Site icon ETHIO12.COM

የጭካኔ ጥግ ! ኩላሊታቸውን እየሸጡ ለመኖር የተገደዱት አፍጋናዊያን

መቼስ አሜሪካ በአፍጋኒስታን ምድር የፈፀመቺውን ግፍና በደል ፤ ጭካኔና ሰቆቃ ስንዘረዝር ውለን ስንዘረዝር ብናድር የሚያልቅ አይሆንም !! በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ንፁኖችን ህፃን አዛውንት ሴት ወንድ ሳትል ጨፍጭፋ በመጨረሻም ሽንፈቷን ተከናንባ የወጣቺው አሜሪካ ተክላው የወጣቺው መዘዝ ዛሬም አፍጋናዊያንን እየለበለበ አሰቃቂውን ኑሮ እንዲገፉት እያደረገ ነው ።

ለበርካታ አመታት የአፍጋኒስታንን ኢኮኖሚ ያወደመቺውና ከጥቅም ውጪ ያደረገቺው አንሷት ዛሬ በታሊባን ተሸንፋ ተዋርዳ ስትወጣም ካፈርኩ አይመልሰኝ በማለት ጠንካራ የኢኮኖሚ ማእቀቦችን ጥላ የአፍጋናውያኑን ኑሮ የሲኦል አድርጋባቸዋለች ። በጦርነት ያቃታትን በኣኮኖሚ ለመበቀል መሆኑ ነው !

እናም ይህቺ ሀገር በአሁኑ ሰአት ከ 9.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የአፍጋሃኒስታንን ገንዘብ በሀገሯ አግዳለች ። ለዚህ ፕሬዝዳንት ጆባይደን የሰጠው ምላሽ ” የታገደው የአፍጋኒስታን ገንዘብ በአፍጋኒስታን ለገደሉ ዜጎቻችን ካሳ ይሰጣል ” የሚል እጅግ አሳፋሪ መልስ ነበር ። አዎ በርግጥ ከሊቀሰይጣኗ አሜሪካ ከዚህ የተለየ አይጠበቅም ።

አሜሪካ ይህንን ማድረግ ያስቻላት አፍጋኒስታንን በተቆጣጠረቺበት ወቅት የሀገሪቱ ገንዘብ በአሜሪካ በኩል እንዲንቀሳቀስና አሴቷም አሜሪካ እንዲቀመጥ በማድረጓ ነበር ።

በዚህ የአሜሪካ ገንዘብ ስርቆትና ማእቀብ የአፍጋናዊያን ኑሮ ተመሰቃቅሏል ። ዛሬ አፍጋናዊያን ኑሯቸውን ለመግፋት ቤተሰባቸውን ለማስተዳደር ኩላሊታቸውን መሸጥ ግድ ብሏቸዋል ያውም በ 1,500 ዶላር ብቻ !!!

ኑረዲን የተባለው አፍጋናዊ ለ AFP የሰጠው ቃለመጠይቅ በጣም አስደንጋጭ ነበር ። ኑረዲን ኩላሊቱን የሸጠበትን ሁኔታ ሲያወራ ” ቤተሰቦቼን ማስተዳደር አቃተኝ ለልጆቼ ስል ኩላሊቴን መሸጥ ነበረብኝ እናም በ 1,500 ዶላር ሸጥኩት ። ሌላ ምንም አማራጭ አልነበረኝም ። አሁን ግን ኩላሊቴን በመሸጤ ተፀፀትኩኝ በጣም ያመኛል ከባድ ነገር መሸከም አልችልም መስራት አልችልም ” ይላል ።

አሁን የኑረዲን ቤተሰብ ህልውና ያለው ጫማ እየጠረገ በቀን 70 ሳንቲም በሚሰራው የ 12 አመት ልጁ ላይ ነው ። አያሳዝንም ?

እንደውም ብዙ አፍጋናዊያን ኩላሊታቸውን ለመሸጥ ፈልገው ገዥ የሚያጡበት ሁኔታ ሁሉ ተፈጥሯል ። ህዝቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደለየለት ድህነት ውስጥ እያመራ ሲሆን የሚልሱት የሚቀምሱት ለማግኘት ኩላሊታቸውን መሸጥ ግድ ሆኖባቸዋል ። ከዚያም የተያያዥ በሽታዎች ተጠቂ ሆነው እየማቀቁ ይገኛሉ ። ለዚህ ሁሉ ተጠያቂዋ ወራሪዋ አሜሪካና አጋሮቿ ናቸው ።

የአሜሪካ ሀጢያት ቢያወሩት አያልቅም !!!

Seid_Mohammed_Alhabeshiy

Exit mobile version