Site icon ETHIO12.COM

በሳዑዲ አረቢያ ያሉ ዜጎችን መለየት አስቸጋሪ መሆኑና፣ ስጋት ያስነሱ ጉዳዮች መኖራቸው ተገለጸ

ትህነግ አቶ አንዳርጋቸውን የመን አውሮፕላን ጣቢያ ድረስ ሄዶ ከየመን አውሮፕላን ማረፊያ በያዝቸው ሰሞን፣ የብሄርና የጎሳ የእርስ በርስ ጦርነት ጋር በተያያዘ ትህነግ ከአንደኛው ወገን ጋር ግንኙነት እንዳለው በይፋ ይነገር ነበር። በሶማሌ ከሚንቀሳቀሰው የአልሸባብ ጋር ተናቦ እንደሚሰራ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል። አሁን የተነሳው ጉዳይ በቀጥታ ከዛ ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ባይገልጽም ስልሳ ሺህ የሚሆኑ ሱዳን ስደተኞች ጣቢያ ገብተው ነበር ከተባሉት የትህነግ ሳምሪ የሚሰኘው ሃይል ውስጥ ግማሾቹ የት እንደገቡ እንደማያውቅ ዩኤን ኤች ሲ አር ማስታውቁን የሚያስታውሱ ነገሩን እዛ ድረስ እየለጠጡት ይገኛሉ።

በተለያዩ ሚዲያዎችና ማህበራዊ ገጾች ” ፍትህ በሳዑዲ ላሉ ወገኖች” የሚለው ድምጽና በምስል ተደግፎ የሚሰራጨው መረጃ የኢትዮጵያዊያንን ቀልብ የሳበ፣ ልብ የነካና እያስጨነቀ ያለ ጉዳይ ከሆነ ስነብቷል። መንግስት ቢያግዝ፣ ባልስልጣን ልኮ ቢወያይ፣ ኤምባሲው ምክክር ቢያደርግ የሚለወጥ ነገር አልተገኘም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞችን በተመለከተ በፓርላማ ጥያቄ ቀርቦላቸው በሰጡት መረጃ ጉዳዩ አሳዛኝ ብቻ ሳይሆን ለውሳኔ አሰጣጥ አዳጋች የሆነ ሚስጢር እንዳለው መናገራቸው መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።

“ባለፉት ወራት ችግር ውስጥ ሆነንም ቢሆን በርካታ ኢትዮጵያዊያንን ከሳዑዲ ወደሀገራቸው መልሰናል” ያሉት አብይ፣ ችግሩ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት እንደመንግስት ሪፎርም እየሰራ በመሆኑ፣ የሀገራቸው ዜጋ ስራ እንዲሰራና ኢኮኖሚያቸውን ለማሻሻል ከውጭ የመጡ ሰዎች የሚሰሩትን ስራዎች በራሳቸው ዜጎች ለማሰራት ፍላጎት ስላላቸው በመሆኑ “ይህን ማድረግ አትችሉም” ማለት እንደማይቻና ቅድሚያ ለዜጎቻቸው ስራ መስጠት ላይ አተኩረው መስራታቸውም ሃጢያት እንደሌለው አመልክተዋል።

“ከኢትዮጵያ በኩል ያለው ፈተና የእኛ ዜጎች በህገ ወጥ መንገድ የሄዱ መሆናቸው ነው፤ ሁሉም ፓስፖርት ያላቸው አይደሉም፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ስለመሆናቸው እርግጠኛ መሆን አይቻልም፤ ሁሉም ከዚህ ወደሳዑዲ የሄዱ ስለመሆኑም ለማወቅ ያስቸግራል፡፡ ቁጥራቸውም ከፍተኛ ነው። ወደ እንድ መቶ ሺህ ይጥጋል። ስለዚህ መከራም አብሮ እንዳይመጣ ቆም ብሎ ማጥናት ይፈልጋል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማ አብራርተዋል።

በሳዑዲ አሉ ከተባሉት ወገኖች ውስጥ ውትድርና ስልጥነው ወደዛ ያመሩ እንዳሉበት፣ እነሱን ለመለየት አስቸጋሪ መሆኑንና በደፈናው የሚወሰን ውሳኔ መዘዝ ሊያመጣ እንደሚችል አዲስ የተነሳው ጉዳይ መነጋገሪያነቱ ዜጎች ወደ የመን ዘልቀው እንዲያስቡ አድርጓቸዋል።

ወደ የመን ሄደው ወደ ከሳዑዲ የሚገቡ እንደሆኑ ስማቸውና አካባቢያቸው እየተጠቀሰ ሲገለጽ የነበሩት ይሁኑ ሌሎች፣ ከየትኛው የህብረተሰብ ክፍል ስለመሆናቸው፣ የስጋታቸው መጠን ምን ያህል እንደሆነ በዝርዝር ባይገልጹም ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የሰለጠኑ አሉበት” ብለዋል። ያም ሆኖ መንግስት ከሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር በቅርበት እየሰራን መሆኑንን አመልክተዋል።

“በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ቡድንም ተቋቁሟል፤ በደንብ አጥንተን ዜጎቻችንን ወደሀገራው እንመልሳለን፤ ስንመልስ ጥፋት የሚያስከትሉ ሰዎች ካሉበት ጥንቃቄ እናደርጋለን” ሲሉ አብይ አህመድ በጥቅሉ አስታውቀዋል።

ከየመን የብሄርና የጎሳ የእርስ በርስ ጦርነት ጋር በተያያዘ ትህነግ ከአንደናው ወገን ጋር ግንኙነት እንዳለው፣ በሶማሌ ከሚንቀሳቀሰው የአልሸባብ ጋር ተናቦ እንደሚሰራ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር። አሁን የተነሳው ጉዳይ ከዛ ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ባይገልጽም ስልሳ ሺህ የሚሆኑ ወደ ሱዳን ስደተኞች ጣቢያ ገብተው ነበር ከተባሉት የትህነግ ሳምሪ የሚሰኘው ሃይል ውስጥ ግማሾቹ የት እንደገቡ እንደማያውቅ ዩኤን ኤች ሲ አር ማስታውቁን የሚያስታውሱ ነገሩን እዛ ድረስ እየለጠጡት ይገኛሉ።

Exit mobile version