በሳዑዲና ኢራን በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል

በሳዑዲ አረቢያ እና ኢራን በሞት ፍርድ የሞት ቅጣት የሚፈጽምባቸው ሰዎች ቁጥር እአአ 2021 ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ብቻ በ18 አገራት 579 የሞት ቅጣቶች ተግባራዊ ሆነዋል ያለ ሲሆን፤ ይህም ከቀደመው ዓመታት ጋር ሲነጻጸር የ20 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ብሏል።

ኢራን 314 ሰዎችን በሞት በመቅጣት ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበባት አገር ሆናለች። በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ደግሞ በሞት የተቀጡ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ጨምሮ 65 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

አምነስቲ በዚህ ሪፖርቱ ላይ ቻይና አለመካተቷን ገልጿል። ቻይና የሞት ፍርድን አገራዊ ምስጢር አድርጋ ስለምትይዝ በአገሪቱ በሞት የተቀጡ ሰዎች አሃዝን ማወቅ ባይቻልም ቤይጂንግ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በሞት እንደምትቀጣ ይገመታል።

አምነስቲ ከቻይና በተጨማሪ በሰሜን ኮሪያ እና ቬትናም በተመሳሳይ የሞት ፍርድ ምስጢራዊ ስለምታደረግ በቀጠናው በሞት የተቀጡ ሰዎችን ዝርዝር ማወቅ አዳጋች ነው ብሏል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ እንደ ኢራን ባሉ አገራት በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር ጭማሪ ያሳየው ከአደኛ እጽ ዝውውር ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ የሚባሉ ሰዎች ቁጥር ከመጨመሩ ጋር በተያያዘ መሆኑን ገልጿል።

እአአ 2017 ላይ ኢራን 23 ሰዎችን በሞት የቀጣች ሲሆን እአአ 2020 ላይ ቁጥሩ በአምስት እጥፍ አድረጎ 132 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል።

በሳዑዲ አረቢያ ደግሞ በሞት የተቀጡ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በ140 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አምነስቲ ገልጿል። በሳዑዲ በዚህ ዓመት መጋቢት ወር በአንድ ቀን ብቻ 81 ሰዎች በሞት መቀጣታቸውን ገልጿል።

ከእነዚህ ሁለት አገራት በተጨማሪ የኢትዮጵያ በጎረቤት አገራት በሆኑት በሶማሊያ እና በደቡብ ሱዳን እንዲሁም በየመን በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ገልጸዋል።

ዘገባው የቢቢሲ ነው

 • `”የዲሞክራሲ ኤቀንቃኝ ነኝ” ባዩ ህወሃትና በለውጡ ሂደት የተመዘገቡ አንኳር ውጤቶች
  በለውጡ ሂደት የተመዘገቡ አንኳር ውጤቶች በዴሞክራሲ ስም ምሎና ተገዝቶ ወደ ስልጣን የወጣው ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ “አብዮታዊ ዴሞክራሲና ልማታዊ ዴሞክራሲ” በሚል ርእዮት ስም ለ27 ዓመታት አገሪቷንና ህዝቧን እንዳሻው ሲያደርግ ቆይቷል። “አቀንቃኝ ነኝ” ባዩ ህወሃት ስልጣን በተቆናጠጠባቸው ዓመታት ውስጥ በስውርና በግልፅ በርካቶችን በሃሰት እየፈረጀ በመግደል፣ በማሰርና በማሰቃየት ብዙ በደል ፈፅጽሟል። ግፉ እየበረታContinue Reading
 • [የዘመን ሃቅ] አለማየሁ እሸቴ ” ማን ይሆን ትልቅ ሰው?”
  “ማን ይኾን ትልቅ ሰው” ደራሲ፥ ተስፋዬ አበበ ያንዱ ቤት ሲጎድል አንዱ እየተረፈው፣ ክፉና በጎዉን ዘመን ሲያሳልፈው፤ እኔ ግን መራመድ ከቶ አልቻልኩም ገና፣ ትኋን ደሜን መጦ ጨርሶታልና፣ ያ’ሥር ሣንቲም ቆሎ ክርሽም አደርግና፣ አንዷን ጣሣ ውኃ ጭልጥ አደርግና፣ ተመስገን እላለሁ ኑሮ ይባልና፤ መኖር በዚህ ዓለም ከፍላጎት ጋር ነው፣ ልናዘዝ በቁሜ ያጣ እንደሞተContinue Reading
 • [የሽግግር መንግስት] ሊቋቋም ነው !!
  ከከፍተኛ ጭቅጭቅ፣ ከከፍተኛ ንትርክ፣ ከከፍተኛ ትንቅንቅ በሁዋላ የብልጽግና የስራ አስፈጻሚ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም መወሰኑ ሾልኮ በወጣ አፈንጋጭ አማካይነት ይፋ ሆኗል። እንደ አፈንጋጩ ገለጻ የሚቋቋመው የሽግግር መንግስት ውስጥ በአገር ውስጥ ያሉም ሆነ በውጭ አገር ያሉ አማጽያን፣ ፖለቲከኞች፣ የዩቲዩብ ሰዎች፣ ፓርቲዎች፣ አስፈላጊ ከሆነ ግለሰቦች እገሌ ከእገሌ ሳይባሉ ይሳተፉበታል። የመንግስት ምስረታው የሚካሄደበት ቀንContinue Reading
 • [አክቲቪስቱ] የዓለም ጤና ድርጅት መሪ በድጋሚ ክስ ቀረበባቸው
  ከሚመሩት “የዓለም” በሚል የሚጠራው ድርጅት ዓላማና መርህ በማፈንገጥ ስልጣናቸውን ተጠቅመው የተራ አክቲቪዝም ስራ ላይ ተጠምደዋል በሚል የሚከሰሱት፣ በአባልነት የመዘገባቸው ትህነግ “አሸባሪ” ተብሎ የተፈረጀ መሆኑ እየታወቀና የሚመሩትን ድርጅት መርህ መጣሳቸው እየታወቀ በድጋሚ ድርጅቱን እንዲመሩ ብቸኛ እጩ መደረጋቸውን በመቃወም ተቆርቋሪዎች ክስ መሰረቱ። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለኢትዮጵያ ጥብቅና በመቆም የሚንቀሳቀሰው “የተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን” ማኅበርContinue Reading
See also  ከሱዳን ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሾልኮ የገባ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ

Leave a Reply