Site icon ETHIO12.COM

የማዕከላዊ ስታትስቲክስ አገልግሎት የመረጃ ባንክ – ዳታ ቤዝ ስርዓት አልዘረጋም ተባለ

ይህም ማለት በየዘርፎቻቸዉ የሚያስተባብሩ የመንግስት አስፈጻሚ አካላት የመረጃ ቋት በቅንጅት የሚሟላበትን ስርዓት እና የሚተሳሰሩበትን ስርዓት አለመዘርጋቱን ያሳያል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ አገልግሎት የዘላቂ ልማት ግቦች የ2012/13 የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት በገመገመበት ወቅት ኤጀንሲዉ የመረጃ ባንክ /ዳታ ቤዝ/ ስርዓት አልዘረጋም የተባለ ሲሆን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ምላሻቸዉን ሰጥተዋል ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ የሃገሪቱን የዘላቂ ልማት ግቦችን የማስተባበር፣ የመምራት ፣ የመገምገም እና አጠቃላይ ሁኔታዎች ሪፖርት የሚያቀርበዉ የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሲሆን የኛ ሃላፊነት ደግሞ የስታትስቲክስ መረጃ አቅርቦትን በሚመለከት ብቻ ነዉ ብለዋል፡፡

ይህም በ3 ዓይነት መንገድ የሚካሄድ ሲሆን አንደኛዉ የመረጃ ምንጫቸዉ ያልታወቀዉን በናሙና ጥናት ፣ አጠቃላይ ቆጠራ በማካሄድ እና ከአስተዳደራዊ መዛግብት ዉስጥ መረጃዎችን በመሰብሰብ ጥራቱንም በማረጋገጥ የምንሰራ ሲሆን በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ስርዓት ዉስጥ አገልግሎቱ የማይቆጣጠራቸዉ የተለያዩ ተቋማት አሉ የነዚህንም እኛ ጥራታቸዉን ከመቆጣጠር ዉጭ ሌላ መረጃ አንሰበስብም ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ቋሚ ኮሚቴዉም የመረጃ ምንጭ ተብለዉ ከተለዩ 50 ሴክተሮች የ 45ቱ መረጃ የኦዲት ሪፖርቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ አለመሰብሰቡ ለምን እንደሆነ ባነሳው ጥያቄ ምላሽ ተሰጥቶበታል ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ምላሽ ሲሰጡ በዋናነት የአቅም ችግር መሆኑን አንስተዋል የአቅም ችግሩ ከሰዉ ሃይል ፣ ከቴክኒክ ወይስ ከፋይናንስ ለሚለዉ ጥያቄ ግን በቂ ምላሽ አልሰጡም፡፡

Via ethio FM 108 እስከዳር ግርማ

Exit mobile version