Site icon ETHIO12.COM

ከ “አበቃ አከተመላቸው” በኋላ …

እነዚህ ሁለት ከያኒያን አበቃ አከተመላቸው ባስባለ አደጋ ውስጥ አልፈው ዳግም የሚያስገርም ሥራዎችን
አበርክተዋል።
ጥላሁን ገሠሠ እሁድ ሚያዝያ 10 እለት 1985 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲአትር
ዜማዎቹን ሲያቀርብ ውሎ ወደ ቤቱ በመሄድ ገላውን ለመታጠብ ወደ ባኞ ይገባል።በጤናው አልተመለሰም በተዘጋ በር ውስጥ ሦስት ቦታ ተወጋግቶ በደም አበላ ተነክሮ ነበር የተገኘው በሩ ሲሰበር።
ማን ወንጀሉን ይፈፅመው የሚታወቅ ነገር
የለም።እንዲያው በ”ሆድ ይፍጀው” ሁሉ ነገር ተድበስብሶ ቀረ።ጥላሁን ከአደጋው በኋላ በለቀቀው አልበም ውስጥ ያለች
አንዲት ሥራ አለች “ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ”
የምትል አንገቱና እጁ ላይ ከደረሰበት አሰቃቂ ጉዳት በኋላ ዳግም ወደ ቀድሞ ብቃቱ መመለስ አይችልም ብለው ለተጠራጠሩ ሁሉ ምላሽ እንድትሆን ታስባ
የተሰራች የምትመስል የተስፋዬ ለማ ግጥምና ዜማ የአበጋዙ ቅንብር የሆነች በቫዮሊን ብቻ
የምትሄድ ሥራ አለችው።

በነገራችን ላይ አያሌው መስፍን ስለ አደጋው በሰጠው የምስክርነት ቃል መሠረት ጥላሁን በዛ ጭንቅ ውስጥ ሆኖ ደጋግሞ ይናገር የነበረው
“ሀገሬን አደራ” እያለ ነበር።

ነጊብ ማሕፉዝ ግብፅ አሉኝ ከምትላቸው ደራሲያን ግንባር ቀደሙ ነው።የኖቤል ሽልማትን በስነ-ፅሑፍ የወሰደው ደራሲ
በጥብቅ ዲስፕሊን ሕይወቱን መርቷል።
በቀን ለአንድ ሰዓት ይፅፋል፣ለአንድ ሰዓት
በአባይ ወንዝ ዳር በእግሩ ይንሸራሸራል፣
ሦስት ሲጋራ ያጨሳል።ሌላው ከነጊብ የሚያስገርመኝ ነገር ለልጁ የሰጠው ስያሜ ነው።”ኡም ኩልቱም”

እናማ በአንድ የጎደለ ቀን በ1994 እ.አ.አ
እንዲሁ በአባይ ወንዝ ዳር ብቻውን ሲንሸራሸር ኦማር አብድልራህማን በተባለ
ሰው አንገቱ ላይ በስለት ተወግቶ ከሞት
ለጥቂት ይተርፋል።ነጊብ ከ1994 በኋላ እነዚህን ሥራዎች ከነርቭ ጉዳቱ ጋር እየታገለ አበርክቷል
Echoes of Forgetness
Dreams of the Rehabilitation Period (2004)
The Seventh Heaven (2005)
Dreams of Departure (2007; posthumous translation)
Before the Throne (2009; posthumous translation)
In the Time of Love (2010; posthumous translation)
Heart of the Night (2011; posthumous translation)
The Quarter (short stories, 2019; posthumous translation)

Via Book for all

Exit mobile version