Site icon ETHIO12.COM

“ምግቤን ከጓሮዬ”

(ዋልታ) የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ አይ ሲ ቲ ፓርክ አካባቢ “ምግቤን ከጓሮዬ” በሚል ሀገር ዐቀፍ የወጣቶች የከተማ ግብርና ማስጀመሪያ መርሃግብር እያካሄደ ነው፡፡

በማስጀመሪያ መርኃግብሩ ላይ የተገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪል ማኅበራት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ማንኛውንም ጫና ለመቋቋም ከሰፊ የእርሻ ልማት እስከ ጓሮ በሚገኙ አነስተኛ ቦታዎች መልማት አለባቸው፡፡

ሀገርን በማልማት በምግብ ራስን መቻል የሁሉም ኃላፊነት በመሆኑ ሁሉም ኅብረተሰብ ያለምንም ልዩነት ሊተገብረው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መለሰ አለሙ በበኩላቸው በምግብ ራስን ለመቻል ወጣቶችና ሌሎችም የጀመሩትን የልማት ሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል::

”ምግቤን ከጓሮዬ’ ንቅናቄው ለሦስት ወራት እንደሚቆም ተገልጿል፡፡

ወጣቶቹ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡ ሲሆን በከተማ ግብርና በመስኖ የለማ ስንዴ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተስፋዬ አባተ – (ዋልታ)

Exit mobile version