት ሚዲያ ለምን ይፋ አይናገሩም?

  • ጋዜጠኛዋ ስለ ጦርነቱ ባላት አቋም ሳቢያ አንሻፋ አቅርበዋለች” ሲሉ አቶ መስፍን ተናግረዋል።
  • ማንኛውም ድርድር ከህወሀት እጅ መስጠት ጋር በተገናኘ ብቻ መሆን አለበት ፣ መንግስት በሰላሙ ላይ ትልቅ እመርታ አድርጓል፣ አሁን ጉዳዩ ያለው ህወሃት እጅ እንደሆነ ይህም ወረራውን ማቆም እንደሆነ፣  ህወሀት ጥሪውን እምቢ እምቢ ብሎ አዲስ ጥቃት ሲጀምር ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ፈጽሞ ማድረስ እንደማይቻል ፣ በተባበረች ኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ ወደፊት ተስፋ እንደሌለው

በአሜሪካን ኢትዮጵያን ፐብሊክ አፌይርስ ኮሚቲ ሊቀመንበር /chairman of the American Ethiopian Public Affairs Committee ሊቀመንበር አቶ መስፍን ተገኑን ጠቅሶ ኤፒ ” መንግስት ከትግራይ ሃይሎች ጋር እደራደራለሁ አለ” ሲል እንደዘገበው የሃሰት ዜና ወደፊትም በትሥሥር ሃሳተኛ ፎቶና ቪዲዮ ካማቀናበር የሚጀምር መረጃ እንደሚበተን ለማወቅ ተችሏል።

ቀደም ሲል የነበረውን የመደራደሪያ አቅም አሟጦ በመጨረሱና ያለውን ሰራዊት በትኖና ትጥቅ አስረክቦ ለድርድር እንዲቀመጥ የተወሰነበት ትህነግ፣ አዲስ የከፈተውን ጦርነት ተከትሎ ” መንግስት የአፋር ክልልን ከዳ” የሚለው ዘመቻ አብሮ መጀመሩ ያስገረማቸው ” ትህነግ በአፋር ንጹሃን ላይ ጦርነት ሲከፍትና 200 ሺህ ሃይል ሲያፈናቅል፣ በተመሳሳይ ‘አፋር ተከዳ’ የሚለውን አጀንዳ እንደተከለ የተረዳ የለም። መንግስት ድሮኑ፣ መከላከያው፣ ሁሉም ሃይሉ በጁ ሆኖ ሳለ ለምን ታገሰ፣ ከክልሉ አመራሮች ጋር ምን ተወያየ? ትህነግ ከዚህ ጦርነት ምን ያጣውን ነገር ለማግነት አሰበ?” የሚሉት ጉዳዮች ሊመረመሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ዲጂታል ወያኔ ዳግም ተጠናክሮ ሃሰት መርጨት ሊጀምር እንደሆነ ያመለከቱ፣ በርካታ የፕሮፓጋንዳ ማሽኖችም ዘመን ” ጋዜጠኛ” አድርጓቸው ከእስር ተፈተው ይህንኑ የክፍያ ዘመቻ ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል። “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምን ይዘምታሉ” በማለት ለቅሶ የቀራቸው ተከፋይ የሚዲያ ፊት አውራሪዎች ቀጣይ ዘመቻ የሚታይ ቢሆንም ” አገር ለማፈራረስና ሕዝብን ለማተራመስ ተግተው የሚሰሩ እነዚህ ተከፋዮችን ህዝብ ራሱና መንግስት በቅርብ ሊከታተላቸው ይገባል” ሲሉ መረጃ የሰጡን አስታውቀዋል።


Exit mobile version