ኦሮሚያ ለአማራ ክልል መቶ ሚሊዮን ብር ሰጠ፤ “ኑ የወደመውን የትውልድ ማረፊያ ተቋም አብረን እንገንባ”ዘመቻ በይፋ ተጀመረ

  • 1 ሺህ 90 የትምህርት ተቋማት ሙሉ በሙሉ ሲወድሙ ሶስት ዩኒቨርሲትዎችና ሶስት ኮሌጆችም ተመሳሳይ እጣ ገጥሟቸዋል።

የኦሮሚያ ክልል በአማራ ክልል ለደረሰው ጉዳት የሚውል የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ። የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የገንዘብ ድጋፉን ለአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ አስረክበዋል።

አሸባሪው ህወሃት በአማራና አፋር ክልሎች በወረራ በቆየባቸው አጋጣሚዎች በድምሩ 1 ሺህ 90 የትምህርት ተቋማት ሙሉ በሙሉ ሲወድሙ ሶስት ዩኒቨርሲትዎችና ሶስት ኮሌጆችም ተመሳሳይ እጣ ገጥሟቸዋል። በመሆኑም የትምህርት ተቋማቱን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ሁሉም ድጋፉን እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

አሸባሪውን ቡድን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት መመለስ መቻሉ የኢትዮጵያውያን ሃያልነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚሁ ወቅት ገልፀዋል። በዚህም በክልሉ ለደረሰው ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት ለመመለስ ለሚደረገው ጥረት የጀመርነውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ በበኩላቸው ጠላቶቻችንን ማሸነፍ የምንችለው አንድነታችንን በማጠናከር ነው ብለዋል።

በሌላ ተመሳሳይ ዜና በአሸባሪው ህወሃት የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የፅሁፍ መልእክት እና በባንክ አካውንት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተጀመረ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በአሸባሪው ህወሃት ውድመት የደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመገንባት የሚያስችለውን የገቢ ማሰባሰቢያ የጋራ ሥምምነት ተፈራርመዋል። በሥምምነቱ መሰረት በ”9222″ ላይ ቴሌ ብርን ጨምሮ ማንኛውም አካል ከአንድ ብር ጀምሮ አጭር የፅሁፍ መልእክት በስልክ በመላክ ድጋፉን ማድረግ እንደሚችል ተጠቁሟል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000448700945 አካውንት በመጠቀም ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻል ተገልጿል።

አሸባሪው ህወሃት በአማራና አፋር ክልሎች በወረራ በቆየባቸው አጋጣሚዎች በድምሩ 1 ሺህ 90 የትምህርት ተቋማት ሙሉ በሙሉ ሲወድሙ ሶስት ዩኒቨርሲትዎችና ሶስት ኮሌጆችም ተመሳሳይ እጣ ገጥሟቸዋል። በመሆኑም የትምህርት ተቋማቱን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ሁሉም ድጋፉን እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

የትምህርት ግብቶችን ድጋፍ ለማድረግ የሚፈልጉ አካላት ደግሞ በትምህርት ሚኒስቴር ዋናው ቢሮ በመገኘት ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል። የገቢ ማሰባሰቢያው “ኑ የወደመውን የትውልድ ማረፊያ ተቋም አብረን እንገንባ” በሚል መሪ ኃሳብ ነው የሚካሄደው።

Related posts:

«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
መንግስት የኑሮ ወድነትን ለማሻሻልና የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ተከታታይ እርምጃ አንደሚወስድ ተገለጸ
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ጋብቻ ሳይፈፀም እንደባልና ሚስት መኖር እና የሚያስከትለው ውጤት
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ

Leave a Reply