Site icon ETHIO12.COM

መስቀል አደባባይ ፕሮፋይሉ ነው፤ ሊንኩ ግን ወያኔ ነው

መስቀል አደባባይ በትውፊት የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይዞታና የአዲስ አበባ ኦርቶዶክሳውያን የደመራ በዓል ማክበርያ አደባባይ ነው ። ነገር ግን በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዐት መሠረት የሥርዐተ አምልኮ ማስፈጸምያ ቤተ ክርስቲያን ግን አይደለም።

የመስቀል አደባባይ ክርክር የነገረ ድኅነት (ነገረ መስቀል) ክርክር የሚያደርጉ አዲስ ክርስቲያኖች ይገርሙኛል ፣ ክርክሩ የዜግነት ክርክር መሆኑ መዘንጋት የለበትም ። የዜግነት ክርክር ከሆነ ደግሞ ትውፊታዊ ይዞታነቱ የኦርቶዶክስ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ውይይቱ ሃይማኖት ሳይለይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ሁሉ ይመለከታል ። #ከኦርቶዶክስ ውጭ ላሉ አማኞች የአደባባይ መርሐ ግብር የሚያደርጉበት አማራጭ መፍትሔ ከተገኘ ጥሩ ነበር። አማራጭ መፍትሔ ካልተገኘ ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያውያን መርሐ ግብራቸውን በመስቀል አደባባይ አድርገው ቢገለጉሉበት ኃጢአትነቱ አይታየኝም ። ስለሚያደርጉበት ሁኔታና አፈጻጸም ላይ ስምምነት መፍጠር ግን ይቻላል ። ይህንን የሚደግፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አለን ፤ ነገር ግን ይህን የሚቃወም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የለንም ። (የሐዋ.ሥራ 17 ላይ የአርዮስፋጎስ አደባባይ አገልግሎትን ይመልከቱ)

ለምን ይዋሻል ???

በውጭው ዓለም አብዛኛዎቻችን ኦርቶዶክሳውያን የራሳችን ቤተ ክርስቲያን እስኪኖረን ድረስ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን ወይም የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያንን ተከራይተን ወይም በችሮታ አግኝተን ከካቶሊክ ወይም ከፕሮቴስታንት ቀጥሎ ወይም በቅድምያ በሰዓት ልዩነት በፈረቃ እያመለክን አይደል ??? ምነው ታድያ በሀገራችን በሀገራቸው ኢትዮጵያውያንን ማግለል ለምን አስፈለገን ???

“መስቀል አደባባይ የኦርቶዶክስ ይዞታ ሲሆን የሌሎች ኢትዮጵያውያን ሁሉ አደባባይ ነው “በሚለው መስማማት ያለብን ይመስለኛል ። ከይዞታ ጋር በተያያዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ስያሜው እንዲጠበቅላት ፣ አደባባዩ ደግሞ የገንዘብ ጥቅምና ገቢ የሚያስገኝ ከሆነ ሕግ እስከፈቀደላት ድረስ የጥቅም ተካፋይ እንድትሆን መደራደርና መወያየት ትችላለች ።
ከዚህ ባለፈ እንደቫቲካን ኢትዮጵያን በፍትሐ ነገሥት የምትተዳደር ማስመሰል የትም አያደርሰንም ፤ በአሁኑ ግዜ እንኳን ሀገር በፍትሐ ነገሥት የሚመራ ጳጳስ የለም ፣ በዚህ ምክንያት ጳጳሳቱ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ብለው የራሳቸው የቃለ ጉባኤ ስምምነት እንጅ ከፍትሐ ነገሥቱ ጋር ከተቆራረጡ ቆይተዋል ።

ጎበዝ !!!

አሁን የተቸገርነው በቢሮ አሠራር የሚፈታ የመስቀል አደባባይ ጉዳይን የፓለቲካ ጉዳይ የሚያደርጉ ዲጅታል ወያኔዎች ቤተ ክህነቱን እያዋከቡት ስለሆነ ነው ። ጉዳዩን መቀሌ ካለው ስውር አንጃ ጋር እንደሚገናኝ የሚያውቅ ሰው ያለ ግን አይመስልም ፤ በተለይ ምእመናን አልተረዱትም ። ወያኔ ከመቀሌ ሆኖ አንዳንድ “ባለትዳር ጳጳሳትን” በርኲሰታቸው እያሸማቀቀ ጠበል እንደገባ ጸበልተኛ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ የፓለቲካ እንዲሆንለት ያስለፈልፏቸዋል ።

ወገኔ ንቃ !!!!

የብሔርና የሃይማኖት ግጭት ለማስነሳት መስቀል አደባባይ ፕሮፋይሉ ነው፤ ሊንኩ ግን ከሰሜን ወያኔ ነው ። ከቤተ ክህነት ደግሞ ፓለቲካው ያጠለላቸው አቅመ ቢሶች፣ ኮንዶሚንየም ጠይቀው አይሰጣችሁም የተባሉ የአምልኮ መልክ ያላቸው የሜዳ ቄሶች ፣ ከቤተ ክህነት ውጭም መሠረታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርት የሌላቸውና መዋቅር ውስጥ የሌሉ “አቶዎች” እንዲሁም ከተከፈላቸው ለወያኔ ብቻ ሳይሆን ለሰይጣንም የሚሠሩ ጥቅመኞች የብሔርና የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር የተሰለፉበት ነው ።

እነዚህ ሰልፈኞች ከዲጂታል ወያኔ ጋር በመተባበር በቢሮ አሠራር የሚፈታውን የመስቀል አደባባይን ጉዳይ ኾን ብለው አዲስ አበባ ላይ “የኦርቶ አማራና የኦርቶ ኦሮሞ” በሚል ስያሜ ግጭት ለማስነሳት በማኅበራዊ ሚድያ እየተውተረተሩ ነው።

እነዚህ ግጭት ጠማቂዎች በግጭቱም መሀል ወያኔን አዝሎና በመካከል አሾልኮ አዲስ አበባ ለማስገባት የጊዜ ሰሌዳ ነድፈዋል ፤ ወያኔ ቆዳውን የሃይማኖት አድርጎ “ሰሜናውያን” በሚልና በልዩ ልዩ ኢመደበኛ አደረጃጀት ማኅበራትን ፈጥሮ “ኦርቶ አማራ” ባለው ስውር አደረጃጀት ውስጥ ራሱን ሸሽጓል ፤ ባጠቃላይ ምንም ይሁን ምን የሃይማኖት ግርግርና ግጭት ከተነሣ ወያኔን አዲስ አበባ ለማስገባት የተጀመረ ኅቡእ አደረጃጀት ቤተ ክህነቱን እየናጠው ነው ።

ኦርቶዶክሳዊ ወገኔ ንቃ !!!

የመስቀል አደባባይ ጉዳይ የባሕር ዳር ጉዳይ አይደለም፣ ወይም የወለጋ ጉዳይም አይደለም ፣ ወይም የአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይ አይደለም፣ የሲኖዶስም ጉዳይ አይደለም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉዳይም አይደለም ፣ ጉዳዩ የሚመለከተው በአዲስ አበባ ያሉ የሌሎች ቤተ እምነቶችን አስተያየት ባካተተ መልኩ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትንና የአዲስ አበባ መስተዳድርን ብቻ ነበር። የመስቀል አደባባይን ጉዳይ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደረጃ መፍታት ይቻል ነበር ። ነገር ግን ጉዳዩን በሲኖዶስ ደረጃ ማድረጉ ለማያዳግም ውሳኔ ይረዳል በሚል ታስቦ ሊሆን ይችላል ። በአንጻሩ ግን ጉዳዩ በሲኖዶስ ደረጃ በመታየቱ ምክንያት የሃይማኖትና የብሔር ግጭት ለማስነሳት ስውር የወያኔ ተልእኮ ያላቸው ቡድኖች ጉዳዩን እያጋነኑ ሀገራዊ የብሔርና የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር እየተጠቀሙበት ነው ።

እውነታው ይህ ነው።

ይሁንና የከተማችን የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ሥልጣኔን ልጠቀም ሳይሉ ከቢሮዬ ድረስ አቤቱታችሁን ይዛችሁ ኑ ሳይሉ ፣ እስከአሁን ድረስ በትሕትና አባቶችን በማክበር አቤት በማለት ላገልግላችሁ በሚል መንፈስ ችግሩን በሰላምና በሕጋዊ መንገድ ለመፍታት ከፓትርያርኩ ጋር የተወያዩበት መንገድ ከሲኖዶስ ጽ/ቤት ጋር የሚሄዱበት የትሕትና መንገድ ያስመሰግናቸዋል ።

አባ ማትያስ ግን የአዲስ አበባን ከንቲባ ሳይሆን የመቀሌን ከንቲባ ካላናገሩ የሚስማሙ አይመስልም ። የሳቸው ኢቀኖናዊ አካሄድ የታወቀ ነው ፤ ነገር ግን ሌሎች አባቶች ይህንን የትሕትና አቀራረብ መረዳት ካልቻሉና የውይይት ዕድሉን የማይጠቀሙት ከሆነ የአባቶችን ቃል ላክብር በማለት ወደ ፓትርያርኩ የመጡትና ከሲኖዶስ ጽ/ቤት ቤት ጋር መልካም ግንኙነት የፈጠሩት የከተማችን ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እስካሁን ያሳዩትን ጥረት እያደነኩ ከዚህ በኋላ የዲጅታል ወያኔ የአሉባልታ ዘመቻ ሳይበግራቸው የመስቀል አደባባይን ጉዳይ በሕግና በሰላማዊ መንገድ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው እንደከንቲባነታቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት መፍትሔ መስጠት የሚችሉ ጀግና መሆናቸውን አምንባቸዋለሁ ።

ይኸው ነው ። ሻሎም !!! Via Dr Zerihun Mulatu / ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ – ነጻ አሳብ የአዘጋጁ አቋም የለበትም!!

Exit mobile version