ባለፉት ሁለት ዓመታት 24 ቢሊየን ብር ድጎማ መድረጉ ተገለፀ- የጥር ወር የነዳጅ ዋጋ ላይ መጠነኛ ክለሳ ተደረ

ETHIOPIA - 1991: Fall of Addis Ababa (Ethiopia). Traffic jam in the gas station. On 1991. FDM-254-10. (Photo by Francoise De Mulder/Roger Viollet via Getty Images)

በ2013 በጀት አመት የጥር ወር የነዳጅ ዋጋ ላይ መጠነኛ ክለሳ ማድረጉን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የአለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሬን ተከትሎ በጥር ወር የነዳጅ ምርት አቅርቦት ላይ መጠነኛ የዋጋ ክለሳ መደረጉን በሚኒስቴሩ የንግድ ዕቃዎች ዋጋ ጥናት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሙላት ተናግረዋል።

መንግስት ከ2011 ዓ.ም ሚያዝያ ወር ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ  ጭማሪ ቢያሳይም መንግስት ጭማሬውን በመሸፈን ላለፉት 2 አመታት 24 ነጥብ 05 ቢሊየን ብር የዋጋ ሸክሙን ተሸክሞ መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡

በተጠናቀቀው የታህሳስ ወርም ምርቱ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የዋጋ ጭማሬ አሣይቷል ያሉት ዳይሬክተሩ መንግስት ሁሉንም የዋጋ ጭማሪውን ሸፍኖ ከሄደ በኢኮኖሚው ላይ አሉታዊ ተጸእኖ የሚያሳድር በመሆኑ መንግስት 75 በመቶውን እንዲሸፍን እና ቀሪው 25 በመቶ በህብረተሱ እንዲሸፈን ተደርጎ መጠነኛ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉን አብራርተዋል፡፡

ሌሎች መሰረታዊ ሸቀጦች የአቅርቦትና ስርጭትን በተመለከተ የጊዜ ሰሌዳቸውን ጠብቀው ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለህብረተሰቡ እየተሰራጩ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ካሳሁን የኮቪድ 19 ወረርሺኝ ተከትሎ ገበያውን ለማረጋጋት በተደረገው ጥረት ላለፉት ስድስት ወራት  ከ 392 ሚሊየን ሊትር በላይ ዘይት እና 4 ሚሊየን ኩንታል በላይ ስኳር እና ከ 8 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሩዝ ምርት ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ መደረጉን ተናግረዋል።

አሁን ላይ የ 5 በመቶ ቀረጥ እየከፈሉ ምርቶቹን እንዲያስገቡ መደረጉ ተገልጿል፡፡

በቀጣይም የቀረጥና የታክስ ሁኔታዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንደ አስፈላጊነቱ የሚታይበት ሁኔታም እንዳለ ተገልጿል፡፡

ሀገሪቱ ከወጪ ንግዱ የምታገኘው የገቢ መጠን እና ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገቡ ምርቶች የምታወጣው የንግድ ሚዛን መጠን ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ሸቀጦችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት አስፈላጊ በመሆኑ ስትራቴጂ ተቀርጾ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል።

በዚህም የዘይት ምርት በሀገር ውስጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራነው ያሉት አቶ ካሳሁን 2 ፋብሪካዎች ዝግጅታቸውን አጠናቀው  ወደ ስራ የገቡ ሲሆን ሌሎችም በቀጣይ እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡

ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚደረገው ጥረት በሌሎች የመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል፡፡

FBC


Leave a Reply