Site icon ETHIO12.COM

ለቴሌኮም ወንጀል የሚውል መሳርያ ወደ ኢትዮጵያ ያስገባው የውጭ ሀገር ዜጋ እንዲቀጣ ተወሰነበት

ለቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል የሚውል የቴሌኮም መሳርያ ወደ ኢትዮጵያ ያስገባው የውጭ ሀገር ዜጋ በፅኑ እስራትና በገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ ተወሰነበት።

”ሚ/ር ሊ ናይዮንግ“ የተበላው ተከሳሽ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 761/2004 አንቀፅ 3 (1) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ውስጥ ከቻይና ሀገር ወደ ኢትዮጵያ በሚገባበት ጊዜ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ፍቃድ ውጭ የሞዴል ቁጥሩ TD-LTE‚SERIAL NUMBER 2153034036DWG2000‚BRAND INSTAR ሆኖ ሁለት ባለ 8 ሲም አንድ ላይ 16 ሲም ካርድ የሚወስድ “ጌት ዋይ“ የተባለ ለቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል የሚውል መሳርያ ከእነአክሰሰሪው በቦሌ አየር መንገድ በኩል ያስመጣ በመሆኑ በፈፀመው ከሚኒስትር መስርያ ቤቱ ፍቃድ ውጭ የቴሌኮም መሳርያዎችን ከውጭ ሃገር ማስገባት ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ ተመሰርቶበታል ።

በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረበው ተከሳሽም በአስተርጓሚ ታግዞ ክሱ ደርሶትና ተነቦለት የእምነት ክህደት ቃሉን አንዲሰጥ ሲጠየቅ ”ድርጊቱን በፍፁም አልፈፀኩም“ ሲል የፈፀመውን ወንጀል ክዶ ተከራክሯል ።

ዐቃቤ ህግም ዝርዝር የሰው፣የሰነድና የኢግዚቪት ማስረጃዎችን አቅርቦ በማሰማቱና በማስረዳቱ ተከሳሽም መከላከያ አቅርቦ እንዲከላል በተሰጠው ብይን መሰረት መከላል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን ጥፋተኛ ነህ ሲል የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቷል ።

በዚህ መሰረት ፍርድ ቤቱ የካቲት 30/2014 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት ተከሳሽ ከዚህ በፊት የጥፋተኝነት ሪከርድ የሌለበት በመሆኑ አንድ የቅጣት ማቅለያ በመያዝ ተከሳሽን ያርማል መሰል አጥፊዎችን ያስተምራል ሲል በ9 ዓመት ፅኑ እስራትና በ50 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት አንዲቀጣ በመወሰን በኢግዚቪትነት የተያዘው የቴሌኮም መሳርያ ደግሞ ለመንግስት ገቢ አንዲሆን ትዕዛዝ ሰጥቷል

Via ministry of justice

Exit mobile version