Site icon ETHIO12.COM

የወንጀል ምርመራና ክስ ኮሚቴ የምርመራ ስራውን አጠናቆ ወደ ክስ ምስረታ ሊገባ ነው

የወንጀል ምርመራና ክስ ኮሚቴ በቀጣይ ጥቂት ወራት ውስጥ የምርመራ ስራውን አጠናቆ ወደ ክስ ምስረታ ሊገባ ነው


የሚኒስትሮች ግብረ ሀይል የወንጀል ምርመራና ክስ ኮሚቴ በጦርነቱ የተፈጸሙ ወንጀሎችን በተመለከተ በቀጣይ ጥቂት ወራት የምርመራ ስራውን አጠናቆ ወደ ክስ ምስረታ ሊገባ ነው።

የሚኒስትሮች ግብረ ሃይል ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ታደሰ ካሳ፤ የተባበሩት መንግስታት ሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከወራት በፊት በጋራ ባካሄዱት ዝርዝር ሪፖርትና ምክረ ሃሳብ መሰረት ገቢራዊ ለማድረግ ግብረ ሃይሉ እንደተቋቋመ አስታውሰዋል።

የተቋቋመበት አቢይ ዓላማም በጦርነቱ የደረሰውን ጥፋት አፋጣኝ ምላሸ ለመስጠትና ተጎጂዎችን መልሶ የማቋቋም ሰራን ለማቀላጠፍ የድርጊት መርሀ ግብር ቀርጾ ወደ ስራ ከገባ አምስት ወራት ሆኖታል።

ግብረ ሃይሉ የሃብት ማሰባሰብ፣ በተፈናቃዮች፣ በጾታዊ ጥቃት ጉዳዮች፣ የወንጀል ምርመራና ክስ በሚል በአራት ኮሚቴዎች ተዋቅሮ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለትም ከሶስት ወራት በፊት ጀምሮ በንዑሳን ኮሚቴዎች የተከናወኑ ዝርዝር ሪፖርቶችን ገምግሞ ቀጣይ የፖለቲካና አሰራር አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

ካሳለፍነው ህዳር ጀምሮ ግልጽ የድርጊት መርሐ ግብር ነድፎ ሲንቀሳቀስ ከነበረባቸው ጉዳዮች እንዱ በጦርነቱ የተፈጸመ ወንጀል ተጠያቂነትን ማረጋገጥና ስደተኞችና ተፈናቃዮችን መልሶ ማቋቋም እንደሆነ ገልጸዋል።

የወንጀል ምርመራና የክስ ኮሚቴው በአማራ፣ አፋርና ትግራይ ክልሎች የሚያካልል ቢሆንም ጦርነቱ ወደ አማራና አፋር ከቀጠለ በኋላ ምርመራው በሁለቱ ክልሎች ማተኮሩን ተናግረዋል።

የወንጀል ድርጊት መፈፀሙን ማረጋገጥ አስፈላጊ በሆነባቸው አካባቢዎች ስፋትና የወንጀሉ ውስብስብነት አንጻር ጊዜ መውሰዱን ገልፀው፤ በቀጣይ ጥቂት ወራት ውስጥ የምርመራ ስራውን በመቋጨት ወደ ክስ ምስረታ ይገባል ብለዋል።

በጦርነቱ ከተፈጸሙ ወንጀሎች መካከል አንዱ ጾታዊ ጥቃት በመሆኑ ተጎጂዎችን በተጨባጭ መደገፍ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም ግብረ ሃይሉ መክሯል።

በጦርነቱ በተፈጸሙ ጥፋቶች ሁሉ እጁ ያለበት ሁሉ ተጠያቂ እንዲሆን የመንግሰት ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት እንዳለ ጠቅሰው ዋናው ጥፋት ግን በአሸባሪው ቡድን አማራና አፋር ክልል መፈጸሙን ገልጸዋል።

የወንጀል ማጣራትና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ ቡድን ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ 158 ከፍተኛ ባለሙያዎች ተካተውበት የጥፋት ድርጊቶችን የማጣራት ሰራው በመጠናቀቅ ላይ መሆኑንም ገልጸዋል።

በሶስት ወራት ውስጥ የምርመራ ስራውን አጠናቆ ክስ የመመስረትና ተጠያቂነት የማረጋገጥ ስራው ይጀምራል ብለዋል።

Thanks በጦርነቱ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ማቋቋምን በተመለከተም ግብረ ኅይሉ የተፈናቃዮችን ጥቅል መረጃ በትክክል አጣርቶ በማጠናቀር በሰብዓዊ ርዳታ የማዳረስና የማቋቋም ስራዎች እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

Exit mobile version