Site icon ETHIO12.COM

ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ማህበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ የትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ

ትምህርት ሚኒስቴር “ኑ የፈረሰውን የትውልድ ማፍሪያ ተቋም መልሰን እንገንባ !” በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ ለማድረግ ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በወራሪው የህወሃት የሽብር ቡድን ምክንያት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን በተሻለ ደረጃ ለመገንባት መታቀዱን በመግለፅ ማህበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

በአፋርና አማራ ክልል 1,090 ትምህርት ቤቶች ወድመዋል ያሉት ሚኒስትሩ እነዚህን ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ማህበረሰቡ በ9222 አጭር የፅሁፍ መልዕክት የሚችለውን የብር መጠን ፅፎ በመላክ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የተለያዩ የትምህርት ግብዓቶችን ማቅረቡ የሚፈልጉ የህብረተሰሰብ ክፍሎችም 4 ኪሎ በሚገኘው የትምህርት ሚኒስቴር ዋናው ቢሮ በመምጣት ድጋፈ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

የኢትዮ-ቴሌ ኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬ ህይወት ታምሩ በበኩላቸው በቀጣይ ትውልድ ግንባታ ክፍተት እንዳይፈጠር የወደሙና የፈረሱ ትምህርት ቤቶችን በፍጥነት ጠግኖ ወደ ስራ ማስገባት እንደሚበ አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮ-ቴሌኮም ከዚህ ቀደምም ለትምህርት ተቋማት በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ ሲያርጉ መቆየቱን ጠቁመው በአጋርነት የሚያደርገውን ድጋፍ ለወደፊቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የህወሃት ሽብር ቡድን በፈጻሙ ወረራ 1090 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ የወደሙ ትምህርት ቤቶች በትምህርት ሚኒስቴር የሚገነቡ ሲሆን በከፊል የወደሙና ጥገና የሚያስፈልጋቸው 3300 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በክልል ትምህርት ቢሮዎች ይገነባሉ ተብሏል፡፡

Exit mobile version