ETHIO12.COM

ደቡብ ጎንደር ድንገት ተኩስ ከፍተው እስረኛ ካስለቀቁት ውስጥ 16 ሲገደሉ 20 ተማርከዋል

የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር በዞኑ ተደራጅተውና ታጥቀው በድንገት ተኩስ በመክፈት ማረሚያ ቤት ወረው በህግ ጠለላ ስር ያሉ እስረኞችን ለማስፈታት በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ አስራስድስት ሽፍቶች መገደላቸውንና ሃያ መማረካቸውን አስታወቀ።

“በፋኖ ስም የሚነግድ የተደራጀ ቡድን ድንገተኛ ተኩስ ከፍቶ የሕግ ታራሚዎችን አስመልጧል። ከፍተኛ ዝርፊያ ፈጽሟል” ሲሉ  የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት በጋራ መግለጫ መስጠታቸው ይታውሳል።

የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ደጀኔ ለሬድዮ ጣቢያው እንዳሉት ትናንት ሌሊት ስምንት ሰዓት ነፋስ መውጫ ማረሚያ ቤትና ሌሎች ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች እስረኛ ለማስፈታት ከሞከሩት ዘራፊ ታጣቂዎች መካከል አስራስድቱ ሲገደሉ ሃያ ተማርከዋል። ከመንግስት በኩል ደግሞ ሶስት የፀጥታ አካላት መቁሰላቸውን ገልጸዋል።

አቶ ጥላሁን ተደራጅተውና ታጥቀው የመጡት ዘራፊዎች ከተለያዩ አጎራባች ዞኖች የተሰባሰቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።ከማረሚያ ቤት እንዲወጡ ከተደረጉት ታራሚዎች መካከል ስልሳአምስቱ በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳና በደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንት ወረዳ በተውጣጡ ጥምር የፀጥታ አካላት ቅንጅት ባካሄዱት ኦፕሬሽን በያሉበት ተይዘው ወደማረሚያ ቤት እንዲመለሱ መደረጋቸውን አቶ ጥላሁን ተናግረዋል።


የተደራጀ ቡድን ድንገተኛ ተኩስ ከፍቶ የሕግ ታራሚዎች ማስመለጡን እና ዝርፊያ መፈጸሙ ተገለጸ

ኮሚሽኑ መረጃ እንደደረሰው ከዞኑ የጸጥታ አካላትና እና የፖለቲካ መሪዎች ጋር በመተባበር የኦፕሬሽን እና የወንጀል ምርመራ ቡድን በማሰማራት


Exit mobile version