Site icon ETHIO12.COM

ከሳኡዲ «ሀቁን ከመንግሥት ችግር ጋር ለይቼ ምንም ሳልደብቅ ልንገራችሁ»

የተደበቀው የእስረኞች ጉዳይ መንግስት ከፈራችሁ እኔ ልንገራችሁ !
.
እስረኞቹ ከፈጣሪ በታች ይታደጋቸዋል የተባለው ሙከራ የመክሸፍም እድል ሊኖረው ይችላል። ወይም እድለኛ ሆነው የተሻለም ውጤት የማምጠት እድል ያስገኘን ይሆናል። እርግጠኛም ሁኑ አትሁኑምም እዚህ ላይ ጥሬ ሀቁን ከመንግሥት ችግር ጋር ለይቼ ምንም ሳልደብቅ ነው የምነግራችሁ።
.
ልኡካን ቡድኑ የመጣበትን ስራ በተሻለ መንገድ ሰርቷል። ጉዳዩ ግን ከሉኡካን ቡድኑ የገዘፈ ሆኖ ቀርቧል። የኛ መንግስተና የሳኡዲ መንግስት ፍላጎቶች ተመሳሳይነት ቢኖራቸው የነሱ የፀና አቋም የኛ መንግስት ከነሱ የሚፈልገውን ነገር ሊገራው አልቻለም።

ልብ በሉ፣ ይችን ጥሬ ሀቅ የምነግራችሁ እኔም ካለብኝ የህሌና ጥያቄ ነፃ ለመውጣት፣ ሚሊየኖች ለሚጠይቁትና ግራ ለገባቸው፣ ምናልባትም ደፍረው ለመናገር ለተቸገሩ ሰዎች መፍትሔ ይሆናል ብየ ስላመንኩበት ነው ይሄንን ሚስጥር ወደ አደባባይ ያወጣሁት።
.
ውይይቱን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አቀዋለሁ። መሉ የውይይቱ ጉዳይ ከኔ በላይ ያሳለጠው ሰው የለም። ከውይይቱ ተሳታፊ ሉኡካኖች በስተቀር። ይሄንን የምለው ምናልባት ለያዝነው አቋምና ለምናደርገው ንቅናቄ ይጠቅማል ብየ ስለማስብ ነው። የስደተኞችን ጉዳይ በተመለከተ ብቻ ነው የምፅፈው። ሌሎቹን ጉዳይዎች አይመለከተኝም።

መንግስት እስረኞች ወደ አገር እንዲገቡና ከገቡ ቡኋላ በሀገራቸው የሚቋቋሙበትን መንገድ ለማመቻቸት አስቦ ነበር ሉኡኩ ከሳኡዲ መንግስት ጋር እንዲመክር የላከው። ምክክሩም በጥሩ ሁኔታ ተካሄደ።
በምክክሩ ላይ የእነሱና የኛ መንግስት ፍላጎት አልተጣጣም። በጥቅሉ ሳኡዲ በሀገሯ የሚኖሩ ህገወጥ ኢትዮጵያውያንን ለማሶጣት ሙሉ በመሉ ወስና ነው ወደመድረክ የቀረበችው። አጠቃላይ የህዝቡ ብዛት ከግማሽ ሚሊየን እንደሚበልጥ ነው ያሳወቀችው።
.
ይህ ግማሽ ሚሊየን ህዝብ ከዚህ አገር ሲገባ፣ ብዛት ያለው ቁጥር የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ነው። ይህ ክፍል በጦርነት የሚታመስ አደገኛ የኢኮኖሚ መድቀቅ ያጋጠመው የሀገራችን ክፍል ነው። ሄደው ሊኖሩ አይደለም። ተመልሰው ሊመጡ ነው። ምክኒያቱም እነዚህ ሰዎች አገራቸውም ያለው ሀብት የወደመ ሲሆን እዚህም አገር ምንም ነገር የላቸውም። ግዴታ የሚቋቋሙበት ነገር ይፈልጋል።
.
ጦርነት ያደቀቀው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፣ እነዚህን ስደተኞች የማስተናገድ አቅም የለውም። ስለዚህ ኢትዮጵያ ይሄንን ከሳኡዲ ጋር በትብብር ለመስራት ጠይቃለች። ሳኡዲ በበኩሏ፣ ገና መክሬ አሳውቃችኋለሁ የሚል መልስ ሰታለች። እስካሁን እየጠበቅን ቢሆንም ምንም መልስ አልሰጡም። እኔም ከዚህ በፊት ጥሩ ነገር አለ ጠብቁ ብየ የተናገርኩት ይሄንን ተስፋ በማድረግ ነበር።
.
ሌላው የእስረኛ አያያዝን በተመለከተ እንዲያሻሽሉ ተጠይቀው እናሻሽላለን ብለዋል። ምናልባት የተጀመረ ስራ ሊኖር ይችላል። እሱ አይታወቅም።

ሦስተኛው የተነሳው ጉዳይ እስርቤት ካሉት ውጭ ያሉትን ኢትዮጵያዊያን ለጊዜው የመያዝ ስራው እንዲቆም ሉኡካን ቡድኑ ጠይቆ ነበር። ሳኡዲ ግን አይሆንም ብላለች። ህግ የጣሰን አካል በህግ ቁጥጥር ስር አድርጌ ደህንነቴን አረጋግጣለሁ፣ ከጎረቤት አገር የየመን አማፂዎች ጋር ለገባንበት ጦርነት የናተን ሰዎች ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። ሲጠቀሙባቸውም አግኝተን ይዘናቸዋል። ከፈለጋችሁ ማሳየት እንችላለን ብለው እመድረኩ ላይ ተከራክረዋል። ስለዚህ ሳኡዲ አሁንም ቢሆን ማንኛውንም በሀገሯ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንንም ይሁን ሌላ ዜጋ መያዟን ትቀጥላለች ማለት ነው።
.
የስደተኞቹ ጉዳይ ያለው እውነታ ይሄ ነው። አሁን እኛ ምን እናድርግ ? በመንግሥት ላይ ብቻ የምናሰማው የስደተኞች ድምፅ፣ አገራችን ከገባችበት ጦርነት ጋር ተያይዞ ግማሽ ሚሊየን ኢትዮጵያዊያንን የመቀበል አቅም አላት ወይ ? ኢኮኖሚያዊ አቅማችን ይችላል ወይ .? እንዴት እናድርገው ብለን እራሳችንን እንጠይቅ። ለመንግሥት ያስቸገረው ነገር ምንድነው.? በዚህ ዙሪያ መንግስትስ ለምን ሀቁን እየሸሸ ዙሪያ ግጥምም ይሄዳል ብለን ወደ ውስጣችን ጠለቅ ብለን መጠየቅ አለብን።
.
ከላይ እንደነገርኳችሁ ሳኡዲ ኢትዮጵያውያን
ህገወጥ ኗሪዎች ከሀገሯ በአንድ ቀን ቢለቁ ደስተኛ ናት። ከነሱ ምንም ችግር የለባቸውም። ችግሮቹ ከኛ ናቸው። የኛ ችግር ደሞ ያለንበት ወቅታዊ ሁኔታ ነው። እነሱ እኛ ያለንበትን ወቅታዊ ሁኔታ አይተው ለመረዳት አልሞከሩም። ለኡኩ የተላከውም ይሄንን አላማ ይዞ ነበር። ግን አልተሳካለትም። ስለዚህ አሁን ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ንቅናቄ እያደረግን ነው። ይሄንን ከማድረጋችን ጎን ለጎን ለኛ የተቸገረውን የኢትዮጵያን መንግስት እንዴት እንርዳው.?
እንደነገርኳችሁ፣ ሳኡዲ ውስጥ ያለው ስደኛ አብዛኛው የሰሜኑ ክፍል ነው። ወሎና ትግራይ ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ። ኦሮሚያ ጅማና አርሲ ሀረርጌ፣ ከደቡብ ትንሽ የተወሰነ ህዝብ ነው ያለው። ይህ የስደተኞች ግምታዊ ስሌት ነው። ከዚህ በፊት በሰራናቸው ስራዎች ያገኘናቸውን የስደተኞች ዶክሜንት መሰረት አድርገን የወሰድነው ግምት ነው።

ጥያቄው ስደተኞቹን የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ሀገራቸው ቢያስገባቸው፣ የሰሜኑ ክፍለ ገቢዎች ምን ሊሆኑ ነው። ተመልሰው ወደ ስደት እንደሚመጡ ምንም ጥርጥር የለውም። መንግስትም ይሄንን በደንብ ያቃል። ለሳኡዲ መንግስትን ይሄንን ቃል ተናግሯል። እንዳይመለሱ የሚቋቋሙበት ነገር ላይ ከመንግሥት ጋር አብረን እንሰራለን ቢሉም መልሱ መቸ እንደሚመጣ አልታወቀም። በዚህ መሀል እነሱም እያደኑ መያዛቸውን አላቆሙም።
.
የመንግስት ችግሩ ዝም ማለቱ ነው፣ መንግስት አሁንም ቢሆን ነገሮችን ከመደባበቅ ወጥቶ ያለውን ሀቅ ፊትለፊት በማሳወቅ ህዝቡ እንዲረዳው ማድረግ አለበት። ዝምታውን ተከትሎ በመንግሥት ላይ ለሚመጡ ጥያቄዎች ሀላፊነት የሚወስደው እራሱ መንግስት ነው። እኛ በግል እንዲህ ደፍረን የፃፍነው ምናልባት ያለውን ሀቅ ተናግረን ህዝቡ በመረጃ ላይ ተደግፎ ለልጆቹ መፍትሔ እንዲፈልግ ከማሰብ አንፃር እንጅ፣ ሚስጥር ጠባቂ መሆን አቅቶኝ አይደለም።

Suleman Abdela

Exit mobile version