Site icon ETHIO12.COM

ኦርቶዶክስና አዲስ አበባ አስተዳደር መስማማታቸውን በጋራ አስታወቁ

“ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ” ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ የተሰጠ መግለጫ” በሚል የአዲስ አበባ አስተዳደር ይፋ እንዳደውረገው ሁለቱ አካላት ተስማምተዋል። ዜና እያማተቡና ጀምረው ነውጥና ጥላቻ ለሚዘሩት አስደናጋጭ ይሆናል።

መስቀል አደባባይ ላይ በተነሳ ጥያቄ መነሻነት ጉዳዩን የፖለቲካ ይዝት እንዲኖረው ሲደረግ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ሕዝቡን ለአመጽ በግልጽ ሲጠሩት ተሰምተዋል። ” ኦሮቶዶክስ በትንሹ 50 ሚልዮን ተከታይ አላት። ይህ ሕዝብ ከተነሳና አደባባይ ከወጣ …” እያሉ የትርምስ መመሪያ ሲቀርብም ሰንብቷል።

በተለይም አንዳንድ ሚዲያዎች በቃለ ምልልስ ሲያቀርቧቸው የነበሩ ሰዎች ረጩ የነበረው ቃላት ነገሮችን በርጋት የተከታተለው ህዝብ ወደ ጎን ባይለው የታሰበው ሌላ እንደነበር አመልካች ነው። ኦርቶዶክስ የደረጀና ስሟን የሚመጥን ተቋም እያላት እዛና እዚህ መግለጫ በሚሰጡ መሪዎች አማካይነት ቅሬታ የትሰማቸው አባቶች መኖራቸውን ገልጸን ጽፈን ነበር።

ቤተ ክርስቲያን የአመጽ ጠላትና የሰላም መሪ በመሆኗ ጥያቄዎቿን ክብሯን፣ ሃይማኖታዊ ተልዕኮዋን፣ መልካም አርአያነቷን፣ ከሁሉም በላይ አባትነቷን በሚመጥን ደረጃ አቅርባ ልታስፈጽም እንደሚገባ ሲነገሩ የነበሩ በዚህ ዜና እንደሚደሰቱ ይታመናል። ዛሬ ሁለቱ ወገኖች በጋራ ያወጡት መግለጫ ሙሉ ቃል ከስር ይነበባል።

በዛሬው እለት የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በመስቀል አደባባይና በጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ቦታዎች በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ የጋራ ውይይት አድርገናል፡፡

ውይይቱ በፍጹም ቅን ልቡና፣ መደማመጥና መግባባት በተሞላበት ስሜት ተካሂዷል፡፡

በመሆኑም በውይይቱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመስቀል አደባባይና የጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀትን በተመለከተ የተነሱትን ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም ቀጣይ ውይይቶችን መሠረት በማድረግ የማያዳግም ምላሽ ለመስጠት የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ወደፊትም ቤተ ክርስቲያንና የከተማ አስተዳደሩ በልማት፣ በሰላምና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀራርበን የምንሠራ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም.

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ

Exit mobile version