Site icon ETHIO12.COM

ዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ዳያሊሲስ ማዕከል ግንባታ ተጠናቀቀ

በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የከተማ አስተዳደሩ ያስገነባው የዳያሊሲስ ማዕከል ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የማድረግ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ሰላሳ የዳያሊሲስ ማሽኖች የሚኖሩት ማዕከሉ የህፃናት ማቆያ ክፍል፣የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣የቀዶ ጥገና ክፍል፣የሀኪሞች ክፍል፣የታማሚዎች ክፍል፣ለይቶ ማቆያ ክፍል እንዳለው ተጠቁሟል፡፡እንዲሁም ሀኪሞች ታካሚዎቻቸውን በቅርበት የሚከታተሉበት ነርስ ስቴሽን ያለው ሲሆን ደረጃውን የጠበቀ የመፀዳጃ ቤት እንዲሟሉለት ተደርጓል ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት ለ ሰላሳ ታካሚዎች አገልግሎት የመስጠት አቅም ያለውና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀው ይህ ማዕከል አሁን ላይ የሲቪል ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡በቀጣይም ማሽኖቹ ተገጥመው ወደሙሉ አገልግሎት ሲገባ ለኩላሊት ታካሚዎች ከፍተኛ እፎይታን ከመስጠቱም ባለፈ የከተማችንን የህክምና ቱሪዝም መዳረሻነት ጉዞ ያፋጥናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከከንቲባ ፅ/ቤት የተገኘ መረጃ ጠቅሶ ኢዜአ አመልክቷል።

Exit mobile version