Site icon ETHIO12.COM

12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ዘይት ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አስታወቁ

12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ዘይት ጂቡቲ ከሚገኝ አምራች ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አስታወቁ

ሰሞኑን የተከሰተውን የዘይት አቅርቦትና ዋጋ መወደድ ዙሪያ መንግስት ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት ገበያዉን ለማረጋጋት 12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ዘይት ጂቡቲ ከሚገኝ አምራች ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አስታወቁ።

ከዚህ ውስጥ 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ሊትር አገር ውስጥ የገባ ገብቶ እየተከፋፈለ መሆኑን ጠቁመዋል።

ቀሪዉ 7 ነጥብ 7 ሚሊየን ሊትሩ እየተጓጓዘ መሆኑን ተናግረዋል።

በቀጣይም በየወሩ 50 ሚሊየን ሊትር በሶስት ወራት 150 ሚሊዮን ሊትር በተከታታይ ግዢ ይፈጸማል ብለዋል።

ባለፈው አመት 1ነጥብ 1 ቢሊየን ሊትር ወደ አገር ውስጥ መግባቱንና በቀጣይ ገበያዉን ለማረጋጋት የተለያዩ ውሳኔዎች መተላለፋቸዉንና ወደ ትግበራ መገባቱንም ገልጸዋል።

መንግስት በዘይት ላይ የሚያደርገውን ድጎማ በሌሎች ዘርፎች ላይ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።

በዘላለም ግዛው – (ኢ.ፕ.ድ)

Exit mobile version